www.maledatimes.com አገራችንን እያቃጠለ ያለዉን እሳት ተረባርበን እናጥፋ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አገራችንን እያቃጠለ ያለዉን እሳት ተረባርበን እናጥፋ!

By   /   December 9, 2012  /   Comments Off on አገራችንን እያቃጠለ ያለዉን እሳት ተረባርበን እናጥፋ!

    Print       Email
0 0
Read Time:12 Minute, 30 Second

በኢሳ አብድሰመድ

በሀገር ውስጥም ሆነ በወጪው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን  አንድነትን ከማሰብ ይልቅ ግላዊ ጥቅምን ማሳደድን የተሻለ ምርጫ አድርገው ይዘውታል በሃገራችን ውስጥ ያሉ ፓርቲዎች  የአቅማቸውን ያህል ቢንቀሳቅሱም በሀገራቸው ውስጥ የሚደረግባቸው ተጽእኖ   አንደሁለተኛ ዜጋ መታየታችው  ሀገር ያወቀው ጸሃይ  የሞቀው ጉዳይ ነው::

አንዳንዶች ደግሞ የፓርቲዎችን  ስም  ተገን  በማድረግ  እንደ አስመጭና ላኪ የንግድ ስራውን አጧጡፈውታል  በርግጥ  የፓርቲዎችን  መኖር  መጥላቴ ወይም  መንቀፌ ሳይሆን በሀገር  ውስጥም  ይሁን በውጭ ያሉ ፓርቲዎች  እንደገዢው የወያኔ  ቡድን  ያመጣው  የዘር  ክፍፍል በሽታ ወይንም  ቫይረስ  ተጠናውቷቸዋል  በመሆኑም በዘር ተደራጅቶ  መጉአዝን አማራጭ አድረገው  ሲከተሉ  ይስተዋላሉ ። ከሀገራዊ ፓርቲነት ይልቅ  በጎሳና በዘር ላይ ማተኮርን ይመርጣሉ። ይህም  ደሞ ከአንድነት ይልቅ መበታተንን  የሚያስከትል  በሽታ ነው ።

በጋራ መስራት በፓርትዎቻችን ዘንድ  ተራራን የመናድ ያክል ከባድ ሆኖባቸዋል ። ፓርቲዎች  የጋራ  አቁዓም  ኖሯቸው  ለሀገር ሉዓላዊነት በአንድ ላይ የመስራት ፍላጎታቸውን ወደጎን ትተውታል። የተዋቀሩበትንም  ክቡር አላማ  የዘነጉት ይመስላል።

ኢትዮጵያውያን ለዘመናት አንድ አድረጎ  ያኖረንና  ያጣመረን  የነፃነት አርማችን ሰንደቃችን መሆኑ ይታወቃል :: ሕብረ ብሂራዊነት በማይዋጥላቸው አና ጠባብ አመለካከትን  በሚያራምዱ ጥቂት ሆዳሞች  ዘንድ ግን አንድነት ትርጉሙን  እንዲስት: ህብረት እና  እድገት የሰለጠነባትን  ሀገር  የመገንባት ሕልም ወደ  ጎን ችላ እየተባለ ግላዊ ጥቅም ከሀገር ጥቅም አንዲቀድም አየተደረገ  ያለበት ግዜ ላይ  ደርሰናል ::

ሕዝብ ሰላማዊ የሆነ ዲሞክራሲያዊ  ስርዓት ሰፍኖ ማየት የማንኛውም  ሰባዊ እና ዲሞክራሲያዊ  መብቶቹ  ተከብረው እና ሀገር ባለፀጋ  ሆና ማየት የምን ጊዜም ፍላጎቱ ቢሆንም ሀገራችንን  እንደመዥገር  ተጣብቀው አየመጠመጡ  ባሉት የሰሜን  ወንበዲዎች ዘንድ ጆሮ ዳባ ልበስ አየተባለ እዚህ ደርሰናል’

ኢትዮጵያ  ዘመን ተሻጋሪ የሰንደቅ አላማ ታሪክ ካላቸው ሃገራት መካከል አንዷ ናት ፤ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እስከ 1890 ዎቹ  ሁለተኛ  አጋማሽ  ድረስ በቀለማትም  አንድ ወጥ አልነበረም ፤ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት ያሉት ሰንደቅ አላማ ቀለማት ወጥነት ባለው በተያያዙ አራት ማእዘናት በጥቅም ላይ የዋሉት በ1890 ዎቹ  መጨረሻ ነው ፤

በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ለሰንደቅ አላማ ልዩ ትርጓሜና ስርፀት የተሰጠው በ1898 እንደሆነ ይነገራል ፤ ቢጫ የብርሃን፣ ቀይ የመስዋዕትነትና አረንጓዴ የተስፋ ምልክት ተደርጐ ይወሰዳል፡፡ ከዚህ በኋላ ሰንደቅ አላማችን አንድ ጊዜ መንፈሳዊ ሌላ ጊዜ ፖለቲካዊ ትርጓሜ እየታከለበት ዘመን ተሻግሯል ፤ እኛ ኢትዮጵያውያን በሰንደቅ አላማችን ስም በጐም ሆነ መጥፎ ተግባራት በተፈፀሙባቸው ዘመነ መንግስታት ጭምር ለሰንደቅ አላማችን ያለን ፍቅርና ክብር እጅግ ጥልቅ ነው ፤  ምንም  እንኳን የወያኔ መንግስት ባንድራ ጨርቅ ነው ቢልም  ጥንታውያን ጀግኖች ወላጆቻችን ሰንደቅ አላማችንን ይዘው አስደናቂ ትግልና ውጊያ በማካሄድ ከባዕዳውያን ቀጥተኛ ተፅዕኖ ነፃ የሆነች ሃገር አስረክበውናል ፤ በአንዲት ባንዲራቸው ጥላ ስር በመሆን ወራሪውን ሃይል በእግዚአብሔር ረዳትነትና እና በታማኝ አርበኞች ጀግንነት ከቀኝ ግዛት ነጻ የሆነች ሀገር አቆይተውልናል ፡፡

ኢትዮጵያውያን ለአያሌ ዘመናት ብሔራዊ ክብራችንን ባዋረደና እንደ ህዝብ አንገታችንን ባስደፋን አስከፊ የድህነት ማቅ ውስጥ ኖረናል ፡፡ አሁን ሰንደቅ አላማችን የጭቆናም የጭፍጨፋ አርማ አይደለም። የሰንደቅ አላማችን አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት እንደ ዱሮው ሁሉ የልምላሜ የተስፋና ለነፃነት የሚከፈል መስዋዕትነት ምልክቶቻችን ናቸው ። እራሱን መንግስት አድርጎ በመሰየም ኢትዮጵያንና ህዝቧን እያማረረ የሚገኘው የወያኔ ቡድን በግዴለሽነት ሀገራችን ወደ ድህነት: ሁከት: እና ብጥብጥ  ዜጎችን በማፈን  በማፈናቀል  አና በማሳደድ ተግባሩ የሚታወቅው የአቶ መለስ የአገዛዝ ስርዓት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት በኋላ  የፖሊሲ  ለውጥ  ሳያደርግ  እየመራት ይገኛል፤ ዜጎቿ እውነት እና ፍትህ ናፍቋቸው የፍትህ ያለህ እያሉ ቀን ከሌሊት እየጮሁ ይገኛሉ፤ ንፁሃን ዜጎች በወያኔ ሴራ እየተቀጠፉ ናቸው፤ እጅግ ሰብዓዊነት በሌለው ሁኔታ ዜጎች እየተደበደቡ እና እየተገደሉ ይገኛሉ፤ ስለመብት መጠየቅና ሰው ሁኖ መገኘት እንደ አሸባሪነት ከመታየቱም አልፎ ለመብታችን በመቆማችን  ብቻ አሸባሪዎች እየተባልን እንጠራለን፤ የኢትዮጵያ  ህልውና  ቀን በቀን እያሽቆለቆለ አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን እየተመለከትነው ነው:: እኛ ኢትዮጵያውያን እንደዜጋ ይሄን አሰቃቂ በደል ቁጭ ብለን ማየት አይገባንም፤ ሀገራችን የአምባገነኖች መፍንጫ  ሁና  ንፁሃን ዜጎቿ ስቃይና መከራ ሲፈራረቅባቸው ማየት ህመም ነው፤ ሀገራችን ክብሯን  ጠብቃ  መኖር አለባት እንጂ የአምባገነኖች  መነሀሪያ መሆኗ ሊያበቃ  ይገባል፡፡ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ  አገራችን እያቃጠለ ያለዉን እሳት ተረባርበን እናጥፋ! ይህ እሳት በአስቸኳይ ካልጠፋ ወደፊት አገራችን ብለን የምንመካባት ኢትዮጵያ አትኖርም::  በዘር በሃይማኖት በቋንቋ ሳንከፋፈል እጅ ለእጅ ተያይዘን በመነሳት አገራችን ኢትዮጵያን የአምባ ገነን አመራርን  ከስሩ ነቅሎ ለማስወገድ  የተባበረ  ኢትዮጵያዊ  ክንዳችንን በአንድ ላይ ልናውለው  ይገባል::   የጋራ ሃላፊነትን ለመወጣት ለሚተሳሳቡና ለጋራ ጥቅሞቻቸው መከበር ውጤት ለሚያስመዘግቡ እንጂ ለጥቂት ግለኛ ሆዳሞች እንዳልሆነ እስከ መጨረሻው በመፅናት ታሪክ እንሰራለን::  ስለዚህ አገራችንን እያቃጠለ ያለዉን እሳት ተረባርበን እናጥፋ! ይህ እሳት በአስቸኳይ ካልጠፋ ወደፊት አገራችን ብለን የምንመካባት ኢትዮጵያ አትኖርም:: በዘር በሃይማኖት በቋንቋ ሳንከፋፈል እጅ ለእጅ ተያይዘን በመነሳት አገራችን እንታደግ ::

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar