www.maledatimes.com የሚኪያስ የጨለማ ጉዞ ከየት ወዴት - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሚኪያስ የጨለማ ጉዞ ከየት ወዴት

By   /   December 17, 2012  /   Comments Off on የሚኪያስ የጨለማ ጉዞ ከየት ወዴት

    Print       Email
0 0
Read Time:25 Minute, 57 Second

ባለፈው ሳምንት አርብ ምሽት እኩለ ለሊት ላይ ነበር ለወላጅ እና ዘመድ አዝማዶቹ አስደንጋጭ እና አሳዛኝ ዜና ከአካባቢው የእለት ተረኛ ፖሊስ አባላት የልጃቸውን ህይወት ድንገተኛ አደጋ ላይ መውደቅ የሰሙት ።ይህንን ያልተጠበቀ ዜና መስማትም አይደለም ይሆናል ታስቦ አይታወቅም ፡ምናልባትከልጁ የአስተዳደግ እና የተፈጥሮ ባህርይ አንጻር እንዲህ አይነቱን ነገር መጠበቅም ሆነ መገመት ከባድ የሆነ የአይን ብዥታን ይፈጥራል ።በቺካጎ እና አካባቢዋ የሚገኙት የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ አባላቶችም ሆኑ ሌሎች ዜጎች የዚህ ልጅ ወጣት በአጭር መቀጨት ያላስቆጫጨው ያሉ አይመስሉም  ሁሉም እንደ እግር እሳት አንገብግቦአቸዋል አቃጥሎአቸዋል አዝነዋል ተክዘዋል አንብተዋል ሃዘናቸው አብሮአቸው እንደሚዘልቅ ትልቅ የፍቅር መተሳሰብ  ያሳዩበት አጋጣሚ ….የሚኪያስ ህይወት በአጭር መቅረት

በደረቀው ለሊት የመጣው ይኸው አስከፊ ዜና የ እያንዳንዱን የኢትዮጵያዊ የልብ ስብራት ሆኖበታል በተለይም ወላጆቹን በቅርበት የሚያውቅ ሁሉ ሲያለቅሱ ያላለቀሰ ሲተክዙ ያልተከዘ ዝም ያለም አልነበረም ሁሉም በመንፈስ አብሮአቸው ተጉዞአል ።በእርግጥ ይህ ሎሆን የቻለበት ምክንያት በትምህርቱ ጎበዝ በባህርይው ቅን ሰውን አክባሪ እና ታዛዥ ሲሆን የወደፊት የኢትዮጵያ ባለ ራእይ የሆነ ወጣትን መነጠቅ አስመልክቶ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል ይኸውም የአስራ ስምንት አመቱ ታዳጊ ወጣት ሚኪያስ ተፈራ በየነ ።

የሚኪያስ ተፈራ  የህይወት ታሪኩ ከሚያሳየው አጭር መስመር ለአንባቢዎቻችን እንዲህ ብናስተዋወቃችሁ ወደድን እና ሚኪያስ ተፈራ ማን ነው ወደሚለው አጭር መዘርዝር ገባን …..ሚኪያስ ከአባቱ ከዶ/ር ተፈራ በዬ እና ከ እናቱ ወ/ሮ ንግስት አለሙ ገብረ ህይወት እንደ አውሮጳ አቆጣጠር በኖቬምበር 12/1994 አመተ ምህረት በባህርዳር ከተማ ተወለደ ፣ከዚያም አባቱ በስራ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ በተዛወረበት ወቅት ወደ አዲስ አበባ ከቤተሰቦቹ ጋር በመዛወር ኑሮውን ለአጭር ጊዜ በመዲናይቱ  አዲስ አበባ አደረገ ከዚያም በ1995 አመተ ምህረት እንደ ኤሮጳውያን አቆጣጠር ወደ አመሪካን በዳይቨርሲቲ ቪዛ ሎተሪ አማክይነት መጥቶ ይህወቱን በሚድ ዌስት አካባቢ በሚገኘው ኢሊኖይ ስቴት ሸምበርግ ከተማ ውስጥ ኑሮአቸውን አደረጉ በተለያዩ ጊዜያትም በቺካጎ እና አካባቢዋ ማድረጋቸውም መረጃዎች ቢጠቁሙም ህይወቱን ግን በስኬት መምራት እና የትምህርቱን ቀዳሚነት ያሳየበት በሸምበርግ በሚገኘው ትምህርትቤቱ ውስጥ ባለ ብዙ ታሪክ መሆኑ ከተለያዩ መረጃዎች ለመረዳት ችለናል ሚኪያስ ከአጎቶቹ አክስቶቹ እናቱ እና አብቱ እንዲሁም እህስቶቹ እና ሌሎች የቅርብ ዘመዶቹ ጋር በመሆን ህይወቱ እስካለፈበት ባለፈው ሳምንት አርብ ድረስ ከቤተሰቦቹ ጋር በደስታ ይኖረ የነበረ ፍልቅልቅ ወጣት ነበር ።ሚኪያስ በትምህርቱ በጣም ደስተኛ እና ጎበዝ ሲሆን በአጭር ረቀት ሩጫም ሃገራቸውን ካስጠሩት አትሌቶች ተርታ ይመደባል ተብሎ ትልቅ ስፍራ ከተሰጣቸው ታዳጊዎች መካከል አንዱ ነበር ።ህይወቱም ባለፈችበት እለትም የሩጫ ውድድር አከናውኖ የአሸናፊነትን ቦታ ተቀዳጅቶ ነበር ያሉት የቅርብ ዘመዶቹ ይህ ብቻም አይደለም በካሊፎርኒያ በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ውስጥ የሙሉ ስኮላር ሽፕ አግኝቶ ሊሄድ የቀረው 4 ቀናት ነበር የቀሩት ዛሬስ ምን ነካብን እና ህልሙን ባጭር አደረገው በማለት ስሜታቸውን መቆጣጠር እስኪሳናቸው ድረስ እንባቸውን ያረግፋሉ ፤ሃዘናቸው እውነትን ፍለጋ ጎዞ ላይ እንደሆነች ያሳያሉ የዚያችን እውነትን ፍለጋ አቋራጭ ጎዳና ማን ያገኛት ይሆን ? እንዴት የሚኪያስ ህይወት በአጭር ልትቀጠፍ ቻለች የሚለውን አወዛጋቢ ሃሳብ እነሱ ግን አይጋሩትም ሁሉም ይህ ሊሆን አይችልም ይላል በአጠቃላይ በችካጎ የሚገኘውን ህብረተሰብ እንዴት ? መቼ ?   ለምን ? በማን እና የት ? የሚሉት መሰረታዊ ጥያቄዎች አእምሮውን ወጥሮ ይዞታል ።

ለዚህም ምላሽ ለማግኘት ወላጆቹም ጥቂት ጊዜ ለምርመራ እንስጣቸው ይላሉ ወገኖቼ አሉ ዶ/ር ተፈራ በየነ በእኔ የደረሰ አይድረስባችሁ ነገር ግን የ እኔን ልጅ ጉዳት እንደ ልጃችሁ አይታችሁ ህብረታችሁን አሳዩኝ ውጤቱን ማየት ፍላጎት አለን ጉዳዩን በነጻ በሆነው ፍርድ ቤት እንዲታይልኝ በጋራ አብራችሁኝ እንጓዝ ዘንድ እጠይቃችኋለሁ ይላሉ ። የህግ ባለሙያው በሙያው ፣ወጣቱም በሃሳቡም ይሁን ባለው ሙያ ሌላውም ህብረተሰብ ቢሆን እንደ ቤተሰብ በቅርቡ በሚኪያስ ስም በምናወጣው አዲስ ዌብ ሳይት ሃሳባችሁን እንቀበላለን አንድነታችንን እናሳያለን ነገም ቢሆን በሌላው ወገናችን እንዳይደርስ ዛሬ ላይ ቆመን ምን ደረጃ ላይ እንዳለን ማሳየት አለብን ይላሉ ዶ/ር ተፈራ ። ወደ ሚኪያስ የህይወት ታሪክ እንመለስ እና ወጣቱ ጎበዝ ተማሪ ካገኛቸው አጠቃላይ አዋርዶችን ጠቀስ እናድርግላችሁ እና የእውቀቱን አድማስ ስፋት እንገራችሁ ፤

፩ኛ በአጠቃላይ በትምህርት ውጤቱ ሁልጊዜም የማእረግ ተሸላሚ ነበር

2ኛ በ2007 የአሜሪካን ፕረዚዳንት ጆርጅ ቡሽ የከፍተኛ ትምህርት ከፍተኛ ተሸላሚ ነበር።

3ኛ በ2009 በአሜሪካ ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ የከፍተኛ ትምህርት ማእረግ ተሸላሚ ነበር

4ኛ በ2011 በትምህርት ቤቱ የስፓኒሽ ኦነር ሶሳይቲ ኢንዱኬትድ በመሆን ተመራጭ ሆኖአል

5ኛ በ2012 ከትምህርት ቤቱ የከፍተኛ የትምህርት ማእረግ  ሜዳሊያ ተሸላሚ

6ኛ በ2012 የሚድ ሰበርብ ሊግ ሶስተኛ ደረጃ ተሸላሚ

7ኛ በ2012 በስቴት ኦፍ ኢሊኖይ የስቴት ስኮላር ሆኖ ተመረጠ

8ኛ በ2012 የናሽናል አዋርድ ዊነር ነበር

9ኛ በ2012 በካሊፎርኒያ የሚገኘው የፖሞና ኮሌጅ ምኡሉ ስኮላር ሺፕ የማጠቃለያ ተመራጭ በመሆን የመግቢያ  ጥያቄና መልስ ዝግጅት ወይንም ኢንተርቪው ለማድረግ በጉጉት ላይ ሳለ በአስከፊው አደጋ ህይወቱን የተነጠቀ ታላቅ ሰው መሆኑ የሚያሳዩ አጭር መዛግብቶቹ ያሳያሉ ።

 

በልጅነት እድሜው ከወላጆቹ ጋር የአሜሪካንን ህይወት አንድ ብሎ የጀመረው ይሄው ወጣት (ሚኪያ ተፈራ)ለቤተሰቦቹ የመጀመሪያ ልጅ እንደመሆኑም መጠን ለእናት እና አባቱ ብርቅዬ ከመሆኑም በላይ ለህይወታቸው መስመር ልፍቅራቸው ደግሞ ማገር እንደነበር እና ውሮ ዎሸባ ተብለው ከተዳሩ በኋላ ያገኙት የመጀመሪያ ፍሬአቸውን ማጣታቸው ልባቸውን ብቻም ሳይሆን ቅስማቸውንም መሰበሩን ከዜና እረፍቱ በኋላ የስራተ ቅብሩ በተፈጸመበት ወቅት ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ጓደኞቻቸው ቆመው ከገለጹት መካከል ነበር።በመቀጠልም እንዲህ አሉ “ዛሬ በመከራ ተገናኝተናል እንደ እኔ ወጣት እና ታዳጊ ልጅ ያላችሁ ወላጅ ቤተሰቦች ልጃችሁን አትነጠቁ መራራነቱ ይከፋባችኋል ሆኖም ላደረጋችሁት ትልቅ አስተዋጽኦ  እግዚአብሄር ብድሩን ይክፈላችሁ እኔ ምንም አቅም የለኝም ሆኖም ግን በዛሬው እለት ለዕኔ የመከራ ቀንም ቢሆንም በዚህች እለት እኔን እና የምወዳትን ባለቤቴን ንግስትን ለማጽናናት እዚህ ተገኝታችሁ ስላጽናናችሁን ከልብ እናመሰግናለን አሁንም ብድራችሁን በደስታ ይመልስልኝ በማለት አይናቸው እንደጎርፍ የሚያወርደውን እንባቸውን የጠራረጉ መናገር ቀጠሉ ግን አልቻሉም ሃሳባቸው ተቋረጠ አዳራሹም በእንባ እና ጩኸት እንደገና አስተጋባ ።አስራ ስምንተኛ አመቱን ከያዘ ብዙ ወራትን ያላስቆጠረው ታዳጊው ወጣት ሚኪያስ ተፈራ የተገደለው በመኪና አደጋ ተገጭቶ ገጭው አምልጦአል የሚል ምክንያት ከፖሊስ መኮንኖች እና መርማሪዎች ተደጋጋሚ የሆነ ምላሽ ይሰጥ እንጂ አሁንም በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ የተለያዩ የተዛቡ ሃሳቦችን ማሰራጨታቸውን ቀጥለዋል ሆኖም የምርመራው ውጤት እስካሁም አልተገለጸም ከ3 ሳምንት በላይ የሚቆየው ይሄው ምርመራ ምን ይዞ ሊመጣ እንደሚችል ማንም የሚገምተው ነገር የለም ግን ሁሉም በጉጉት ምን ይሆን ገዳዩ እውነት ፖሊሶች እንደ ተናገሩት መኪና ይሆን ከሆነስ እንዴት ጉዳቱ ለምን አልከፋበትም የተፈነገተ ወይንም የግጭት ምልክት አያሳይም የሚለው ጥርጣሬ ሁሉንም እያነጋገረ ያለ ትልቅ የወቅቱ ጉዳይ ሆኖ ያለ ሃሳብ ነው ።በአንዳንድ ግለሰቦች አመለካከት ደግሞ እንዲህ ያለው የማጭበርበር ምልክት ነው ህብረተሰቡን ለማደናገር ያደረጉት እቅድ  እንጂ ይህ የተቀነባበረ ወንጀል ነው የመኪናም ግጭት አይደለም በማለት ያሰምሩበታል ።በቺካጎ የሚገኙትንም ማህበረሰቦችም .. .. የልጃችን ህይወት እንዲህ ባለ ሁኔታ ሊቀጠፍ እንደማይችል ጠንቅቀን እናውቃለን  እንደዚያም ከሆነ ገጨው የተባለውን መኪና ይዛችሁ አቅርቡልን እኛም ፍርዱን ለእግዜር እንተው ወይንም ጉዳዩ በፍርድ ቤት ይታይ ሲሉ ይናገራሉ ሙግታቸውንም ይሞግታሉ ።ስለ ግጭቱም አስመልክቶ የተያዘ ከሌለ በወቅቱ ከጓደኞቹ ጋር እጓደኞቹ ቤት ፊልም በማየት እስከ ምሽቱ 11፡30 ድረስ በሰላም እንደነበር እና ወላጅ አባቱ መጥቼ ልውሰድህ ሲለው አይ ጓደኞቼ ያደርሱኛል ከ እነሱ ጋር መምጣት ስለምችል አትቸገር ብሎት የአንድ ሰአት ጊዜ እንዲሰጠው ፈቃዱን ጠይቆት በአንድ ሰአት ልዩነት ውስጥ ህይወቱ ጠፋ ተብሎ ከፖሊሶች ሲነገራቸው ምን ሊያስቡ ይችል ይሆን ?የጊዜያቶቹን ሁነቶች እና እንቅስቃሴዎች የተመለከተ ሁሉ ፍርዱን ወደ አንድ አቅጣጫ እንዲያተኩሩ ያደርጋሉ ።በተለይም በምርመራ ወቅት ተይዘው ወደ ነበሩት ሶስት ጓደኛሞች ላይ ያተኩራል ግን ፖሊሶች እነሱን ሃያ አራት ሰአት ባልሞላ ጊዜያት ውስጥ ከእስር ቤት እንዲለቀቁ አድርጓል ለምን ይህም ምንም ፍንጭ ያልተገኘለት አጀንዳ ነው ። አክስቱ አበባ ገብረህይወት እንዳለችው ከሆነ ቀድሞ አብረውት እቤቱ ድረስ ያደርሱት የነበሩ ልጆች ከ2ኛ ክፍል ጀምረው ጓደኛሞች ሆነው ፍቅርን ያሳለፉ የነበሩ ጓደኛሞች ዛሬ ችግር ሲደርስበት የት ነበሩ መንገድ ላይ ሲገጭስ የተገጨበትን መኪና ለምን አልገለጹም ወይንም ከገደሉት ምክንያቱን አላሳወቁም የሆነ ያደረጉት ነገር እንዳለ እና በ እነርሱ ውስጥ ብቻ የተቀበረ ሚስጥር አለ ሲወድቅ ካዩት 911 ወይንም ለወላጅ አባቱ እንዲህ ሆነ ብለው ለምን አልገለጹለትም ሌሎች ሰዎች የመጀመሪያ እርዳታ እንደሰጡት እና ከዚያም ፖሊስ መጥቶ ወደ ሆስፒታል መውሰዱን ነው የሰማሁት ይህ ከበስተጀርባው ነገር አለ ! በማለት የውስጣዊ ጥርጣሬዋን  አጋርታናለች ።

የሳምንቱ የልብ ስብራታችን አሁንም ከ እርሱው ጋር አብሮ ይጓዛል ዝም የሚል አንደበት አይኖረንም ፣አዎ ሚኪያስ የሃገር የህዝብ የቤተሰብ እንዲሁም የራሱ መኩሪያ እና ተስፋ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅ ታላቅ ተማሪ እንደነበር አጠቃላይ የቺካጎም ህዝብ እንዲሁም የትምህርት ቤቱ መምህራን ተማሪዎች እና ስተዳደር ሰራተኞች በቀብሩ ስነስርአት ወቅት ገልጸውልኛል  የመጨረሻው ስኬት ግን የጨለማው ጉዞ የህይወቱ ፍጻሜ መሆኑ ቅጭታችንን ይብስ ወደ ማንነት ጥያቄ ወስዶብናል ስለሆነም ይህንን ምላሽ እንሻለን እንላለን  !የዘሃበሻ እና የማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ዝግጅት ክፍል በቦታው ተገኝተው ያደረጉትን ጥንቅር ወደፊትም ለማቅረብ ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋሉ  .. .. .. በዚህ በሁለት ሳምንት ውስጥ ይቀርባል ተብሎ የታሰበውን ታክስኮሎጂ ወይንም የአሻራ ምርመራ ውጤት በጥንቃቄ መጠበቅ እና የመጨረሻውን ውጤት ማየት የሁላችንም ጉጉት ነው በእርግጥም  ይህንን ጉዳይ የያዘው የሸምበርግ የወንጀል ምርመራ ክፍል ለመገናኛ ብዙሃን ምንም ነገር ለመግለጽ እንደማይፈልግ በቺካጎ ሰን ታይምስ ላይ የቀረበው ሪፖርት ሲያሳይ ከዚህ ጋር በተያያዘ ልጁ አስፓልት ላይ ተኝቶ ነው የተገጨው ብለው የሰጡትም መረጃ መገናኛ ብዙሃኖችን ሊያሳምን አለመቻሉ ይባሱኑ ጥርጣሬ ውስጥ እንዲከታቸው አድርጓል  ስለዚህ ወላጅ አባቱ ዶ/ር ተፈራ እንደገለጹት እኛም ህብረታችንን ወደ አንድ አቅጣጫ መልሰን ጉዳዩን ትኩረት እንዲሰጥበት አብረን እጅ ለ እጅ ተያይዘን እንጓዝ እላለሁ “ፍርድ ነጻ ፍትህ እያልን ጩኸታችንን እናሰማ ዘንድ “ለዚህም ደግሞ ከዚህ ቀደም በሚኒያፖሊስ በአንዲት ወጣት ላይ የደረሰውን የመኪና አደጋ አስመልክቶ ወላጅ አባቷ ያቀረቡትን ሪፖርት እንዳስታውስ እና የተደረገውን ካምፒየን ምን ይመስል እንደነበር ረድቶኛል ያም በአካባቢው የነበሩትን ህብረተብ አንድነት እና ህብረት አጉልቶ ያሳየ ኢትዮጵያዊነታችን የተንጸባረቀበት ስለሆነ ዛሬም በመላው ሰሜን አሜሪካ የሚገኙትን ኢትዮጵያኖች ለዚህ ጥሪ ሁላችሁም ምላሻችሁን ትሰጠ ዘንድ ከመተማመን ጋር ነው ። ለዚህም የመጨረሻውን የምርመራ ውጤት ማወቅ አስፈላጊ ነውና ሁላችንም መጠበቅ መልካም ነው ። ማለዳታይምስ

በዚህ አጋጣሚ ማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ዝግጅት ለመላው ቤተሰቦቹ እንዲሁም ለቅርብ ጓደኞቹም ጭምር የዚህ ልጅ ህይወት ሃዘኑ ያንገበግበናል ብለው ልባቸው በሃዘን ለተሰበረ ሁሉ መጽናናትን እየተመኘን …ለታዳጊ ሚኪያስም የዚህን አለም ተሰናብቶ መሄዱ የኛ ፈቃድ ባይሆንም አምላክ በቀኝ እጁ እንዲያኖረው እና የሰላም እረፍት እንዲኖረው ምኞታችንን እንገልጻለን ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on December 17, 2012
  • By:
  • Last Modified: December 17, 2012 @ 6:14 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar