www.maledatimes.com ሰሞኑን በቴዲ አፍሮ ስም የተለቀቀው የጴንጤ መዝሙር፤ የቴዲ አፍሮ አለመሆኑ ተገለጸ፤,…ድርጊቱም “ከክርስትና አማኞች የማይጠበቅ…” በሚል ተኮንኗል። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሰሞኑን በቴዲ አፍሮ ስም የተለቀቀው የጴንጤ መዝሙር፤ የቴዲ አፍሮ አለመሆኑ ተገለጸ፤,…ድርጊቱም “ከክርስትና አማኞች የማይጠበቅ…” በሚል ተኮንኗል።

By   /   December 12, 2012  /   Comments Off on ሰሞኑን በቴዲ አፍሮ ስም የተለቀቀው የጴንጤ መዝሙር፤ የቴዲ አፍሮ አለመሆኑ ተገለጸ፤,…ድርጊቱም “ከክርስትና አማኞች የማይጠበቅ…” በሚል ተኮንኗል።

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 38 Second

(EMF) ሰሞኑን በቴዲ አፍሮ ስም የተለቀቀው የፕሮቴስታንት ወይም በተለምዶ የጴንጤ መዝሙር፤ የቴዲ አፍሮ አለመሆኑን፤ ቴዲ አፍሮን ያነጋገሩ የኢ.ኤም.ኤፍ ምንጮች ገልጸዋል። “በይቅርታ ተቀበለኝ” የሚለው መዝሙር በቅድሚያ የተለቀቀው በፕሮቴስታንት ክርስትና አማኞች ድረ ገጽ ላይ ሲሆን፤ ከዚያ በማከታተል በ24 ሰዓት ውስጥ በፌስ ቡክ እና በሌሎች ማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ ዜናው በሰፊው መሰራጨቱ ይታወቃል። ድርጊቱም “ከክርስትና አማኞች የማይጠበቅ…” በሚል ተኮንኗል።

<iframe width=”560″ height=”315″ src=” http://www.youtube.com/embed/eyk0ihCNpuk” frameborder=”0″ allowfullscreen></iframe>

ሆኖም “ስለመዝሙሩ ቴዲ አፍሮ ምንም አያውቅም። ሌላ ሰው የቴዲ አፍሮን ድምጽ አስመስሎ የዘፈነው ነው።” ተብሏል። በእርግጥም ይህ ከተነገረን በኋላ መዝሙሩን በድጋሚ ስንሰማው፤ ዘማሪው ድምጹን ብቻ ሳይሆን የአዘፋፈን ስልቱን ጭምር የቴዲ አፍሮን አስመስሎ ለመጫወት ጥረት ማድረጉ በግልጽ ያስታውቃል። ይህ ዜማ ቴዲ ቀደም ሲል ከተጫወተው “ንገሪኝ ካልሽማ” ከሚለው እና ከሌሎቹ ዜማዎቹ ቆንጠር ቆንጠር ተደርገው ከተወሰዱ በኋላ የተገጣጠሙ መሆናቸው ነው የተገለጸው። ዘማሪው ዘፈኑን ጥሩ አድርጎ ቀይሮ ቢጫወተውም፤ ይህንኑ የድምጽ ክሊፕ ከቴዲ አፍሮ ምስል ጋር በማቀናበር የተለቀቀው ቪዲዮ ተራ ዝናን ለማግኘት የተደረገ አሳፋሪ ተግባር መሆኑን ብዙዎች ይስማሙበታል።

በዚህ ነጠላ ዜማ ምክንያት፤ ቴዲ አፍሮ “ሃይማኖቱን ቀይሯል፤ ከ’ንግዲህ አይዘፍንም” የሚል ወሬ በሰፊው ከመሰማት አልፎ፤ በሌሎች የአሜሪካ ክፍለ ግዛቶች የሚያደርጋቸው ዝግጅቶች የሚሰረዙ መሆናቸው በወሬ ደረጃ ቢሰራጭም፤ በቅርብ የሚደረጉት የኦሃዮ፣ የቦስተን እና የላስ ቬጋስ የሙዚቃ ዝግጅቶች የሚደረጉ መሆናቸውን የቴዲ አፍሮ ፕሮሞተሮች በተለይ ለኢ.ኤም.ኤፍ ገልጸዋል።

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar