www.maledatimes.com በነ እስክንድር ነጋ ንብረት ዙሪያ የተሰየመው ችሎት ትዕዛዝ ሰጠ- MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በነ እስክንድር ነጋ ንብረት ዙሪያ የተሰየመው ችሎት ትዕዛዝ ሰጠ

By   /   December 8, 2012  /   Comments Off on በነ እስክንድር ነጋ ንብረት ዙሪያ የተሰየመው ችሎት ትዕዛዝ ሰጠ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 50 Second

ትናንት አርብ ሕዳር 28/2005 ዓ.ም የፌዴራሉከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ የንብረት ውርስ ላይ በሶስት ተከሳሾች ላይ የቀረበውን የአቃቤ ህግ አቤቱታ ተመልክቶ ትዕዛዝ መስጠቱ ተዘገበ። በዚህ መሰረት በ1ኛ ተከሳሽ በአቶ አንዷለም አራጌ ባለቤት ስም የተመዘገበው የቤት መኪና ፤ በ7ኛ ተከሳሽ አቶ እስክንድር ነጋ ስም የተመዘገበ 1 ቤትና ከእናታቸው በውርስ ያገኙት ተዳምሮ 2 መኖሪያ ቤቶች እና በባለቤታቸው ስም የተመዘገበ 1 የቤት መኪና ፤ እንዲሁም በሌሉበት በተከሰሱት በ16ኛ ተከሳሽ በአቶ አበበ በለው ባለቤት ስም ፥ የተመዘገበ መኖሪያ ቤት ላይ የቀረበውን የውርስ አቤቱታ ያደመጠው ፍርድ ቤቱ የ1ኛ ተከሳሽ የአቶ አንዷለም አራጌ ባለቤት በጠበቃቸው አማካኝነት መኪናዋ ልጆችን ትምህርት ቤት የምታመላልስ መሆኗን የጠቀሱ ሲሆን ፥ የ7ኛ ተከሳሽ የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ችሎት ፊት ቀርበው እንደማይከራከሩ ገልጸዋል።
የ16ኛ ተከሳሽ አርቲስትና አክቲቪስት አበበ በለው ባለቤት በትላንቱ ችሎት ባለመቅረባቸው ለታህሳስ 18 መጥሪያ ደርሷቸው ችሎት እንዲገኙ ትዕዛዝ አስተላልፏል። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ስለንብረቱ ጉዳይ እንደማይከራከርና በዚህ ጉዳይም ፍርድ ቤት መቅረብ እንደማይፈልግ መግለጹ
ይታወሳል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on December 8, 2012
  • By:
  • Last Modified: December 8, 2012 @ 11:50 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar