www.maledatimes.com የመንግስት ጉዳይ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ አንጻር - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የመንግስት ጉዳይ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ አንጻር

By   /   December 8, 2012  /   Comments Off on የመንግስት ጉዳይ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ አንጻር

    Print       Email
0 0
Read Time:13 Minute, 48 Second

በዚህ አመት የተለያዩ ክስተቶች እና ሁነቶች ተካሂደዋል በእርግጥም ለውጡ መሰረታዊ ለውጥ ሳይሆን ጅምላ የሆነ የሰዎች ወይንም ማህበራዊ ትእይንት የሆነ ለውጥ እንዳለ ነው የሚያሳየን ፣ከጠቅላይ ምንስትሩ ሞት እስከ አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትሩ ሹም ብሎም  ከጋዘጠኞች እና ፖለቲከኞችን ማሰር እንዲሁም የፓትርያሪኩ ማሸለብ … የእስልምና እምነት ተከታዮች መብታችን ይከበር ጥያቄ እና እንዲሁም የኦርትዶክስ እምነት ተከታዮች የሃይማኖቷን መሪ እራሷው ትተካ እረ ብዙ ብዙ ነገሮች የሚያነሱ እና የሚጥሉ ሰለ ሃገሬ የሚሉት እና የተማሪዎች እሮሮ በየጊዜው ሲስተናገዱ ቆይተዋል ሆኖም ቀረ በአሁኑ ወቅት ክፉኛ የወቅቱ ወሬ የሆነው ደግሞ የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት መነሳትን አስመልክቶ የተነሳው አተካራ ወሬ ሲሆን ቀጣዩ ደግሞ የአዳዲሶቹ ሚንስትሮች ሹም ሽር ጉዳይ አነጋጋሪ ከመሆኑም በላይ አስጨናቂ ሆኖአል ።በተለይም የመራሹ ወያኔ ህወሃት ሰርአታዊ አስተዳደር ከአዲሱ ስርአት ጋር ሲነጻጸር የመልክ እንጂ የባህር ወይንም የጸባይ ምንም ልዩነት እንደሌለው አንዳንድ ግለሰቦች ይገልጻሉ ።የኢትዮጵያ መንግስት ካለው የፖለቲካ አንጻር ከደርግ መንግስት ጋር ሲያነጻጽሩት የዚህ አስተዳደር እድገቱ እና የዲሞክራሲያዊ ሂደቱ ከጊዜ ወደጊዜ እያሳየ ያለው በጣም ረቂቅ እና ምንም አሌ የማይባል ትልቅ የሆነ ምድራዊ ኮሜዲ እየሰራ ነው ያለው ። በተለይም በእድገት ሰበብ ያለውን እቅድ እና በደርግ መንግስት የነበረውን  ስርነቀል ድህነት ስራ ከወታደራዊ ጦርነት ጋር ተደማምሮ የነበረውን የስራ ሂደት ይህንን ስናይ ሰለ እድገቱ እና አጠቃላይ ዲሞክራሲያዊው ስራአቱን  እንዲህ በቀላሉ ኢትዮጵያን ከአለማችን ሃብታም ደረጃ ጋር ሊያወዳድራት የደረሰበት የ እድገት ደረጃ የሚያደርሳት ነው የሚመስለው (የሚያሳይ ይመስላል )። በአጠቃላይ የ ድገት ሂደቱ ከገንዘብ ምንዛሬአችን ጀምሮ እስከ አገሪቱ የእለታዊ የምግብ ግዠ ዋጋ ጋር ሲነጻጸር የትየለሌ ነው ኑሮ ዋጋውን ማየትም ሆነ መስማት የሚያስጠላበት ዘመን ደርሰን ሳለ ፖለቲካዊ ስልጣን ቅብብሎሽ በድሎት መከናወን ተጀምሮአል ። በተለይም ፓርላማው ህዳር 2ዐ ቀን 2ዐዐ5 á‹“.ም ባደረገው ስብሰባ ያገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቀድመው ከተሾሙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በተጨማሪ ሁለት ባለስልጣናትን  በምክትል   ጠቅላይ ሚኒስርት ማእረግ ለፓርላማው አቅርበው አፀድቀዋል ይህ ማጽደቃቸው ሲታይ ከምን አንጻር እንዴት ሊሆን ቻል የሚለውን ባለፈው ሁለት ወራት ቀደም ብሎ የአውራምባ ታይምስ አዘጋጁ አጠር ያለች የዜና መዋቅር አቅርቦ እንደነበር የሚታወስ ነው ፡፡ ይህ ጠቅላይ ማኒስትሩ የህገ-መንግሥቱን አንቀጽ 75 በመጣስ ያቀረቡት ሲሆን ፓርላማውም የህገ መንግሥቱን አንቀጽ 9(1) በማገናዘብ  የቀረበለትን ሹመት ሳይመረምር  ማጽደቁ የፓርላማው አሰራር በህገ መንግሥት የተሰጠው የህግ አውጭነት ስልጣን አተገባበር በሥራ አስፈፃሚው የሚመራ መሆኑን በግልጽ የሚያሳይ ነው፡፡ ህገ ወጥ የሆነውን ይኼንኑ የሚንስትሮች ምርጫ ቅድሞ አዘጋጅቶ ለይስሙላ በፓርላማ ውስጥ ለማከናወን መሞከር የማይታሰብ ህልም ወይንም ታስቦ ያልተፈታ ህልም ያላቸው ወያኔዎች ማድረግ የተሳናቸውን ሁሉ በጭካኔ ለማድረግ የሚቃኙበት አጭሩ አቋራጭ መንገዳቸው እንደሆነ ይፋ ነው ይህው ባለፉት ጊዜያት  በጥድፊያና ከህገ መንግስቱ ጋር በሚፃረር መልክ የወጡት- የፀረ ሙስና፣ የመያዶች፣ የፕሬስ እና የፀረ ሽብር አዋጆች ቀጣይ  አካል እንጂ አዲስ ነገር አይደለም፡፡በሽብር ወንጀል ሰዎችንም በመወንጀል ሰዎችን ለ እስር የሚዳርገውን ይሄንኑ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ሊያጸድቁበት የቻሉበት አንዱ መንገዳቸው ነው  በተጨማሪም የአጀንዳው አቀራረብም ሆነ የሹመቱ  አፀዳደቅ ከፓርላማው የአሠራር ሥነ-ሥርዓት ጋር ያልተጣጣመና በተለመደው ጥድፊያ የተከናወነ ነው፡፡ አጀንዳው ለፓርላማው አባላት  በተለመደው አሠራር መሠረት ያልተሰራጨ ከመሆኑም በላይ  በሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ከሕገ መንግሥቱ አንፃር  ሳይመረመርና   ሳይታይ መጽደቁ ይህንኑ ያረጋግጣል፡፡ይህንን ፖለቲካዊ ሂደታቸው ያልተጣመረላቸው የወያኔ መሪዎች ምርጫዎቻቸውን እነርሱ እንደ እንዝርት ሊያሾሯቸው የሚችሏቸውን እና እንደፈለጓቸው ሊያዟቸው የሚችሏቸውን አባሎቻቸውን በርእሰ ብሄር ስም አዋቅረው መያዛቸው ለእነርሱ የዲሞክራሲያዊ መንገድ ጎዳና ጠራጊ መስሎ ይታያቸዋል።ይህ ግን የኢትዮጵያ ፖለቲካ መንገድን የሚጠርግ ሳይሆን መንገዶቹን የሚያቆሽሽ ከመሆኑም በላይ ህብረተሰቡን ወይንም ትውልዱን ገዳይ የሆነ ሂደት የያዘ የመንግስት አጀና የሚስተናገድበት የተወሰኑ ሰዎች መድረኩን የሚያጋፍሩት ቴአትሩን ደግሞ ትቂቶቹ የሚተውኑት ሆነው ሲገኙ አጋፋሪዎቹ ከተጋፋሪዎቻቸው ውጭ እራሳቸውን ችለው የኳስ ሜዳ ጨዋታውን የሚያከናውኑት እና የመሃል ዳኞች ናቸው ።ከ እነሱው ውጭ ማናቸውም ነገር በማንም አይከናወንም ቁንጮ የተቀመጠው ሌላ ሆኖ ጎፈሬውን የሚያደምቀው ደግሞ ሌላ መሆኑን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጋለጠ የመጣው አሰቃቂው ስራታቸው እራሱ አፍጥጦ መናገር ጀምሮአል ።ፖለቲካዊ ፋይዳቸው ለራሳቸው የጠመመባቸው የወያኔ አመራር አካላት በሰዎች ጃንጥላ ስር በመጠለል ዛሬም ነገም የሃገሪቱን ግዞተኝነት እየመራ መክረምን ይመኛል ህዝቡስ ምን ያስብ ይሆን የመንግስት ጉዳይ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ እና የፍላጎት አንጻር ሂደቱ ለሃገሪቱ ጠቃሚ ይሆን ወይስ የግላዊ ወይንም የፖለቲካ ፓርቲ ጥቅም የሚከበርበት ደህንነቱስ ለሃገር ወይስ ለግለሰብ አሊያም ለፓርቲ እና በአንድ ዘር ለተዋቀረው መንግስታዊ ድርጅት ?ለወደፊቱም ቢሆን ይህች አሳብ ጠቃሚ ነች እና ካነበብኩት ጋዜጣ ላይ ቀንጨብ አድርጌ ወሰድኳት ሰለወደድኳትም ሃሳቡም ለኔም ሰለተስማማችኝ እንዲህ አቀረብኳት “ቀና ቀናውን ያሳየንና ሂያጁም መጪውም በፍቅርና በዕድገት አኳያ ይተያዩ ዘንድ ተግተን እንፀልይ፡፡ ራዕይ ቅን ልቡና ይፈልጋልና “ልብና ልቦና ይስጠን” ብለን እናሳርግ እንደሰባኪው ካህን!
አገራችን “ልጓም የሚጠብቀውን፣ ሜዳ የማይበቃውን ጮሌ ሠንጋ ፈረስ እንደ እንዝርት የሚያሾር ምርጥ ፈረሰኛ – መሪ፣ ምርጥ ኃላፊ፣ ምርጥ ባለሙያ፣ ምርጥ ካህን ወዘተ ትሻለች፡፡ አዲሱ አሮጌውን በሚተካበት ሂደት፤ ጉዳይ የሥልጣን – ሽግሽግ – ተኮር ሳይሆን ምርጥ አመራር የመፍጠር መሆን ይኖርበታል፡፡ አህያይቱን የመከራት ውሻ “ተይ ወይዘሮ አህያ አታናፊ:- የፊተኛው መቀስቀሺያ፣ ሁለተኛው መቅረቢያ፣ ይሄኛው መበያ ነው” እንዳለው ቀና አመራር ከዚህ ነፃ መሆን ይገባዋል፡፡ አለበለዚያ የዲሞክራሲም፣ የፍትሕም፣ የልማትም፣ የመልካም አስተዳደርም ተስፋ ያገሬ ባላገር አለ እንደሚባለው፡- “የፖለቲካ ነገር፣ መጀመሪያ ዘርዛራ ወንፊት፣ ቀጥሎ ጠቅጣቃ ወንፊት፣ በፍፃሜው መሹለኪያ የሌለው ድፍን ወንፊት” እንዳይሆን መጠንቀቅ ተገቢ ነው፡፡”

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on December 8, 2012
  • By:
  • Last Modified: December 8, 2012 @ 4:00 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar