www.maledatimes.com በጊዜ ያንብቡት ( በይግዛው እያሱ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በጊዜ ያንብቡት ( በይግዛው እያሱ)

By   /   December 19, 2012  /   Comments Off on በጊዜ ያንብቡት ( በይግዛው እያሱ)

    Print       Email
0 0
Read Time:12 Minute, 35 Second
በጊዜ ያንብቡት ( በ ይግዛው እያሱ)
ማንም ሰው ስለ ወያኔለማወቅወያኔነትንመቀበልአይጠበቅበትም:: ወያኔነትንለመቀበልየወያኔንተንኮልናሴራተቀብሎህዝብንበጋራለማጥፋትየተዘጋጀመሆኑንማረጋገጥናመፈለግብቻነው::ወያኔዎችበጋራየሚስማሙበትነገርየህዝብፍትህየህዝብእኩልነትየህዝብመብትየሚረጋገጥበትን በአጠቃላይአገራዊስሜትንበማጥፋትየወያኔንጥቅምናየስልጣንዘመናቸውንለማራዘምየሚያደርጉትንማንኛውምየተንኮልስራለመደገፍቃልየሚገባበትን የጋራሰነዳቸውመከበሩላይ ነው::
ይህንእያወቁወገናቸውንለማጥፋትበፍርፋሪተታለውመሀላየሚፈፅሙብዙዎችናቸው:: ትቂቶቹችግርአስገድዷቸውየሚቀበሉሲሆኑአብዛኞቹደግሞህሌናቸውንሽጠውለሆዳቸውያደሩሆድአደሮችእንደሆኑይታወቃል:: ባጠቃላይየወያኔመንግስትየዘርፖለቲካባገሪቱውስጥበማንገስህዝቡንበብሄርከፋፍሎአንዱንካንዱበማባላትየስልጣንዘመኑንለማራዘምየተጠቀመበትአካሄድለጊዜውየጠቀመውቢሆንምህዝቡግንዛሬዛሬእውነታውንእየተረዳሲመጣእውነትለህዝቡበማሰብበቋንቋውበባህሉየመጠቀምየመናገርየመዳኘትመብትአለህየተባለውእውንሆኖበተግባርሲተረጎምእያየውባለመሆኑወያኔንአንቅሮየተፋበትናለማስወገድምጥረትእያደረገያለበትወቅትላይደርሷል::
ወያኔበአንድየዘርየጎሳየበላይነትተቋቁሞከጫካእስከከተማየሚያደርጋቸውተነኮሎቹደባዎቹሁሌ ራሱን ኮፍሶ እንዲኖር የሚያደርግበት አካሄዱ ማብቂያው አሁን ነው:: ውድ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! ዛሬ ወያኔ መጽሐፍ ነው:: የተንኮል መጽሐፍ:: ገለጥ እያደረግን ስናየው ጉዱን ከውስጡ ዘርዝረን ማንበብ የምንችለው:: ማንም ኢትዮጵያዊ ስለወያኔ ተንኮል ሴራ ከፋፍሎ ለመግዛት ስለተጠቀመበት ስልት የሕዝብን ሀብት በመበዝበዝ የራሱን ካዝና በማድለብ የሕዝብን ሀብት ለግሉ ያዋለ ስለመሆኑ በውጭ ባንኮች ብሩን እየሰበሰበ ያለ መሆኑን ህዝቡን ከቀየውና ካገሩ እያፈናቀለ መሬቱን ለውጭ ባለሀብት በመቸብቸብ ገነዘቡን በሙስና በመዝረፍ የሚያሸሽ መሆኑን ወያኔ የሚቃወሙትን አሸባሪ በማለት በህገ መንግስቱ ላይ በመቆም ህገ መንግስት እየጣሰ ያለ መንግስት መሆኑን ጋዜጠኞችን አሸባሪ በማለት የሚያስር መሆኑን ወያኔ የከተማውን ህብረተሰብ በመልሶ ግንባታ ሽፋን ቤቱን በዶዘር እያፈራረሰ ከቦታው እያፈናቀለና እያሳደደ ካገር እንዲወጡ እያደረገ ያለ መሆኑን ወያኔ ሲሻው እየገደለ ሲያሻው ዜጎችን ያለአግባብ እያሰረና በወያኔ ያልተጠመቀ በአገሪቱ ሰርቶ መኖር እንዳይችል እያደረገ ያለ መሆኑን ወያኔ የሀይማኖት ነጻነትን በመገደብ ህዝቡን በእምነቱ እንዳይጸልይ በማድረግ ሙስሊሙን ከመስጊድ ኦርቶዶክሱን ከየቤትክርስቲያኑና ከየገዳማቱ በማስወጣት የሚያሳድድና የሚያስር ጨካኝ መንግስት መሆኑን ወያኔ በልማት ሽፋን ከጉሮሮው እየነጠቀ የወር ደምወዙን በመውሰድ የመንገግስት ሰራተኛው በርሀብ እየተሰቃየ ቤተሰቡን መምራት እንዳይችል እያደረገ ያለ መሆኑን ወያኔ ሰላዮቹን በህዝብ ላይ በማሰማራት የወያኔን ስርዓት ለመቃወም አስባችኋል በማለት ድብደባ ስቃይና እሳራት በህዝብ ላይ እያደረሰ ያለ መሆኑን ባጠቃላይ ወያኔ የመከራ ቀንበር በህዝብ ላይ ጭኖ ዘላለም ለመኖር እያሰበ ያለ መንግስት መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ ያውቀዋል::
ይህን የህዝብ የጋራ ችግር የሆነውን ወያኔ በአንድ ጠቅለል ባለ ወረቀት ላይ የጻፈው ጸሀፊ ጋዜጠኛ አትሞ ስላወጣው ሀዝብን ለአመጽ የሚያነሳሳ ጹሁፍ ጽፈህል ተብሎ ሲያስር ይታያል:: ህዝቡ ይህንን መጽሀፍ በየቤቱ ጽፎ ራሱ ይዞታል:: ይህ ጋዜጠኛ ምናልባትም ህዝባዊ ስላደረገው ባንድ ሰው ስም አሳትሞ በመውጣቱ ካልሆነ በስተቀር ችግሩን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይቅርና ወያኔም ራሱ ያውቀዋል:: ታዲያ ወያኔ ምኑ ላይ ነው ለሰላም ታግያለሁ ለሰላም ቆሚያለሁ ብሎ ህዝባዊ ስራን ሰርቶ ልማት አምጥቶ የኢትዮጵያን ህዝብ ከችግር አውጥቶ ህዝቡ የሰላም አየር ተንፍሶ ህዝቡ በሰላም ወጥቶ ገብቶ ልጆቹን አስተምሮ በሰላም ያለችግር ርሀብ ጠፍቶ በቀን ሶስት ጊዜ በልቶ ኑሮውን የሚገፋው::? ደርግ ብሄራዊ ውትድርና የመንደር ምስረታ የአምራቾች የህብረት ስራ ማህበር ያለ ህዝብ ፋላጎት በህዝብ ላይ ጫነ ብሎ ወያኔ ጫካ ሆኖ ከዚህ ነጻ አወጣሃለሁ እያለ ሲተርክልን ሲዘምርልን ኖሮ መንበረ ስልጣኑን በህዝብ ድጋፍ ከተቆናጠጠባት ቀን ጀመሮ ግን ብሄራዊ ውትድርና መልኩን ቀይሮ የኢትዮጵያ ወጣት ለውጭ ሀይሎች እየተሸጠ ሌላ አገር እየሄደ ሲዋጋና ሲሞት ይታያል:: ከዚህ የሚገኘው ገቢ የባለስልጣናት ካዝና ማሞቂያ ሆኗል:: ሰፈራ ማስፈሩ በደርግ ምን ላይ ነው ጥፋቱ? በጋራ  መኖሩ? ዛሬ መሬቱ ለውጭ ባለህብት በመሸጡ ሚሰፍርበት ጠፍቶ አርሶ አደሩ ከቀየውና ካገሩ እየተሰደደ በየሜዳው አልቀረም? ሚላስ ሚቀመስ አጥቶ በርሀብ እያለቀ አይደለምን?
       የዚህ ችግር ስፋት መቋጫው አሁን ነው:: ራሱን ላልሆነው ወያኔ ጊዜ አንስጥ:: በአውጫጭኝ ተደግፎ ትልቁን የኢትዮጵያ ህዝብ ሊመራ አይችልም::
ስለዚህ:-
   እኛውለእኛእንቁም  (በይግዛውእያሱ)
ከትግራይኦሮሚያከአማራተውጣጠው
ሊደግፉኝመጡከደቡብተስፋአጥተው::
እኔምብየነበርከፊትእንድትመሩኝ
ከኋላምሁናችሁእንድታባርሩኝ
ቃሌንእንዳከብርብርታትእንድትሁኑኝ::
ጎትቱኝደግፉኝግፉኝከኋላየ
ካለናንተአይሆንምከብዶኛልስራየ::
ድንገትሳላስበውሰዎችጥለውብኝ
እየሱስጌታየአጋዡንላከልኝ::
እንደፓሮትሆኘራዩንላስቀጥል
ነፍሱንይማርናመሌንለመወከል
ሌጋሲለመሆንለሁሉምስራቸው
ቃልእገባለሁኝበደምባጥንታቸው::
ብለውእጅዘርግተውበፓርላማምለው
ስልጣንንሊያቆዩእውነትንረግጠው
ራስንሳይሆኑከዕምነትጋርተጣልተው
ዛሬምይዋሻሉቃልአለብኝብለው::
የተለቀመእንጨትማሰርያከሌለው
መበተኑአይቀርምእድሜውምአጭርነው::
የወያኔምዕድልአሁንእንደዚህነው
ሰብሳቢውንአጥቶባውጫጭኝሚኖረው::
ሀሰትንአዋጥተውለማግዘፍቢጥሩ
መፈርከሱአይቀርምሲጋለጥሚስጥሩ::
ነገምእያንዳንዱይኼውነውእጣቸው
እርስበርስይበላላልህዝብምሳይነካቸው::
ትናንትየጀመረውዕርስበርስመባላቱ
ነገምይቀጥላልሊሞትእናዳባቱ::
ህዝብሆይአሁንግፋጠንክርእንደራጅ
ማንንምሳንጠብቅሳንፈልግአማላጅ::
እኛውለእኛእንቁምለህልውናችን
ጠኔውነገጎድቶንሳይቆምትንፋሻችን::
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on December 19, 2012
  • By:
  • Last Modified: December 19, 2012 @ 5:07 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar