www.maledatimes.com ሥጋን ከሚግጡ መቅኒን ወደሚመጡ ዳግማዊ ጉዱ ካሣ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሥጋን ከሚግጡ መቅኒን ወደሚመጡ ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

By   /   December 17, 2012  /   Comments Off on ሥጋን ከሚግጡ መቅኒን ወደሚመጡ ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

    Print       Email
0 0
Read Time:103 Minute, 33 Second

                 ሥጋን ከሚግጡ መቅኒን ወደሚመጡ

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ማሳሰቢያ፡- ማንም ይሁን ማን የደም ግፊት ካለበት፣ በቀላሉ የሚናደድ ወይ የሚበሳጭ ከሆነ፣ የኢትዮጵያዊነት ስሜቱ የሚያይልበትና ዘወትር የሚያስጨንቀው ከሆነ… ይህን ጽሑፍ በጭራሽ ባያነብ ይመረጣል፡፡ ይህ መጣጥፍ በተቻለ መጠን ከተሞክሮና ከሕዝባዊ ብሶቶች በመነሣት በስፋት የሚስተዋሉ እውነታዎችን እንዳለ የሚያቀርብ እንጂ በተለመደው የይሉኝታና የመለሳለስ ባህል ተዋዝቶ አንድን ወገን ለማስደሰት ወይ ሌላን ወገን ለማስከፋት ያልታለመበት በመሆኑ አንባቢ ከየትኛውም የስሜት ጫፍ በራቀ ሁኔታ እንዲያነብብ ይመከራል፡፡ መልካም ንባብ!

 

… “በእግራችሁ ጫማ አድርጉ እንጂ ሁለት እጀ ጠባብ እንኳ አትልበሱ፡፡ በማናቸውም ሥፍራ ወደ ሰው ቤት ስትገቡ ያንን ሥፍራ እስክትለቁ ድረስ በዚያው ቆዩ፤ ሰዎች በማይቀበሏችሁና በማይሰሟችሁ ቦታ ሁሉ የእግራችሁን አቧራ አራግፉና ከዚያ ወጥታችሁ ሂዱ፤ ይህም ለእነርሱ የማስጠንቀቂያ ምሥክር ይሆንባቸዋል፡፡”

ማር. 6፣ 9 – 12

 

‹ንገረኝ ካልሽማ ተቀይሜሻለሁ፣ ግን አንቺን ትቼ መኖር እፈራለሁ…› የሚለው የቴዲ አፍሮ ዘፈን ትዝ አለኝ – የኢሣትን የዛሬ ልዩ ዝግጅት ስመለከት፡፡ እርግጥ ነው – ይህ መሰሉ ዝግጅት አዲስ አይደለም፡፡ እኔም በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ብዙ ጊዜ  ተመላልሻለሁ፡፡ ግን የበደል ነገር በተወሳ ቁጥር ስሜትን እንደአዲስ ስለሚቀሰቅስ ሁልጊዜ ያው አዲስ ነው፡፡ ታማኝ በየነ በዛሬው ዕለት ስለወያኔዎች ኮኬነት ከሲሳይ አጌና ጋር ባደረገው መሳጭ ቃለ ምልልስ ያቀረበው ዝግጅት አንጎልን ያቀውሳል፡፡ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ ሲያስቡት በርግጥም ከማሳበድ ያልፋል – ከዚያ በላይ ካለ፡፡ ለነገሩ ከወያኔ በቀር በዚህ ጊዜ ያላበደ ኢትዮጵያዊ የት ሊገኝ?

 

ሀተታችንን በአንዲት ቀልድ አዘል ቁም ነገር እንጀምር፡፡ አንድ የአንድ መሥሪያ ቤት ሽማግሌ ዘበኛ ወረፋቸውን ጠብቀው ደሞዛቸውን ቆጥረው ሲረከቡ አሥር ብር እላፊ ይወስዱና እንደወትሮው 300 ብር ሣይሆን 310 ብር ይዘው ይሄዳሉ፡፡ ገንዘብ ከፋይዋ ከፍላ ስትጨርስ ወጪን ከቀሪ በምታወራርድ ጊዜ  አሥር ብር መጉደሉን ትረዳለች፡፡ በስህተት ለማን እንደከፈለችም ትውስ ይላትና የማስመለሻ ዘዴዋን ወዲያውኑ ታቀነባብራለች፡፡

በቀጣዩ ወር ደመወዝ ስትከፍል ያቺን አሥር ብር በስህተት የከፈለቻቸውን ዘበኛ ወርኃዊ መሃያቸውን ሊወስዱ ተሰልፈው ታያቸዋለች፡፡ ከዚያም ተራቸው ደርሶ ስትከፍላቸው አሥሩን ብር ቀንሳ 290 ብር ትሰጣቸዋለች፡፡ እሳቸውም ከፊቷ ላይ ሲቆጥሩት አሥር ብር መጉደሉን ይረዱና ‹ ምነው ልጄ! ለምን አሥር ብር ታጎድይብኛለሽ? በቅጡ ቆጥረሽ አትሰጪም እንዴ?› ብለው ይጠይቋታል፡፡ እሷም ‹እንዴ አባባ፣ ባለፈው ወር … ምነው እንኳን … ደመወዝዎን ስከፍልዎት … አሥር ብር እላፊ በከፈልኩዎት ጊዜ ለምን አልመለሱልኝም?› ብላ በሰው ፊት ታሳፍራቸዋለች፡፡ እንደወያኔ የሌባ ዐይነ ደረቅ የሆኑት ሽማግሌ የዋዛ አልነበሩምና ‹እንዴ፣ ምን ማለትሽ ነው! ያኔ የመጀመሪያ ስህተት ነው ብዬ በምሕረት አለፍኩሽ፡፡ አሁን ግን ለሁለተኛ ጊዜ ስህተት ስትሠሪ ልታገስሽ አልቻልኩም፡፡› ብለው ሕዝበ ተሰላፊ ደሞዝተኛን ጭምር በሣቅ ገደሉት፡፡ አዎ፣ ስህተትን በስህተት ማረም የወያኔዎች የባሕርይ ገንዘብ ነውና ይቺን ጨዋታ ከወያኔዎች ተፈጥሮ ጋር በማስተሳሰር ትንሽ ቆዝሙባት – ፈገግ ካሰኘቻችሁም እሰዬው፡፡

ወያኔ ጫካ የገባው የአፄውንና የደርጉን ስህተት በመቃወም ነበር ይባላል – በይባላል ደረጃ፡፡ እንጂ ዋናው ዓላማቸውማ ትግራይን ገንጥለው የራሳቸውን ነጻ ግዛት ለመመሥረት ነበርአሉ፡፡ ስሙ እኮ ‹ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ› ነው፡፡ በለስ ሲቀናውና የውጪዎቹ ደጋፊዎቹ ሃይ ብለው የሀገር ጥፋት አጀንዳ ሲያሲዙት ግን ሃሳቡን ቀይሮ ለታሪካዊ ጠላቶቻችን ምቹ ሆኖ ተገኘና እስካሁን የሆነውና አሁን እየሆነ ያለው ሁሉ ሆነ፡፡

አሁንና ከአሁን በኋላ መወሻሸት የለም፡፡ እቅጭ እቅጩን ነው የምንነጋገረው፡፡ እናም ወያኔ ጫካ የገባው – በገርነት አስተሳሰብ ወስደንለት – ስህተትን ለማረም ከሆነ ወያኔ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ ዓለምን የሚያስቀና ማኅበረሰብኣዊ ሥርዓት ዘርግቶ በትንቢቱ መሠረት ስደት ከኢትዮጵያ ሳይሆን ወደኢትዮጵያ ሊሆን በተገባ ነበር፡፡ በተገላቢጦሹ ታዲያ ስህተትን በስህተት መለሰና ወያኔ ሆዬ ቀጥሎና እስካሁንም የም(ን)ለውን እንድ(ን)ል ምክንያት ሊሆን በቃ፡፡ በበቀል ተረግዞ በበቀል የተወለደው ወያኔ የነሚካኤል ስሑልን መሰል የአያት ቅድመ አያቶቹን ጭንጋፍ የክህደት ታሪክ እውን ካደረገ ይሄውና 22 ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት ብቻ ቀርቶታል፡፡ በየት እንደሚመጣ አይታወቅም እንጂ ፈጣሪ ቁናውን ሠፍቶ የጨረሰ ይመስለኛል፡፡ ከፈጣሪ ቢሮ ተፈርሞ የሚወጣን ደብዳቤ የሚያስፈጽም አካል ጊዜው ሲደርስ ራሱ አምላክ ይገልጠዋል፡፡ የሚወጣ እንጀራ ደግሞ ከምጣዱ ያስታውቃልና ዕድሜ ለሰጠን ጊዜው ደርሶ ስናየው የመጪውን ምንነት የምንለየው ይሆናል፡፡

በነገራችን ላይ በዚያን ሰሞን በፈረንጅ ቋንቋ አወለካክፌ የጻፍኩትን ደብዳቤ ለብዙ ድረገፆች ብመይል ከሁለቱ በስተቀር በሌሎቹ የውኃ ይሁን የአልኮል ሽታ ሆኖ ቀረ፡፡ በሀገራችን የጤፋችንን ያህል በተወደደ እንግሊዝኛ እንደምንም ብዬ ዕርሜን ብሞነጫጭር በተለያዬ ምክንያት ተቃዋሚ ተብዬዎቹ ድረገፆች ሸለል አሉኝ፡፡ ‹ቂጥኛም ከውርዴ› መጫወቱ ዱሮም የነበረ በመሆኑ ከተለከፉበት በውል ያልገባኝ ደዌ እስኪፈወሱ በትግስትና በጸሎት መጠባበቅ አለብኝ እንጂ ልከፋባቸው አልፈልግም፡፡ ይሁንና ‹ንገረን ካሉማ … › በሚለው የቴዲ ግልብጥ ዜማ በድርበቡ ልንገራቸው፡፡ እንኳንስ እነሱ ጎብላላዎቹ ሐምሌና ነሐሴም ነጉደዋል፡፡

በቅድሚያ ግን ‹ethiolion.com›ንና ‹zehabesha.com›ን ‘Hit the iron when it is hot’ በሚል ርዕስ የሰደድኩትን ጽሑፍ ማንንም ሳይፈሩ ወይ ሳያፍሩ በራሳቸው ነጻ ምርጫ በማስተናገዳቸው በእጅጉ እንዳመሰግን ይፈቀድልኝ፡፡ የኢትዮጵያ አምላክ ወሮታቸውን ይክፈላቸው፤ ከክፉ ይጠብቃቸው፤ ሥራቸውንም ይባርክልኝ፡፡ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ ሐዋርያ መሆን ማለት እንዲህ ነው – ከልቤ ነው፡፡ ‹ያልፈሱበት ቂጥ አያፍሩበትም› እንዲሉ እነዚህ መድረኮች ቢያንስ ከኔዋ መልእክት አንጻር የሚያሳማቸው ነጥብ አላገኘሁባቸውም – ያዝልቅላቸው፡፡ የሌላውን ግን ሆድ ይፍጀው – ተከድኖም ይብሰል፡፡ እንዴ – በሌባ ጣት የአሳደህ በለው ትየባ ሙሉ ቀን ወይም ሙሉ ሌሊት የተከተበን ጽሑፍ ቅርጫት ውስጥ መክተት ምን ማለት ነው – ነውርም አይደል ወገኖቼ? “ይሄኔ የነእገሌ ቢሆን ኖሮ ብስናትም ቢሆን ከነምናምንቴው ያስተናግዱ ነበር” ልል አማረኝና ዳግመኛ መገናኘት የማይቀር ከሆነ ሆድ እንዳንባባስ ብዬ ተውኩት፡፡ በያም ላይ “ይሄ ደግሞ የማነው ‹ኮምፕሌክሳም›” እንዳልባልም ፈራሁ፡፡ ይህ ድርጊታቸው ግና አያቀባብርም ብቻም ሳይሆን ሌላም ባስባለ፡፡

በመሠረቱ እሥረኛ እሥረኛን ነጻ ሊያወጣ አይችልም፡፡ እሥረኝነት ደግሞ መገለጫው ብዙ ነው፡፡ ጥቅም፣ ዘረኝነት፣ አድርባይነት፣ እወደድ ባይነት፣ ወዳጅነትና ጓደኝነት፣ ይሉኝታ፣ ወዘተ. ኅሊናን ያሳውራሉ፤ ወኔንም ያኮላሻሉ፡፡ የተባለው ነገር እውነት መሆኑ እየታወቀ እንኳን በነዚህ ልቦናን አሳዋሪ ምክንያቶች የተነሣ ሰዎች ከእውነት ይርቃሉ፡፡ የእውነትን ጥሩር የታጠቀ ግን በሚያደርገው ነገር ሁሉ ስለማያፍር እውነትን እንዳመጣጧ ያስተናግዳል፤ መጋፈጥ ካለበትም ይጋፈጣል፡፡ በመጨረሻም እውነት ራሷ ነጻ ታወጣዋለች፡፡

[off the record] ወገኖቼ! አንዲት ሴት ልጅ ወንድ ልጋብዝሽ ቢላት መታለል የለባትም – በራስ የምትተማመን ከሆነና ሌላ ጉዳይ(ዐመል) ከሌለባት የማንንም ግብዣ በቀላሉና ሳታምንበት መቀበል አይኖርባትም፡፡ ልጋብዝሽ ሲላት ለምን ብላ መጠየቅ አለባት፡፡ ለተራ ወዳጅነት ከሆነም እርሷም እንደወንዱ ሁሉ ልትጋብዝ ይገባታል፡፡ ያኔ አፍ ይኖራታል – የምትጠየቀውን እምቢም እሸም ለማለት እኩል ነጻነት ታገኛለች፤ የጥቅምና የይሉኝታ እሥረኛ ከሆነች ግን ለብዙ አደጋ ትጋለጣለች፡፡ ማን ጋብዞ ማን ማንን እምቢ ብሎ ይሄዳል? “ኧረ! ይህን ሁሉ ገንዘብ ያወጣሁት እህቴ ነሽ ወይንስ አክስቴ?” ብትባል ማጣፊያው ያጥራትና ወደሚቀርባት አሊቤርጎ መጓዝ ነው የሚኖራት ብቸኛ ምርጫ፡፡ በጥቅም የታሠረ/የታወረ ሰው መፈቻ የለውም፤ ግዝትም እንኳን አይፈታውም፡፡ ያጎበድዳል፤ ያዘጠዝጣል፤ ያሸረግዳል፡፡ ተሳደብ ቢሉት ይሳደባል፤ አሽሟጥ ቢሉት ያሽሟጥጣል፡፡ በቃ፣ ብሃፂሩ – ማለትም ባጭሩ –  ብኩርናውን በምሥር እንደሸጠው እንደኤሣው ይሆንና የኅሊና ነጻነቱን – የራሱን ማንነትና እምነት ለሌሎች አሣልፎ የሸጠ ባሪያ ይሆናል፡፡ [on the record] ብዙዎቹን ነጻ ነን ባይ ድረ ገፆችን በምናቤ ስቃኛቸው ለዚህ ዓይነቱ አስቀያሚ ሂደት ሰለባ የሆኑ   ይመስሉኛል፡፡ (የከፋው ሰው ሲናገር ለካንስ ለከት የለውም እናንተዬ! ከእያንዳንዱ ዐረፍተ ነገር በኋላ ራሴን ስታዘበው እንዴት እንዴት ነው እምናገረው እባካችሁን?)

ይገርማችኋል፡፡ አንዳንድ ድረ ገፆች ትግሬን ሲነኩባቸው ነብር ይሆናሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ አማራን ሲነኩባቸው አንበሣ ይሆናሉ፡፡ አንዳንዶች ኦሮሞን ከነኩባቸው ግሥላ ይሆናሉ፡፡ አንዳንዶች ኢሕአዲግን ከነኩባቸው ዓሣማ ይሆናሉ (ዓሣማ ሲናደድ እንዴት ይሆን ግን?)፡፡ አንዳንዶች ታዋቂ ግለሰቦቻቸውን ሲነኩባቸው የቆሰለ አውሬ ይሆናሉ፡፡ አንዳንዶች ግንቦት ሰባትን ወይም ጥምረትን ከነኩባቸው ንብ ይሆናሉ፡፡ አንዳንዶች መድረክን ከነኩባቸው አቦሸማኔን ይሆናሉ፡፡ አንዳንዶች ኢሕአፓን ከነኩባቸው ተርብ ይሆናሉ፡፡ አንዳንዶች ኦነግን ከነኩባቸው አነር ይሆናሉ፡፡ አንዳንዶች አርበኞች ግንባርን በጨረፍታም ቢሆን ነኻ ካደረጉባቸው ኩርፊያቸው አይጣል ነው፡፡ አንዳንዶች ሻዕቢያን ሲነኩባቸው ይገሰላሉ፡፡… አንዳንዶች ያን ወይ ይህን ሃይማኖት ሲነኩባቸው ጭክ እንዳለች ዶሮ ይሆናሉ፡፡ እጅህን አጣጥፈህ ካልተቀመጥህ ጣጣው ብዙ  ነው፡፡ ይታያችሁ እንግዲህ – የትኛው ጸሐፊ የትኛውን አካል ሳይነካ ሊጽፍ ይችላል? በቀጥታም ይሁን በተዛዋሪ ይህን ወይ ያን ሳይነኩ እንዴት መጻፍስ ይቻላል? ስንቱ ተፈርቶ፣ ለስንቱስ አሸርግዶና ተሽቆጥቁጦ ይዘለቃል? ምሥጋና ከጻፍክ ግን በተለይ የተመስጋኙ ወገን አቀንቃኝ ባላደራ የሆነ ሚዲያ መሪ ዜናው አድርጎ ቦግ ያደርግልሃል፡፡ ይህም ከንቱነት ይመስለኛል፡፡ አጥብቆ በኩራዝና በሻማ ብርሃን መፈለግስ ደካማ ጎንህን የሚነግርህን ሰው ነው፡፡ አመስጋኝ አማሳኝ ነው እሚባል ከነተረቱ ወዳጄ ልቤ፡፡ ምሥጋና ያነሆልላል፤ ከዓላማም የማናጠብ ጠባይ አለው፡፡ ሰይጣንም የተዋረደው ራሱን ከመጠን በላይ በመውደዱና በራስ ፍቅር በመጠመዱ ነው፡፡ የምሥጋና ምርኮኛ የሚሆን ሰው ወይም ድርጅትም ቢሆን በራስ ፍቅር የተተበተበ ከንቱና ግዑዝ ነገር ነው፡፡ እንደውነቱ ከሆነ ጠንካራ ጎን ተናገሩት አልተናገሩት ምንም አይፈይድም፡፡ እንደ አካሄድ ታዲያ መታበይና በጥቂት ነገር መኩራራት የባሕርይ ዐመላችን እንደሆነ መዝለቁ ያሳስባል፤  ያሳዝናልም፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ በኢትዮጵያ በሰማንያዎች የሚቆጠሩ ዘውጎችና በመቶዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካም ይሁኑ የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች እንደዚሁም በመቶዎች የሚቆጠሩ የሃይማኖት ባለ አክሲዮን ኩባንያዎች አሉ፡፡ ሁሉም ጤነኞች ወይም ሁሉም በሽተኞች ናቸው ማለትም አይቻልም፡፡ ሰው የታየውን ሲጽፍ ከማፈን ይልቅ ታዲያን የሚመለከተው አካል ተመልክቶ ምላሽ እንዲሰጥ ቢደረግ ይበልጥ ጠቃሚ በሆነ ነበር እንጂ በየት ዞረሽ ቀደምሽኝ ዓይነት ገና ከአሁኑ በእከክልኝ ልከክልህ አንዱ የአንዱን ገመና ለመሸፋፈን መሞከሩ ከጅልነት ያለፈ ቡልሃነት ነው – የሥራ ቦታን ያለማወቅ ድንቁርናም ይመስለኛል፡፡ ‹ነጻ አስተያየትን እናስተናግዳለን› እያሉ ሕዝብን ‹የሚፎግሩ› የእነዚህን መሰል ድረ ገፆች አዘጋጆች ቆሽታቸው እንዲህ ጠባብ ከሆነች ፍየል ጠባቂ ቢሆኑ ይሻላቸዋል የሚል አስተያየት አለኝ፡፡ እኔማ ‹ድንቄም ሃሳብን በነጻነት ማስተናገድ!› እያልኩ ማሽሟጠጥ ከያዝኩ ቆይቻለሁ – እንደሠንጋተራና ካዛንቺሶቹ የቡና ቤት እህቶቼ ከንፈሬን ለሽርደዳ በሚያመች መልኩ ሞጥሞጥ በማድረግ፡፡ ሲጥማቸው ይለጥፋሉ – ሳይጥማቸው በሃያ ቁጥር ምስማር ይከረችሙሃል -  ያኔ በአንዲት ቃል ወይም በአንዲት ዐረፍተ ነገር እንዳስከፋሃቸው ይገባሃል፤ ያቺን ጦሰኛ ስንጣሪ ሃሳብ ወይም ሐረግ አውጥቶ ቀሪውን ለባለአድራሻው ማድረስም አንድ ነገር ነበር – ግን ኢትዮጵያዊው የትምክህትና የትዕቢት አባዜ የትም ብንሆን መች ይለቀንና፡፡ እንደእውነቱ ግን የሚላክ ነገር መጣም ያለበት ለነሱ ነው ወይንስ ለአንባቢ? እኚህን መሰል ወገኖች አይጋፎረምንና የአቡነ አረጋዊ – ማነው – የአማረ አረጋዊን ሪፖርተር ከኢቲቪ ቀጥሎ በሁለተኛነት በማስቀመጥ ‹ወያኔ ቁጥር ሦስት› ቢባሉ ያንሳቸው ይሆን? ሆ! ‹በጊዜ የጮኸ ጅብ አያሳድረኝም› አሉ! ከአሁኑ የምን ሰውን ለማፈን መሞከር ነው፡፡ ‹ውሻና ባለጌ በቤቱ ይኮራል› እሚባለው ለካንስ ትክክል ነው፡፡ ኤዲያልኝ! ይሄ ኢትዮጵያዊነት ስንቱን ያሳያል ‘ባካችሁን…

ይህ ዓይነቱ ነገር ‹ቂጥ ከፍቶ ክንንብ› ዓይነት ነው እሚመስለኝ፡፡ ሀገር የሚያውቀውን የወያኔን ገመና ከማራገብ ይልቅ የራስን ማንነት በመፈተሸ ከወዲሁ ራስን ማረቅ ይገባል እንጂ በቃላት አጠቃቀም ዙሪያ ዘርፍ እያወጡ በፀጉር ስንጠቃ በመፈላሰፍ የገዛ ወገንን በደጅ ማባረር ሞራላዊም ሆነ ሀገራዊ ርባና የለውም፡፡ ሌባን ሌባ ቢተካው ለውጡ የት ላይ ነው? የወያኔን ቱሪናፋ ቲቪና ሬዲዮ በተቃዋሚ ቱሪናፋ የሚዲያ ውጤት ለመተካት የተያዘ ሩጫ ካለ á‹« ትልቅ ስህተት ነውና ከአሁኑ ቆም ተብሎ ቢታሰብበት የተገባ ነው፡፡ ለነገሩ የኢትዮጵያ መሬት በ144 ጠበል ካልተረጨ የሚያበቅለው ሁላ አጋሰስና ደንቆሮ፣ መጭና እንክርዳድ እየሆነ ተቸግረናልና ከአሁኑ ይልቅ የወደፊቱ ቢያስፈራን ሥጋቱ እንደሥጋት ትክክል ነው – ‹የአበራሽን ጠባሳ ያዬ በእሳት አይጫወትም› ወንድሜ፡፡ ቢሆንም ተስፋችን ይበልጡን በፈጣሪ ላይ ነውና አንድዬ እንደሚያስተካክለው ትልቅ ተስፋ አለኝ – ከተደጋጋሚ ቅጣትም እንዲሠውረን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡

ወደዋናው ጉዳይ ልመለስ፡፡ ይሉኝታ ከትግራይ ተጠራርጋ ከወጣች ብዙ ዘመን አለፈ ብዬ ለማመን መገደዴን ስገልጥላችሁ ልደብቀው በማይቻለኝ ሀፍረት እየተሸማቀቅሁ ነው፡፡ አዝናለሁ – ግን መናገር   ደግሞ አለብኝ፡፡ ይህን እንድልም ነባራዊ ሁኔታዎች ያስገድዱኛል፡፡ ከአንድ ትልቅ የሚባል ማኅበረሰብ ውስጥ ጥቂት የማይባል ወገን በእልህና በቁጪት ተነሳስቶ ቀሪውን ሀገር ሲወርና በምርኮ á‹­á‹ž ነጻነትን በመደፍጠጥ ሀብትንና ንብረትን ሙሉ በሙሉ ሲቆጣጠር ይሉኝታቢስነት እንጂ ሌላ ሊባል አይችልም፡፡ እናም በአሁኑ አያያዝ ወያኔና የበቀለባት የትግራይ መሬት በጥቅሉ ይሉኝታና ሀፍረት የሚባሉ ቃላት በመዝገበ ቃላቸው (dictionary) ውስጥ  ስለመኖራቸው መጠራጠር ጀምሬያለሁ ብዬ በድፍረት ስናገር በጠንካራ ኢትዮጵያዊነት የምትታወቁ የዚያ ክልል ጥቂት የማትባሉ ባለሦስት ዐይን ዜጎች ከእውነታውና ከብሶቴ አንጻር ብዙም እንደማትቀየሙኝ በመገመት ነው፡፡ አባባሌን የምትጠራጠሩ ካላችሁ አዲስ አበባንና መላዋን ኢትዮጵያን በአሁኑ ወቅት ጎብኙና የምለውን በተግባር አረጋግጡ፡፡ሀብትና ንብረት እንዴት እንደሚያፈሩና በአንድ ቀን አዳር እንዴት ሚሊዮነር እንደሚሆኑ ተውትና ለአነጋገራቸው እንኳን ለከት እያጡ የመጡ ዜጎች ቁጥር ቀላል እንዳልሆነ ትረዳላችሁ፤ ፍርድ ደግሞ ለራስ ነው፡፡ አንዳንዶቹ የዋሃን ትግሬዎች በዘራቸው ማንነት እንዴት እንደሚኮፈሱ እኮ ብታዩ እናንተም ታፍሩላቸዋላችሁ፤ ታዝኑላቸዋላችሁም፡፡ ‹ጥንት በደጉ ዘመን የማውቀው ጓደኛየ እንዲህ ነበር እንዴ?› ብለህ እስክትጨነቅም ድረስ ታሪክን ወደኋላ ዞረህ እንድትፈትሽ ትገደዳለህ፡፡ (አንዳንዶቹ) ማተብ የሚባል ነገር ያላቸውም አይመስሉም፡፡ አማራነትም ሆነ ትግሬነት በምርጫ ሳይሆን በተፈጥሮ ግዴታ እንደሚገኝ ተዘንግቶ አማራን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት የተያዘው ወያኔያዊ ዘመቻ ሊበርድ ያለመቻሉ ምሥጢርም ክፉኛ ያስጨንቃል፡፡

መለስ ዜናዊ አማራን አጥፍቶ ሳይጨርስ ባጭሩ ተቀጨ፡፡ እናውቃለን፡- ኤድስ ያለባቸው ሰዎች ከትግራይ እየተለቀሙ ወዳማራው ክልል እንዲበተኑና ‹ነፍጠኛ›ን እየበከሉ እንዲጨርሱ ይደረግ እንደነበር እናውቃለን፤ ለዚያም ነው መለስ በልቅ አንደበቱ ‹ሁለት ሚሊዮን አማራ በኤድስ አልቋል› ሲል በኩራት የተናገረው፡፡ በአማራው አካባቢ ዘር አምካኝ ንጥረ ነገር በመድኃኒት/በክትባት/ ስም ይሰጥ እንደነበርም  ሰምተናል፡፡ በትግራይ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንዳይገባ እየተደረገ በዚያች ክልል ሕዝብ እንዲራባ ሲደረግ በአማራው አካባቢ የሕዝብ ቅነሣ ፕሮግራም ተዘርግቶ ጦርነቶችንና የጎሣ ግጭቶችን ጨምሮ በተለያዩ ዘዴዎች አማሮች እንዲያልቁ መደረጉን፣ ያም ተግባር ወያኔ እስካለ ድረስ በቀጣይነት የሚከናወን መሆኑን እናውቃለን – ኑሯችን በሬ ካራጁ ዓይነት መሆኑን አንዘነጋውም፡፡ ሌላው ቀርቶ በኢትዮጵያዊነታቸው ሊደራደሩ ያልፈለጉ ወጣትና ሽማግሌ ቀደምት የትግራይ ተወላጆች በወባ መከላከያ ክሎሮኪን ስም በሚሰጣቸው የመርዝ ክኒን እንዲያልቁ መደረጉን እናውቃለን፡፡ አማራንና በየትኛውም የማኅበረሰብ ክፍል የሚገለጽ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ያልተነደፈ ሥልት አለመኖሩን ጠንቅቀን እናውቃለን – ለርሱው ለአንድዬ ሰጥተን ቁጭ ብለናል እንጂ፡፡ ምክንያቱም በዘረኝነት ልክፍት አልተመረዝንምና እሾን በእሾህ ለመንቀል የተዘጋጀን የአማራ ተወላጆች ልንኖር አልቻልንም፤ ከአሁን በኋላም አንኖርም(ለምሳሌ የሠሩልኝን ባንዴራ እኔ አላውቀውም – ላውቀውም አልፈልግም፤ ዳቦ እንጂ ባንዴራ መች ቸገረኝና ዱሮውንስ? – ለወያኔ ዕድሜ መርዘም ዋናው ምክንያትም አማራው ሊጠቀምበት በሚቀፍፈው የአማራነት ማንነቱ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነቱ ብቻ ፀንቶ መክፈል የሚገባውን መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀቱ ነው – አለበለዚያማ እነስንዴውና እነአስማረ እነአሥራትም ቢሞቱ እነሱን የሚተካ ጀግና ይጠፋ ነበርን? ጀግንነት ግን በተኩስ ብቻ መሆን አልነበረበትም! የጦር መሣሪያ የድንጋዮች ጡንቻ ነው፤ ዕውቀትና ጥበብ ግን የሰዎች ሀብት ነው…)፡፡

“ጉድጓድ ለሰው አትቆፍር፤ ከቆፈርክም አታርቀው፤ ቀድሞ እሚገባበትን አታውቀውምና፡፡” ይባላል፡፡ መለስ በቆፈረው ገባበት፡፡ ሃሌ ሉያ፡፡ ሥዩም መስፍንና á‹« ማይም ጄኔራል ተብዬም በቅርቡ ይገቡበታል፡፡ በቁማቸው አሣራቸውን እያዩ እንደሆነ ከተገነዘብን ቆይተናል፡፡ ባስለከፉን ተለከፉ – በቆፈሩት ገቡ ወይም ሊገቡ ዳር ዳር እያሉ ነው፡፡ የዘሩትን ማጨድ ያለ ነው፡፡ በዚህ ማንም አይጠቀምም፤ ብንስማማ ግን ሁላችን እንጠቀም በዓለምም ደረጃ በመልካ ጎናችን እንታወቅ ነበር፡፡ በምቀኝነትና በጥላቻ ስለተሞላን ግን የኋሊት ቀረን፡፡

አንድ ሰው ወይም አንድ ማኅበረሰብ ከእንስሳነት ደረጃ ወጥቶ እውነተኛ ሰውነትን ሊቀዳጅ የሚያስችሉት መለኪያዎች አሉ፡፡ ከነዚህም መካከል ዋናው እንደውሻና ድመት በዝርያው እየተፈላለገ ለጥፋትና ውድመት መሠማራት ሳይሆን አማራ ትግሬ ወይም ነጭና ጥቁር ሳይባባል በሰውነት ብቻ እየተጠራራ ለመልካም ነገር መሠለፍ መቻሉ ነው፡፡ ደምና አጥንት እያነፈነፈ የሚቧደንና ካለዘሩ የማይቀላቀል እንስሳ ብቻ ነው – ሊያውም በአሁኑ ዘመን ዐይጥና ድመትና ውሻና ዝንጀሮ ሳይቀሩ እየተፋቀሩ በኅብረት መኖር እንዲችሉ ሥልጡናኑ ሰዎች ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠሩላቸው እንደሆነ በአስደናቂ ታሪኮች መዝገብ እየተረዳን ነው፡፡ ጅቦች፣ቀበሮዎች፣ ዝንጀሮዎች፣ ጥንብ አንሳዎች… በዝርያቸው አማካኝነት እየተፈላለጉ ለአደን ቢሠማሩና የሚያገኙትን ግዳይ ቢቀራመቱ እንስሳት ናቸውና የተለመደ ነው፤ አንፈርድባቸውምም፡፡ ሰው ግን ሰው በመሆኑ ወደነዚህ እንስሳት የንቃተ ኅሊና ደረጃ በመውረድ ከአንድ ክፍለ ሀገር ተሰባስቦ ጦርን ወደሌሎች ማዝመትና መውረር፣ በዘረኝነት ጭቅቅት ተለውሶም ሌላን ሕዝብ መቆሚያና መቀመጫ ማሳጣት አይገባውም፤ እንደዚያ ካደረገ ደግሞ ሰው ለመሆን ጥቂት ግን ወሳኝ የዕድገት ደረጃዎች ይቀሩታልና በዚህ አሣፋሪ ተግባር ውስጥ የሚገኝ ሁሉ ሰው ሊባል አይቻለውም፡፡ አንድ የሕዝብ አካል ምን ቢቸግር፣ ምን ቢደኸይ፣ ምን አማራጭ ቢያጣ በጎበዝ አለቃ ተጠራርቶ በጠራራ ፀሐይ ሌሎች ወገኖቹን በራሳቸው ‘resource’ እና በራሳቸው ሁለንተናዊ ወጪ በጦር ማንበርከክና ያለ የሌለ ሀብትና ንብረትን በግፍ መዝረፍ ከጤናማ ማኅበረሰብ የሚጠበቅ አይደለም፡፡ ስለዚህም የትግራይ ሕዝብ ራሱን የሚፈትሽበትና የተጣመመውን የሚያቃናበት የጥሞና ጊዜ እንዲኖረው በዚህ አጋጣሚ ልጠቁም እወዳለሁ፡፡ እስከዚያው ግን ከወያኔ ጋር ዘምተው  በብቃታቸው ሳይሆን በዘራቸው  ምክንያት ኢትዮጵያን እንደመዥገር እየመጠመጡ የሚገኙ ትግሬዎችን እንደሰው ላለመቁጠር አሁኑኑ ቃል ገባሁ – ይህን ዘረኛ ሥርዓት ለመፋለም ጫካ የገቡ የትግራይ ቆራጥና ዕንቁ ልጆችን አስፈላጊ ሆኖ ባገኘሁት ጊዜ ለመቀላቀልም አሁኑኑ ወሰንኩ፡፡ እናም ዳር እስከዳር እንደወገብ ቅማል ሰንጋችሁ የያዛችሁን ትግሬዎች – ምርጫ ስለሌለኝ እንጂ ይህን ስል በጣም አዝናለሁ – ሰው እስክትሆኑና ከዚህ ከባለራዕዩ ጣዖታዊ አዚማችሁ ወጥታችሁ የሰውነት ደረጃችሁን እስክታሻሽሉ ድረስ የምናወራው በእንስሳነት አጠቃላይ ምድባችን እንጂ እንደሰዎች አይሆንምና ወደውስጣችሁ በአፋጣኝ ገብታችሁ ከምታሳዩን አስነዋሪ ምግባራችሁ ሳይረፍድባችሁ ተመለሱ በማለት ወንድማዊ ምክሬን ልለግስላችሁ እወዳለሁ – ካልሰማችሁኝም የራሳችሁ ጉዳይ፡፡ እያንዳንድሽ ከጎንሽ ታገኝዋለሽ፤ አንድዬ እንደሆነ ዘንድሮ ቆርጦ ተነስቷል፤ የሚምርሽ እንዳይመስልሽ፡፡ ‹በፋሲካ የገባች ገረድ ሀሁልጊዜ ፋሲካ ይመስላታል› እንደሚባል ሁልጊዜ ጌትነት የለም ደግሞ፡፡ እኛ እንደሆን መከራ ችግሩንም፣ ሞቱንም፣ ስደቱንም፣ ማጣቱንም፣ የቁም ስቅል ወያኔያዊ ግርፋቱንም ለምደነዋልና አይሞቀን አይበርደንም፤ ይልቁናስ ይብላኝ ገንዘብ እንደጉድ ላግበሰበሳችሁ ወያኔዎች፡፡ ሕይወት የሌለው ባዶ ሕንፃና ከጉንፋን የማያስጥል የሀብት ክምችት ደግሞ ከፈጣሪ መቅሰፍት አያድንም፡፡

ቀደም ባለ አንድ ወቅት ለሥራ ጉዳይ ቡርኪናፋሶ ውስጥ ነበርኩ፡፡  በኤርትራ ክፍለ ሀገር የወጣቶች  ማኅበር ሊቀ መንበር የነበረ አንድ መለሎ ትግሬ ወጣት ሲነግረኝ ‹ ትግሬን ማመን አስቸጋሪ ነው፤ ቫይረሱ (የወያኔነት ማለቱ ነው) በእያንዳንዱ ትግሬ ደም ውስጥ አይጠፋም፡፡ ስለዚህ እነሱን መጠንቀቅ ተገቢ ነው፤ …› ያለው ሁልጊዜና በተለይ አሁን አሁን አይረሳኝም – ያን አባባሉን ሊያፈርስ የሞከረ ጓደኛ ትግሬም እስካሁን አላገኘሁም፤ ብዙ ጓደኞች አሉኝ but almost all of them are sympathetic to TPLF though at times they seem to oppose some of its devastative moves. (እንግሊዝኛ እንዴት ደስ ይላል እባክህን! ባማርኛው ላይ ሸጠሸጥኩት አይደል?) ከትግሬ አንደበት ያን የመሰለ ቃለ ሕይወት መስማት በወቅቱ እጅግ አስገርሞኝ ነበር፡፡ እንዲህ ሲባል ደግሞ ከንፍሮ ጥሬ እንደሚወጣ ሁሉ ከትግሬ መሀልም እንደጌታቸው ረዳ (የኢትዮሰማይ ድረገፅ አዘጋጅ) ዓይነት በፍጹም ኢትዮጵያዊነቱ የሚያምን ትግሬ የለም ማለት እንዳልሆነ በበኩሌ አምናለሁ፡፡ በተረፈ ግን ላለመቀያየም እየተባለ በሽፍንፍን ‹ትግሬ ሳይሆን ወያኔ ነው ሀገር እያጠፋ ያለው› በሚለው አገም ጠቀም አማርኛ የማላምን መሆኔን የምገልጸው በታላቅ ሀዘን ነው -  እውነታው እንዲያ በሆነ ዕዳውም ገብስ በሆነልን፡፡ ይልቁናስ ‹ላም እሳት ወለደች እንዳትልሰው ፈጃት፣ እንዳትተወው ልጇ ሆነባት› ወይም ‹ጣት ገማኝ ተብሎ ተቆርጦ አይጣልም› የሚባሉትን ብሂሎች ‹የዘሬን ብተው ያንዘርዝረኝ› ከሚለው መጣያ ጋር አፅንዖት ሰጥቼ ላተኩርባቸው እፈልጋለሁ፡፡ ከነገሮች አካሄድም እያስተዋልኩት ያለሁት ይሄንኑ ነው፡፡ ብዙ እንግዳ ክስተቶችን እየታዘብኩ ያለሁበት ሁኔታ ተፈጥሯል አኅዋተይ፡፡

የለየለት ፀረ ወያኔ ነው የምትለው ትግሬ የቁርጥ ቀን ሲመጣ ከወያኔዎች ጋር ሲመሣጠር ታገኘዋለህ፤ ባንድ በኩል አንተን ለመምሰል እየሞከረ በሌላ ሰበርባራ መንገድ ደግሞ ወያኔን ጠጋግኖ የትግሬውን የበላይነት እንዳስጠበቀና በእግረ መንገድም የሌሎችን የበታችነት እንዳረጋገጠ ለመኖር ሲቋምጥ ታያለህ፡፡ እስስት በለው፤ ከፈለግህም የሌሊት ወፍ ብለህ የሁለት ዓለም ሰው መሆኑን ንገረው – በራሪና አጥቢ፤ እዚህ ሲሉት እዚያ እሚገኝ መሠሪ ፍጡር፡፡ ማንን እንመን እንግዲህ?

ጉዳችን ተዘርዝሮ አያልቅም፡፡ የሀገሪቱ ምርጥ የጥቅምና የሥልጣን ቦታዎች በምርጦቹ የትግራይ ብሔር አባላት መያዛቸውን፣ ይባስ ብሎም መከላከያንና ደኅንነቱን በዋናነት ጨምሮ የብዙ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሥራ ቋንቋ ትግርኛ መሆኑን አሳምሬ አውቃለሁ፡፡ አልዋሻችሁም ፤ ለምን እዋሻለሁ? አልሸፋፍንም፤ ለምን እሸፋፍናለሁ? ያበጠ ካለ ይፈንዳ – እናገራለሁ፡፡ ከዚህ በላይ ምን እሆናለሁ? ሀገሬስ ከዚህ በላይ ምን ልትሆን ትችላለች? ሁሉም ነገር አልቆበት ሙጣጭ ላይ ለደረስንበት ዘመን እንደብዙዎች በ‹ሰውን አላስከፋም› ሰንካላ ሰበብ እውነትን ልረጋግጣት አልፈልግም፡፡ ከፈለግህ አንብበኝ ፤ ካሻህም ተወኝ፤ እውነቱ ግን ይሄውና ከዚህም በላይ ነው – እንደወረደ እናገራለሁ – ተከተለኝ፡፡

አፓርይድ ከደቡብ አፍሪካ ሲባረር የፖለቲካ ጥገኝት የተሰጠው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ ጥገኝነት ሰጪዎቹም ከትግራይ ክፍለ ሀገር የመጡት ወያኔዎች ናቸው፡፡ ይህ ኢትዮጵያ ውስጥ የገባው አፓርታይድ ከደቡብ አፍሪካው የሚለየው በታሪክ ምናልባት ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቁር በጥቁር ላይ ያወጀው ልዩና ታይቶም ሆነ ተሰምቶ የማይታወቅ አፓርይድ መሆኑ ነው፡፡ የተለመደው አፓርይድ ነጭ በጥቁር ላይ ያካሄደው የዘር መድሎ ነበር፡፡ የኛው ግን ከአፓርታይድም የከፋ የጥቁር በጥቁር – ወንድም በወንድሙ ላይ የጣለው አድልዖና መገለል ነው፡፡ ይህ ታሪክ ይቅር የማይለው የትግሬዎች በሌሎች ወገኖቻቸው ላይ መንገሥና ያም ያስከተለው ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ፣ ሥነ ልቦናዊ፣ ወታደራዊ … ሁለመናዊ ባርነት በየትኛውም የዓለም ክፍል ታይቶ አይታወቅም፡፡ በአስተሳሰብ አድማሱ ጠባብ የሆነ ሰው ካሸነፈህ ትሉ በማይተኛ እሳቱ በማያንቀላፋ ሲዖል ውስጥ እንዳለህ ቁጠረው – ምሕረት ብሎ ነገር የለም – ዕድሜ ላለፉት ሃያ አንድ ዓመታት የትግሬ አገዛዝ  እኛ ኢትዮጵያውያን ለዚህ ህያው ምሥክሮች ነን፡፡

ታማኝ የጠቃቀሳቸው እርሱም እንደጠቆመው አባይን በጭልፋ ዓይነት ነው እንጂ ውስጡ ሲታይ ሌላው ይቅርና የፀሐይ ብርሃንና የምንተነፍሰው አየርም ማግኘታችን ራሱ እንደተኣምር ሊቆጠር የሚገባው ነው፡፡ [off the record – all animals are equal, but some are more equal than the others. (Animal Farm, George Orwell.]  [on the record]ትግሬ ሥራ ለመያዝ መማር አይጠበቅበትም፤ ማወቅ አይጠበቅበትም፤ ዲግሪና ዲፕሎም መያዝ አይጠበቅበትም፡፡ ዲግሪ መያዝ ካስፈለገውም ሌላ ሰው ‹ይማርለት›ና ወይም በፎርጅድ ይሠራለትና ወይም በትዕዛዝ ከአንዱ አድርባይ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ሁሉም ነገር ተሟልቶ ይበጅለትና ወረቀቱ ይሰጠዋል – ሊያውስ እንዲያው ለወጉ እንጂ ተማርክ አልተማርክ ብሎ ማን ሲጠይቀው? የሁለተኛና የሦስተኛ ክፍል ሠርቲፊኬት ሳይኖረው  ኮሎኔልና ጄኔራል ሆኖ ቢሾም ሕግ አልባው ወያኔ የሚሣነው ነገር ስለሌለ ይቻላል፡፡ ጠርዜዋ ባላገር ባንክ ቤት ገብታ በመቶ ሺዎች ስታስገባ ወይም ስታወጣ ብታይ አንተ ምናልባት ማውጫ/ማስገቢያ ቫውቸር ላይ በመጻፍ መተባበር ይኖርብህ እንደሆነ እንጂ ከየት እንዳገኘቸው ብትጠይቅ በሽብርተኝነት ከስሳህ ቃሊቲ ልታወርድህ ትችላለች፡፡ ገንዘቡ ሁሉ በነሱው እጅ ነው ጌታየ፡፡ ሥልጣኑ ሁሉ በነሱው እጅ ነው እመቤቴ፡፡ ምን ችግር አለ? ለነርሱ የሚበቃው ትግሬነቱና ታማኝነቱ ብቻ ነው – አሁንም ያበጠ ይፈንዳ፡፡

የሀገሪቱ የመሬት ውስጥና የመሬት ላይ ሀብቶችና ጥሪቶች በሙሉ በትግሬዎች ለትግሬዎች እየታደለ እነሱ በቅንጦትና በቁንጣን ሲጨነቁ ሌላው በርሀብና በሆድ ቁርጠት እያለቀ ነው፡፡ ወርቅና የእምነ በረድ ማዕድኑ፣ እርሻውና ፋብሪካው፣ ሆቴልና ቱሪዝሙ፣ ኢምፖርትና ኤክስፖርቱ፣ የትምህርቱ ሴክተርና አግሮ-ኢንዱስትሪው – ምን አለፋህ ሁሉም በነሱ ቁጥጥር ሥር ነው – በቅልውጥ መልክ ካልሆነ በመብት ደረጃ አንተ በኢትዮጵያ ምንም ድርሻ የለህም፤ ካንተ ከ‹ሰባተኛው ዜጋ› ይልቅ ሕንዱና ፈረንጁ እንደልባቸው የሚንፈላሰሱባት ኢትዮጵያ ተፈጥራለች(ለዶር. ኢንጂኔር ቅጣው ሰላምታዬ ባለበት ይድረሰው)፤ አንተማ የቀለስካት ጎጆም በላይህ ላይ በግሬደር እየፈረሰች ወደለዬለት የበረንዳ አዳሪነት እየተሸጋገርህ አይደል ወንድምዬ? የነሱ ቀለሚኖዎች የኛን ‹ደደቢኖዎች› እየተኩ ከሞላ ጎደል ሁሉንም የመንግሥት የሥራ ሴክተሮች በትግሬ ለመተካት የተያዘው ዘመቻ ተጧጡፎ ቀጥሏል፡፡ በአንድ ሀገር የተለያዬ የትምህርት ፖሊሲ፣ የሥነ ተዋልዶ ፖሊሲ፣ የዕድገትና ልማት እስትራቴጂ፣ የበጀት አመዳደብ፣ የሥልጣን ኮታ፣የሕገ መንግሥት አንቀጽ፣ የፍትሕ ሥርዓት፣… ተቀርፆ አንዲት ብቸኛ ክልል የተለዬ ትኩረት ስታገኝ (ቢያንስ አገኘች እዬተባለ ሲነገር) ሌሎች በብርሃን ፍጥነት የኋሊት እየተሸቀነጠሩ፣ ዜጎቻቸውም በማይምነት ጥቁር አለንጋ እየተገረፉ በዲግሪ ከተመረቁም በኋላ አንዳንዶቹ ትንሽና ትልቁን የ”‹A,B,C,D” ቅርጽ መለየት ወደማይችሉበት ደረጃ ደርሰውልሃል ወንድሜ ኢትዮጵያዊው! ምን ትላለህ – ኢንሳንና መከላከያን በመሳሰሉ የፀጥታና የ‹ሀገር› መከላከያ ተቋማት ውስጥ ሌላው ወገን በገዛ ሀገሩ እንደመጻተኛና እንደባዕድ ስለሚቆጠር አንድም የምሥጢር ቦታ በኃላፊነት እንዳይዝ ብቻ ሳይሆን በሥፍራው ዝር እንዳይል በጥብቅ የሚከለከልባቸው መሥሪያ ቤቶች ሞልተውልሃል ወንድማለም! የአደባባይ መሥጢሩን ነው እዚህ እንደአዲስ እየነገርኩህ ያለሁት፡፡ ባለህበት በርታልኝ የኔ ውድና ዕንቁ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ወገኔ! ባለሽበት በርቺልኝ የኔ ከርታታ ኢትዮጵያዊት ስደተኛ – ሁሉም ያልፋል፡፡(ዕንባዬ የዚያችን የዐረብ እመቤትሽን ቁጣና የፎቅ መወርወር አያስቀሩልሽም እንጂ እዚች ቦታ ላይ ስደርስ ስቅስቅ ብዬ አልቅሼልሻለሁ – ለኔና ለቤተሰቤም ጭምር፡፡ ምን እናድርግ የቤታችን የሲዖል ትሎች ዕረፍት ነሱን ፤ እግዚአብሔር ይይላቸው!!! )

መሬቱ ሁሉ ተሸጦ ያለቀው በትግሬ ካድሬና ባለሥልጣን ነው፡፡ ብሩን ከየት እንደሚያመጡት ወይም እንዴት እንደሚያመርቱት አታውቅም – ግን አምጥተው በከተሞች ሲረጩትና ኑሮውን ሲያሻቅቡት ታያለህ፡፡ የሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ኃላፊዎችና ፈላጭ ቆራጮች ትግሬዎች ናቸው፡፡ አየር መንገድም ሂድ ባንክም ግባ ፖለቲካ እምብዝም በማይመለከተውና ለመንግሥት በማያሰጋው ስፖርት ፌደሬሽንም ሂድ የትም ግባ የትም ውጣ ከትግሬ በስተቀር ባለሥልጣን አታይም፡፡ የቦርዶች አባላትና ሊቃነ መናብርት ከትግሬ ውጪ ብዙም አታገኝም፡፡ በምርጥ ትምህርት ቤት የሚማሩ ልጆች የወያኔ ናቸው – አስፋልት ላይ እንደሚፈጭ ጥሬ ተሰጥተው የምታያቸው ደግሞ የሌሎች ልጆች ናቸው፡፡ ሥራ ቅድሚያ የሚሰጠው ለትግሬ እንዲያም ሲል ለአሽቃባጭና ለአድርባይ ነው፡፡ ዐይን የከተማ ቦታ የሚሰጠው ለትግሬ ነው – ፈቃድ ሳያስፈልገው ሄዶ ማጠርና ቤት መሥራት ወይም በውድ ዋጋ መቀወርም ይችላል፡፡ ጦሩን እንደሰማኸው ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠሩት እነሱው ናቸው፡፡ ከጋዜጠኝነት አቅም ሳይቀር ለአማራው ክልል የሚመደቡት ከትግራይ ነው – ‹ጨ›ንና ‹ቸ›ን እየፈተሉ ሲገማምዱት በአንደበታቸው ታውቃቸዋለህ፡፡ አሁን ባሕር ዳር ላይ አንድ አማራ ጋዜጠኛ ጠፍቶ ነው? በቲቪ የሚቀርበውም ባለሥልጣን ሁሉ 11 ቁጥር ነው፡፡ አንተ ምን ቤት ነህ? ምንስ ታመጣለህ? ይህ ሁሉ ታዲያ የአጋጣሚ ነው ወይንስ የንቀት ወይንስ ከሌላው ብሔር የተማረና የዜግነት መብቱም መከበር የሚያስፈልገው ሰው ጠፍቶ ይሆን? ሌሎች ከጥቅምና ከኃላፊነት የሚታገዱት ለወያኔ ፖለቲካ ስለማይታመኑ ይሆን?  ሌላው ይቅርና የየትምህርት ቤቱን ርዕሰ መምህርና ም/ር/መምህር፣ ዩኒት ሊደር፣ የየዩኒቨርስቲውንና ኮሌጁን አመራርና አስተዳደር ብትቃኝ መቶ በመቶ በነሱው እጅ ነው – ልብ አድርግ! ለምሳሌ የአንድ ኮሌጅ ዲን/ፕሬዚደንት በዘሩ ትግሬ ባይሆን ከጎኑ ሻጥ ብሎ እንደዐረብ በርሜል ገፊ ወደተፈለገው አቅጣጫ የሚያሽከረክረው ትግሬ መኖሩን ማወቅ አለብህ፤ ደግሞም በስሞች እንዳትዘናጋ፡- ወርቁ ፈረደ መኮንን ወይም ተሾመ አበበ የሚሉ ስሞችን ብታይ ወይም ገመቹ በዳዳና ጫልቱ ገቤሣ የሚሉ ስሞችን ብትሰማ ትግሬ ሊሆኑ እንደሚችሉ ክፉኛ ጠርጥር – በማስመሰል እንደወያኔ የለምና፡፡ ለኦሮሞ የትግሬ ኦሮሞ፣ ለአማራ የትግሬ አማራ፣ ለአፋር የትግሬ አፋር… ማዘጋጀት ለወያኔ በጣም ቀላል ነው -  ለሥራው እንደሆነ ጊዜው ሞልቷል፡፡ በ22 ዓመታት ውስጥ እንኳን የትግሬ ጉራጌና የትግሬ ፈረንጅም መሥራት ይቻላልና በቋንቋ ተታለህ ልብህን እንዳትሰጥ፡፡ ኤርትራዊው በረከት ስምዖን ጎንደር ውስጥ ተወልዶ አድጎ በዘሬን ብተው ያንዘርዝረኝ ይሄውና ሕወሓትን ቀጥ አድርጎ á‹­á‹ž የለም? የብአዴን አባል ሲሉኝ እንዴት እንደምናደድ ልነግራችሁ አልችልም፡፡ ማነው በረከትን ብአዴን ያደረገው? ከሕግሓኤና(ሻዕቢያ) ከሕወሓት ጉያ አውጥቶ ለሥልቱ ሲል ትግሬውን ሰውዬ አማራ ያደረገው መለስ እንጂ በዘር ሐረጉ እንደሆነ የጠራ ኤርትራዊ ነው፡፡ እውነትን ለመናገር ስለፈለግሁ እንጂ በረከት አማራ ቀርቶ ሲያሻው ጦጣም ይሁን – ለነገሩ  ለካንስ ጦጣ ልቅም ያለች ቆንጆ ናት!

በግሉ ዘርፍም ከሞላ ጎደል ዋና ዋናው የንግድና የኢኮኖሚ ሴክተር የተያዘው በነሱው ነው፡፡ የንግድ ድርጅት በአክሲዮን ልታቋቁም ብትፈልግ ትግሬዎቹን ካላካተትህ አትታመንምና በግድህ ታስገባቸዋለህ፤ በዚያውም ሥራህ ይቀላጠፍልሃል – በሥልክ ብቻ፡፡ ቢሮክራሲው የተያዘው በነሱ ስለሆነ የምች መድኃኒት የሚሆን ትግሬ ካልያዝክ ተደፍተህ ትቀራታለህ እንጂ አንድም ነገር አይሳካልህም፡፡

አዲስ አበባ ውስጥ ስትኖር መቀሌ ላይ ያለህ ሊመስልህ ቢችል ጠግቦ የሚዘፍነውና የሚያዘፍነው በመኪናም የሚርመሰመሰው በአብዛኛው የትግራይ ተወላጅ ወርቁ ዘውግ በመሆኑ ብዙም አይግረምህ፡፡ ሌላው አፈር እየጋጠ የወያኔ ትግሬ ዊስኪ እየጨለጠና ጮማ እየቆረጠ ያለበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነው ያለ ጎይታይ፡፡ አንዳንዴ ‹እንዴ፣ (አንዳንዱ) ትግሬ አስተዳደር ብቻ ሳይሆን ጥጋብም አይችልም እንዴ?› ብለህ ልታስብ ትችላለህ፤ እውነትህንም ነው፡፡ ወንድሜ (አንዳንዶች) ጥጋብ አይችሉም – በፍትህ ማስተዳደርም፡፡ እርግጥ ነው በሩቅ ያድርግ እንጂ ጥጋብን ማንም አይችላትም፤ በነሱ ግን የባሰ መሰለኝ፡፡

ወያኔዎች ራሳቸው ሕግ ስለሆኑ ከማንኛውም ሕግ በላይ ናቸው፡፡ ለአንተ ግን ያለው ሕግ ቢጠብህ ወይ ቢሰፋህ በአንድ አዳር ሌላ አዲስ ሕግ ወጥቶ እንድትቀየድ ትደረጋለህ፡፡ የትግሬን ‘all-out’ ወረራ ስታይ ‹በውነት ትግራይ ውስጥ ለቤት ጠባቂነት እንኳ የቀረ ሰው ይኖር ይሆን?› ብለህ ልታስብ ትችላለህ፡፡ ለአቅመ ሀገር ወረራ የደረሰ ትግሬ ትግራይ ላይ ተወስኖ የቀረ ላይመስልህም ቢችል ትክክል ነህ፡፡ በመሠረቱ ሁሉም ሕዝብ ከትግራይ ተነቅሎ ሊመጣ አይችልም፤ አይጠበቅምም፡፡ ነገር ግን ንቃታቸውና ብልጥነታቸው ከአብዛኛው ትግሬ የተሻሉ የትግራይ ልጆች ከዚያች በተፈጥሮ ሀብት እየተመናመነ መሄድ ምክንያት በድርቅ ከተመታች ክፍለ ሀገር እየተወነጨፉ መለስ በፈጠራት መላዋ ኢትዮጵያ በየዘርፉ ተሰግስገው ሞልተውልሃል፤ አንተ ግን በስደት አሣርህን ታያለህ፡፡ ቤንሻንጉል ሂድ፣ አፋር ሂድ፣ ደቡብ ሂድ፣ ምሥራቅ ሂድ፣ ምዕራብ ሂድ ሁለት ኢትዮጵያውያን ባሉበት አንድ ወንድሞቹን ለሆዱ ሲል የካደ ትግሬ ታገኛለህ፡፡ ሌላውን ጅል ኮንዶም ፊት ለፊት ያደርጉትና በርሱ ቂጥ እየፈሱ አንተን ያሞኙሃል – “ጠቅላይ ሚኒስትር” ኃይለ ማርያምን እንደሚጫወቱበት ዓይነት ማለት ነው፡፡

ይህችንም በድጋሚ ላስታውስህ፡- (ጥቂቶቹ) ሀፍረትና ይሉኝታ ብሎ ነገር አልፈጠረባቸውም፤ ስለነሱ እኛ እያፈርንላቸው በቀጥቃጭነትና በተቀጥቃጭነት የጎሪጥ እየተያየን  አብረን እስካሁን አለን፡፡ ይህ ፍርጃ እስከመቼ እንደሚቀጥል በውል ተለይቶ ባይታወቅም የጫሩት እሳት ሀገር ምድሩን እየለበለበ አሁን ድረስ ዘልቋል፡፡ የሥሉስ ባዛውር ጸሎት በሠመረ ዕለት ግን ይህ እሳት ወደነሱው ዞሮ አንድ ፈረንጅ በኢሣት የቴሌቪዥን መስኮት ሲናገር እንደሰማሁት … የሥራቸውን ያገኛሉ የሚል ከግምት ያለፈ እምነት አለኝ፡፡ ያኔ ታዲያ ወዮ ለኛ በሉ፤ ቀኑ ቀርቧል፡፡ የበረሃ አንበጣ እየበላ ‹ንስሃ ግቡ፣ መንግሥተ ሰማይ ቀርባለች› እያለ ይጮህ የነበረውን መጥምቁ ዮሐንስን በዚህን ዘመን መጠበቅ የዋህነት ነው፡፡ እግዚአብሔር ኃጢያተኞችንም ያናግራልና በምለው ነገር እንዳትዘባበቱ በኅያው እግዚአብሔር ስም አደራችሁን፤ ይልቁንስ በተለቀለቀው ዐውድማ ውስጥ ገብተን ሁላችንም እንደእህል ከመወቃታችን በፊት ልብ ያለው ልብ ይበልና አንድ ነገር ይደረግ፡፡ ‹አይመጣምን ትተሸ ይመጣልን ባሰብሽ› እንደተባለው አንዳች መላ ያለው ወገን ከአሁኑ በባሰ ብዙ ሳይረፍድብንና በሌሎች ሀገራት እንደዘበት የታዘብነው ዕልቂት ሳይከሰት ሥር ለሰደደው ችግራችን ዘዴና ብልሃት እንፈልግለት፡፡

በወያኔ ምልዓት እንድትገረም ጥቂት እውነታዎችን ላክልልህ፡፡ ከቀበሌ ጀምርና እስከላይ ውጣ የምታገኘው ባለሥልጣን በአብዛኛው ትግሬ ነው፡፡ በአብዛኛው የምልህ ትግሬ ተቀጣሪ እስኪዘጋጅ ወይም ለማስመሰል ሲባል ብቻ የሚቀጠሩ አንዳንድ ሌላ ምርጫ ያጡ የሌላ ብሔር ድምጽ አልባ አባላት መኖራቸውን ለመጠቆም እንጂ አዛዥ ናዛዡማ የትም ይሁን የት ያው ትግሬ ነው – ይገርምሃል ወንድማለም – የአማራውን ወይም የኦሮሞውን የይስሙላ ሥራ አስኪያጅ ጽዳቷ ወይም ዘበኛው ትግሬ ሲያንቆራጥጠው ብታይ ልዩ አፓርይድ ባለበት ኢትዮጵያ ውስጥ ስለምትገኝ እንዳትደነቅ፡፡ ይህን ተናገርክ አልተናገርክ መሬት ላይ የፈጠጠውን እውነት አይለውጠውም፡፡ መቀያየም ዱሮ ቀረ እህታለም፡፡ የቀብር ጉድጓድ ውስጥ ሆነህ እውነትን ብትሸፋፍን ይበልጥ የምትጎዳው አንተ እንጂ ቀባሪህ አይደለም፡፡ ቀባሪህማ ያንተን ዝምታ ይፈልገዋል – ቀባሪህ ተራው ደርሶ እስኪቀበር ያንተን ፍጹማዊ ታዛዥነት ይሻል፡፡ የሚደንቀው ግን ይህን ሥርዓት ባርከውና ቀድሰው የላኩት የዴሞክራሲ ቁንጮ ነን የሚሉን አሜሪካውያን መሆናቸው ነው፡፡ ሁሉን ነገር ያውቁታል፡፡ ነገር ግን ለምን ይህን መፃጉዕ ሥርዓት ከዚያ መፃጉዕ ሰውዬ ጋር በኢትዮጵያ ላይ እንዳነገሡ ሊገባን ያልቻልን ወገኖች ብዙ ነን፡፡ ምናልባት የብሔራዊ ስሜቱ በአንጻራዊነት ከሌሎች የተሻለና ሁሉንም አስተባብሮ ፓናአፍሪካኒዝምን ያስፋፋል ብለው የሚፈሩትን አማራንና የኦርቶዶክስን ሃይማኖት ከጨዋታ ውጪ ለማድረግ አስበው ከሆነ ተሳስተዋል – የማይጠፋን ለማጥፋት መሞከር ለጊዜው እንጂ እስከወዲያኛው አይሳካም፤ ስትቀብረው የሚፋፋ፣ ስታጠፋው የሚገን፣ ስትገድለው የሚድን፣ ስትበትነው የሚሰባሰብ ነገር መኖሩን ማወቅ ይገባል(በፊዚክስ ትምህርት Matter is neither created nor destructed. የሚል አባባል አለ መሰለኝ፤ አማራም እንደዚያው ነው – አትፈጥረውም አታጠፋውምም፤በቃ! እህል -ለምሳሌ ስንዴ – ካልሞተ እንደማይበዛ ታውቅ የለም?)፡፡ ከኢትዮጵያዊነቱ ውጪ አንድም የማንነት መገለጫ የሌለውን አማራ ለማጥፋት ብዙ ዓለም አቀፍ ጥረት ቢደረግም እንኳንስ ሊጠፋ ሌሎችን እያስተባበረ ሀገሩን በጋራና በእኩልነት ሊያስተዳድር ዝግጅቱን አጠናቅቋል – ይህ ዜና እርግጥ ነው ለክፍታፎቹ ለነመሀመድ የኑስና ስብሃት ነጋ የሚመር ነው፡፡ በ80ዎቹ ሚሊዮኖች ለሚቆጠረው ምዝብር ኢትዮጵያዊ ግን ታላቅ የምሥራች ነው፡፡ ሊነጋ ሲል መጨላለሙ የነበረ ነው፡፡

[off the record] በልጅነቴ እንዲች ያለች የዘፈን ግጥም እሰማ ነበር፤አሁን ትዝ አለችኝ፡-

ነግሬሽ ነበረ ባጥር ተንጠልጥዬ፤

          ትግሬ ውሽማ እንጂ ባል አይሆንም ብዬ፡፡

[on the record]ጥሩ ነው፡፡ ፈጣሪ ለባልነት አጫቸው፡፡ አያያዙን ባለማወቃቸው ግን የተሰጣቸውን ዕድል አማሰኑት፡፡ አሁን ሥልጣን ከያዙት ውስጥ በርካታዎቹ እንኳን ለባልነት ለውሽምነትም እማይሆኑ መሆናቸውን በገሃድ አረጋገጡ፡፡ እነሱንና መሰል ደቀ መዛሙርታቸውን አስተካክሎ ሰው እስኪሆኑ ድረስ እግዚአብሔር በምን ሂደት ውስጥ ሊያሳልፋቸው እንደሚችል ከመገመት ውጪ እርግጡን ማወቅ ያስቸግራል፡፡ የሚያሳዝኑኝ – ቫይረሱ ሊኖርባቸው ወይ ላይኖርባቸው ቢችልም – እንደለዘብተኞቹ ሁቱዎች እየሆነ ባለው ሁሉ ቅስማቸው የሚሰበረውና በሌሎች ወንድሞቻቸው ስቃይና እንግልት አንጀታቸው እየተላወሰ ያሉ ትግሬዎች ናቸው፡፡ እነዚህኞቹ ባለኅሊና ትግሬዎች – ከነዚህም ውስጥ የተወሰኑት ከዚያ አስጠሊታ የዘር አሽክላ ነጻ ይሆናሉ ብዬ ልገምት ባልፈልግም – በወንድሞቻቸውና ወንድሞቻችን ሊሆኑ በሚጠበቅባቸው ወራሪ ትግሬዎች የአማጊዶነት ጠባይ ሳያፍሩ አይቀሩም ብዬ እገምታለሁ፡፡

ደግነቱ ዋናው ቀባሪህን ፈጣሪ አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ የዶግ አመድ አድርጎልሃል – ሊያውም ሁለቱን የዲያቢሎስ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን መሪዎችን በአንድ ጥይት አነጣጥሮ በመረምረም ሟርታቸውን በአንዴ ነው ያፈረሰው፤ ከእንግዲህ የሕንዱም ሆነ የሱዳኑ አይሠራም – ከአናቱ ተበርቁሷልና፡፡ ከአናት የተቦደሰ ትብታብ ዳግመኛ አያቆጠቁጥም፤ ለተወሰኑ ጥቂት ጊዜያት በስሙ እየነገዱ ሊቆዩ ይችላሉ እንጂ ሃቲማቸው አልቋል፡፡ አሰይጣኛቸው አይሆኑ ሆኖ ፈራርሶ ወደማይቀርበት የሲዖል ዓለም ነጉዷል፡፡ አሁን የሙት መንፈሱ በኮልኮሌዎቹ አማካይነት እየተመላለሰ አስቸገረን እንጂ የሉሲፈር ወኪል የነበረው መለስ እንደሆነ በውርጃ እንደጠፋ ሽል በዕኩይ ምግባር የበከተና በደም የሕዝብ ዕንባ የፈራረሰ በድኑ ይኑርበት አይኑርበት በማይታወቅ ሁኔታ በሚጠላትና ብዙዎች የወያኔ ትግሬዎች በሚጠየፏት ከፊል ኢትዮጵያዊት ባንዴራ ተሸፍኖ መቅ ወርዷል(መለስ እንደማይጸድቅ ትልቅ ግምት አለኝ – ግምት ነው እንግዲህ፣ ያውም ትልቅ!) – መለስ ከጸደቀ ጽድቅና ኩነኔ ከናካቴው የሉም ማለት ነው፡፡ በዚያም ላይ አፈራርሷት የፈረሰው የቅድስት ድንግልን ሀገር፣ ሀገረ ኢትዮጵያን በመሆኑ ፈጣሪ በዚያ ላይ አይቀልድም የሚል ፅኑ እምነት አለኝ፡፡ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፡፡ በመሠረቱ በማንም ሞት የመደሰት ፍላጎት የለኝም – በርሱም ሞት ያን ያህል አልተደሰትኩም – My words might seem oxymoronic, nonetheless, I cannot hide the fact that I had a mixed feeling between happiness and sorrow, for the reason(s) I never knew then, of course, when I heard his inevitably long-awaited death. በዋናነት ግና በፈጣሪ ፍርድ አልተደሰትኩም ብል መዋሸት ይሆንብኛል፡፡ የፈጣሪን ፍርድ ማድነቅ ደግሞ ተገቢ ነው፡፡ በመጨረሻው መጨረሻ ላይ በቅርብ ለሚጠበቀው  ሊወጡት ፈጽሞውን ለማይቻላቸው የመከራ ሕይወት የዳረጋቸው (አንዳንድ) ትግሬና ሌሎች ወገኖቻችንም በመለስ ሞት በከባድ ሁኔታ ሊያዝኑና የፖለቲካውን አጥብበው ‹የሀዘኑን ምኅዳር› ያን ያህል ሊለጥጡት ባልተገባ ነበር የሚል አስተያየት አለኝ፡፡ ሰውዬው ላይመለስ ሦስትና አራት በሽሎንንና ገናሌን የመሳሰሉ ትላልቅ ወንዞችን ሊገድብ የሚችል ገንዘብ በሀዘን ሰበብ እየመዘበሩና ምስሉን እየሰቀሉ ያሉ ባለሥልጣናትም ከዚህ ያልተገባ ምግባራቸው ሊቆጠቡ በተገባቸው ነበር – በሞቱ ከእሥራታቸው ነጻ ሊወጡ ይጠበቅባቸው ነበርና፡፡ በነገራችን ላይ ጊዜው ሲደርስ የመለስ አፅም ካለበት ወጥቶ ለፍርድ ቢቀርብ ደስ እንደሚለኝ ልገልጥ እወዳለሁ፡፡ መለስ በአነጋገሩም በድርጊቱም ሰው ስለመሆኑ በቂ ማስረጃ ትቶ ስላላለፈ ለሰው ልጅ በሞቱም በሕይወቱም የሚገባው ክብር ለርሱ የሚገባ አይደለምና በአነጋገሬ ሃሳብ አይግባችሁ፤ የመለስ ስብዕና የተረጋገጠው በአሻንጉሊቶቹና በነሱዛን ራይስ የዐይጥ ምሥክር ድንቢጥ የጥቅም ወይም የዐይን ፍቅር ተጋሪዎቹ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ መለስ በአካል ሳይሆን በምግባር ሰው አለመሆኑን ለመገንዘብ ከፍ ሲል የጠቀስኩትን አመክንዮ አስታውሱልኝ፡፡

አንድዬ ውሎ ይግባ እንጂ ገና ብዙ ያሳየናል፡፡ ሌሎቹንም እንደዚያው ሊቀጣ ወረፋ አሲዞልሃል፡፡ አሁን ልትማረር ትችላለህ፡፡ ነገር ግን የማታ ማታ ፈጣሪህ ይክስሃል፡፡ በሰው ደግሞ ብዙም አትተማመን፡፡ ሰው ያው ሰው ነው፤ ዱሮውንም ‹ሁለት እግራ› ይባላል – የሰውን በቃሉ አለመገኘትና አለመታመን ለማጠየቅ፡፡ ከሰው የሆነ የሰው  ነው፡፡ ፈጣሪ ያልታከለበት የሰዎች ጥረት ለተጨማሪ አበሳ ይዳርግህ ይሆናል እንጂ እምብዝም አይጠቅምህም፡፡ ከፈጣሪ ያልተላከ ከሰይጣን እንደተላከ ይቆጠራል፡፡ የሰይጣንን ልዑካን ደግሞ እስኪያንገሸግሸን አየናቸው – የፈጣሪን ሚና ወስደው እስከመመለክ የደረሱ፣ ከነጭርሱ የካዱና ያስካዱ ሆነው የተገኙ፣ እንዲሁም ሃይማኖት የሚባል የሌላቸው መሆናቸውን በይፋ ያወጁ መሪዎችን አስተናግደን የጭራቅ ብፌ ባገራችን የፖለቲካ መድረክ ሲርመሰመስ ታዝበናል፤ ከአሁን በኋላ የሚመጣው ከእስካሁኖቹ የተለዬ መሆን አለበት፡፡ ወደፈጣሪ ግን ከአንገት ሳይሆን ከአንጀት ልንመለስ ይገባናል፡፡

ሌሎች ባለወር ተራ ነን ባዮችም በመቶዎች የስግብግብነትና የሥልጣን ጥም ማርኪያ አጥሮች ውስጥ ታጭቀውና ላለመደማመጥና ላለመግባባት ምለው ተገዝተው ይሄውና ለሌላ ዙር ስቃይና እንግልት ሊያመቻቹህ በሚመስል መንገድ ሲዶልቱ እነሱ እንኳን ባቅማቸው – ገና በላም አለኝ በሰማይ – እርስ በርሳቸው እየተራኮቱና እየተጣሉም አይደል? ስንት ቦታ የተከፋፈሉ መሰለህ! አዎ፣ እባብ የልቡን አይቶ እግሩን ነሳው እንዲሉ ነው ነገሩ፡፡ ከነዚህ የሕይወት ገጠመኝና ዕድሜ ከማያስተምራቸው ገልቱ ጎምቱዎች መካከል አንዳቸውም እንኳ የሚጠቅሙህ ቢሆኑ ኖሮ ነጻነትህ እስካሁን አይቆይብህም ነበር፡፡ እንግዲያውስ ፈጣሪ የራሱን ሰው እስኪያዘጋጅ ታገስ፡፡ የራሱ ጊዜ ሲደርስ፣ የራሱን ሰዎች ሲያዘጋጅ ግን በየትኛውም ጎራ የሚገኙ እነዚህን አልቅትና መዥገሮች፣በተለይም እነኚህን አንበጣና ተምቾች እንደጢስ አብንኖ ያስወግድልሃል – የምልህ እውነት ነው ወገኔ – ብቻ በርትተህ ጸልይ፤ ከመጥፎ ሥራም ተቆጠብ፤ ራስህን ፈትሽ፤ ብዙ፣ እጅግ ብዙ የምታስተካክላቸው ነገሮች አሉ፤ ፍቅር ሸሽታሃለች – ሀሰተኝነት በደጅህ ተንሠራፍቷል፤ እያለህ እንደሌለህ ሆነሃል – በሥጋም በመንፈስም፡፡ ብዛትህ የአካል እንጂ የመንፈስ ልሂቅነትን አልጨመረም፡፡ ሆዳምነትና ዘረኝነት ኅልውናህን እየቦረቦሩት ናቸው፡፡ ሆን ተብሎ የተዘራብህ ማይምነትና የሞራል ዝቅጠት እያኮሰመነ ከሰውነት ተራ ሊያወጣህ ተቃርቧልና በቶሎ ተመለስ – እንስተካከል ወገን፡፡ አስቸጋሪ እንግዳ ተዘቅዝቆ ይተኛል ይባላል፡- ተዘቅዝቅን እየጸለይን ፈጣሪ ሊሰማን ተቸገረ፡፡ የኛን የቤት ሥራ ከሠራን ግን ፈጣሪ በኛ ላይ አንዲትም ቀን የሚጨክን ልብ የለውም – አሁን ግን ምናችንን አይቶ ይድረስልን? ጠፍተናል እኮ! አልጠፋንም ብለን ልንዋሽ አይገባም፡፡

እነዚህ ወያኔዎች እንኳን ለፈጣሪ ለሰውም የሚከብዱ ሆነው እንዳልሆነ ተገንዘብ፡፡ በፍጹም፡፡ አሁን ለምሳሌ በቤተ መንግሥት ማን አለ? ማንም! ማን ነው ሀገሪቱን እያስተዳደረ ያለው? ማንም! ከመጠነኛ ወንጀሎች በስተቀር የሀገሪቱ ዜጎች በአንጻራዊ ሁኔታ ሰላም ውለው ወደየቤታቸው የሚገቡት በማን ጠባቂነት ይመስልሃል? በማንም! ፖሊሱ ራሱ በዘረፋ ተግባር በሚሠማራባት ሀገር፣ ባለሥልጣኑ ሁሉ በገንዘብ ፍቅር በተለከፈባት ሀገር፣ ፍርድ ቤት በሌለባት ሀገር፣ ፍትሕ በጠፋባት ሀገር… ዜጎች በማን ጠባቂነት ወጥተው የሚገቡ ይመስልሃል? በማንም! ማን ነው ታዲያ የሀገሪቱን እስትንፋስ ውሎ እንዲያድር እያደረገ ያለው? ከፈጣሪ በስተቀር ማንም! እናስ? ነገን ለማየት ከክፉ ሥራ ተቆጥበንና እውነትን ተገን አድርገን በትግስት እንኑር፤ ሁሉም ያልፋል፡፡ ሁሉንም በቅርብ ታያለህ፡፡ የጠገበ የሚራብ አይመስለውም፡፡ የተራበም የሚጠግብ አይመስለውም፡፡ ሁለቱ ግን ተወራራሽና ተፈራራቂም ናቸው – አንዱ በሌላኛው ማኅፀን ውስጥ ይኖራል፤ ጊዜው ሲደርስ ግን ግዘፍ ነስቶ ይወጣና አዲሱ ኹነት ነባሩንና ቀዳሚውን አስወግዶ የራሱን ተራ ይረከባል፡፡ የጠገበ ይራባል፤ የተራበም ይጠግባል፡፡ ግን ለሁሉም ጊዜ አለው – የሎሚ ተራ ተራም ጉዳይ ነው፡፡ እና እነዚህ እከካቸውን በኢትዮጵያ ሕዝብ ሀብትና ንብረት ያራገፉና እንደ መዥገር ያበጡ የወያኔ ትግሬዎች እንደፊኛ የሚፈነዱበት – እንደ እምቧይ የሚፈርጡበት ዘመን በመቃረቡ ሃሤት አድርግ፡፡ እዩኝ እዩኝ ያለ ደብቁኝ ደብቁኝ ይላል ትል የለም በብሂልህ? ታዲያ ምን አዲስ ነገር አየህ? ዘመን ሲያዘም የሚከሰተውን ጉድ ታያለህ፡፡ በዚህ ድራማ ውስጥ እየተሳተፉ ለሚገኙ ትግሬዎች ግን እዘን፡፡ ወዮ ለነሱ! ወዮ ለኛ! ወዮ ላማጭ ለረማጭ! ወዮ ለዚያች ቀን! አማራ ሆኖ መፈጠር ያስጨነቀውንና ራስን ያስረገመውን ያህል ትግሬ ሆኖ መፈጠር ዕጥፍ ድርብ የሚያስጨንቅበትና እንደኢዮብ ዕለተ ፍጥረትን የሚያስረግም ዘመን በቅርብ ይመጣል፡፡ ዛሬ ስንሻው ስሙን ወደ ሐጎስነት የለወጠውን ያህል ነገ ጎይቶምና አብረኸት ወደ ዘበርጋና ሻሽቱ ይለውጣሉ – ሊያውም ጊዜ ካለን፡፡ ዛሬ የመለስን ፎቶ ለታይታና ለማስመሰል እንደአሽንክታብ በደረት ኪስና በቦርሣ ያልያዙትን ያህል፣ እንደሮናልዶ ምስል በመኪና ውስጥ ያልለጠፉትን ያህል፣ በቤት ውስጥ እንደስዕለ ማርያም በሚያምር ፍሬም ያልሰቀሉትን ያህል – á‹« ጊዜ ሲመጣ  እንደጴጥሮስ ‹ ይህን የምትሉትን ሰው ካለዛሬ አላውቀውም› የሚባልበት የነጻነት ዘመን ሊወለድ የቀረው ጊዜ እጅግ በጣም አጭር ነው፡፡ ዛሬ ወዶና ፈቅዶ ሳይሆን ለማስመሰልና አካባቢን ለመመሳሰል ብሎ የትግርኛ ዘፈንን የሞባይል የጥሪ ድምፅ የሚያደርግ ኢ-ትግሬ ዜጋ ጅላጅል አድራጎቱን የሚኮንንበት ጊዜ እየመጣ ነው (በነገራችን ላይ የኔ ሞባይል መጥሪያ ብዙውን ጊዜ የትግርኛ ኢንስትሩመንታል ነው – ምርጫየ ስለሆነ!)፡፡ የምነግርህ ያዋጁን በጆሮ ያህል ነው፤ ነገር አላብዛብህ፡፡ በቸር ያገናኘን፡፡

ኅሊናው ለታወረ የእውነት ብርሃንን፣ አንጎሉ በሞራ ለተሸፈነ መገለጥን፣ ልቡ በገንዘብና በሀብት ፍትወት ለናወዘ መፍትሔ ሥራዩን አንድዬ እንዲያዝለት እየተመኘሁ … የዛሬዋን ‹አጭር› ጦማር አበቃሁ፡፡

በእግዚአብሄር ኃይል ኢትዮጵያ በክብር ትነሣለች!

 

Finale

 

“No one has the right to choose from which ethnic group she/he should be born; being Tigrian or Amhara by birth is not a matter of choice, it is rather mere coincidence naturally favored by environmental and societal phenomena.”

‘Anonymous’

                                                Source: —

 

They think because they hold us in their infernal chains of slavery, that we wish to be white[Tigrian?], or of their color[ethnic group?]—but they are dreadfully deceived—we wish to be just as it pleased our Creator to have made us.

David Walker (1785 - 1830

 

Our dehumanization of the Negro then is indivisible from our dehumanization of ourselves: the loss of our own identity is the price we pay for our annulment of his.

James Baldwin (1924 - 1987)

 

I’m really not such an idiot that I don’t realize that if a man calls me a nigger, it’s his fault the first time, but mine if he has the opportunity to do it again.

            Nella Larsen   (1891 - 1964)

 

To like an individual because he’s black[Tigrian] is just as insulting as to dislike him because he isn’t white[Amhara – (take care of ill-conceived connotations!)].

            Attributed to E. E. Cummings   (1894 - 1962)

 

Socrates said he was not an Athenian or a Greek, but a citizen of the world.

            Plutarch   (46? - 120?)

 

Our nation is moving towards two societies, one black[non-Tigrian], one white[Tigrian]—separate and unequal.

            Otto Kerner, Jr.   (1908 - 1976)

Source: M. Encarta, 2009 ed., suggestive additions in brackets are  mine.

 

Racism is the lowest, most crudely primitive form of collectivism. It is the notion of ascribing moral, social or political significance to a man’s genetic lineage—the notion that a man’s intellectual and characterological traits are produced and transmitted by his internal body chemistry. Which means, in practice, that a man is to be judged, not by his own character and actions, but by the characters and actions of a collective of ancestors.

Source: The Virtue of Selfishness, Ayn Rand

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on December 17, 2012
  • By:
  • Last Modified: December 17, 2012 @ 8:01 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar