www.maledatimes.com እንኳንም አልፃፍኩ (ጨረቃ እና… ቁ2) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

እንኳንም አልፃፍኩ (ጨረቃ እና… ቁ2)

By   /   January 4, 2013  /   Comments Off on እንኳንም አልፃፍኩ (ጨረቃ እና… ቁ2)

    Print       Email
0 0
Read Time:11 Minute, 43 Second


ጨረቃ ቀይና ግዙፍ ሆና ከበፊት ክበቶ ተልቃ ተንጣላለች።ስስ ደመና ቢሸፍናትም ድምቀቶን ሊከልላት አልቻለም። ግማሽ ማንነቶ ወደ ድቅድቁ እየገባ ስባ ለማውጣት የምትታገል የሚመስለው ትዕይንቶ በሀሳቤ ውስጥ የሚሞግቱኝን ነገሮች አቁሜ ፈዝዤ እንዳያት አስገደደችኝ።ተስባ ስትወጣ፤ጎትቶ ሲያስቀራት.. በተፈጥሮ ማለልኩኝ መሰለኝ.. ’የፍጥረት ፈጣሪ እኔም አንዱ ፍጥረትክ ነኝና ማንነቴን ቀይረክ እንደ አዲስ ፍጠረኝ’… ‘’መንፈስ ስለእናንተ ይቃትታል’’ መ.ቅ ላይ አነበብኩኝ ልበል? ልክ እንደዛው ሳላስበው ከሀሳቤ መሀል፤ ሳላስበው ከጨረቃና ከምድር መሀል ፀለይኩ። ከፍጥረትና ከፈጣሪ ተመልሼ ወደ እራሴ ልብ ገባው።ከሀሳቤ ውስጥ ቀጥ ብለው እንደ ማገር ለየቅል የቆሙ ከአራት በላይ ሀሳቦች እኔኑ ወጥረውኛል። የሚገርመው ተያይዥነታቸው በአንድ ነገር ብቻ መሆኑ ነው። እሱም እኔ ደም ውስጥ በመኖራቸው ብቻ ድንገት ጅልነቴን አሰብኩ ብልጥ በመሆኔ ። አይኔን ወደ ጨረቃዋ ሰደድኩ። ከደመናው ደምቃ ለመውጣት ትታገላለች፤ሀሳቤም ከሀሳቤ ውስጥ ለመውጣት ይታገላል።ግንኙነት ያላቸው መሰለኝ ከሀሳቤ ከወጣው ጨረቃም እንደምትወጣ ጠረጠርኩ። ጥርጣሬን ለማረጋገጥ ከምፈራው ሀሳቤ ዘልዬ ተዘፈኩ። አንዱን ደረመስኩት መሰለኝ እንደ መቅለል ሲለኝ አንጋጠጥኩኝ… ደመናው ዝቅ.. ጨረቃ ብቅ ብላለች ወይ.. ጉድ… ተገረምኩ! አላቸው ማለት ይሆን ? አንድ ሁለት ጨማምሬ ከደቂቃዋች በሆላ መልሼ አንጋጠጥኩ ‘’የለመደች ጦጣ….’’ እንደሚባለው ሆነና አልሆነም በለሆሳስ መፍትሄ…… ሄ…. ሄ… ሄ ስል ተነፈስኩ። የክረምቱ ንፋስ ፊቴን ሲዳስሰው ተሰማኝ የተቀመጥኩት በምሰራበት ህንፃ አናት በአንዱ ጥግ ውሽቅ ብዬ ነው። ባለኮፍያው ሹራብ ላይ ጃኬት ደርቤአለው ከውስጥ የሥራ ሸሚዝና ቲሸርት አለ በእጄ ሳይቀር ብርዱን ለመከላከል ሹራብ አጥልቄአለው።ንፉሱ መንካት መዳሰስ የሚችለው የፊቴን75% ብቻ ነው ከድፍኑ አካሌ እሱንም እያደረገ ነው። ከአፌ ውስጥ ያለውን ጉም ተፍቼ አይኔን ጨረቃ ላይ አፍጥጬ በእኩል ደቂቃ ከሀሳቤ ተሳፈርኩ ምን ያህል እንደቆየው ባላውቅም ስመለስ በህይወቴ ያደረኳቸው እና የደረስኩበት ማንነቴ ውጤት እኩል ሂሳብ ላይ አገኘዋቸው። ለወትሮ ለምክንያት ሶስት ወይም አራት ሰዋችን አላጣም ነበር።አሁን ግን እኔ እንደሆንኩ ተረዳው ገረመኝ ።እንዴት እንደፈጠርኩት የማላውቀው ማንነቴ በብዙ ግጭቶች መሀል እኔኑ ይሞግተኛል ሲገርም መምጫውም መሄጃውም ያልታወቀ ማንነት። እንደመባነን ብዬ የአይኔን ሀይል ወደ ጨረቃ ሳብኩት። ደመናው እየሸፈናት እኔን አውጣኝ እያለች በምትለማመጠኝ በሚመስል ሁኔታ ቁራጭ ብርሃኖ ቀርቶ ነበር።ማስበው የነበረው እንደዚ ይሆን እንዴ? ራሴን ከሷ ጋር አያያዤ አሳዘነችኝ ለእሷ መያዝ ተጠያቂው ራሴን አደረኩት።ሀሳቤን ለመጣል ‘’በሚሆን ይሆናል….’’ በጅል ሀሳብ ተነፈስኩ አይኔን ጨረቃ ላይ የሚገርም ትዕይን እያየ ነበር።ከመቅጽበት ቁራጭ ብርሀኖን እየተጎተተ የወጣች ይመስል ተስባ ወጥታ ቁራጭ ማንነቶን በበፊቱ ብርሀኖ ቁራጭ ልክ ከዳመናው ስር ደበቀችው።አግራሞቴ ሥራዬን እንዳያስረሳኝ በመፍራት ሰዓቴን ስመለከት አስር ደቂቃ ቀርቶኛል። የባከነ ሰዓት በዚ ደቂቃ ከእኔ ሀሳብ ጋር ደመና ውስጥ ያለችውን ቁራሽ ጨረቃ እንዴት ነው እንደማላቃት ጨነቀኝ መፍትሄ…ሄ…ሄ አሁንም በለሆሳስ ተነፈስኩ ለእሷም ለእኔም ። ድንገት አንድ ሀሳብ መጣልኝ ሀሳቤን ለሰው ለማጋራት የማልችል ስግብግብ ስለሆንኩ ለምን አልጽፈውም… አዋ… ለምን አልጽፈውም…. አዋ ልፃፈው ! ሀሳቤንም መላውን አልኩኝ እራሴው ለራሴ። ትልቅ መፍትሄ እንዳገኘው ነገር ቅልል ሲለኝ ተሰማኝና ለማፅደቅ አይኔን አቀናው።አይኔን ማመን አቃተኝ በእዚ ቅፅበት ግዝፈቶ እና ቅላቶ ግርማ ሰጥቶት ተንጣላለች ያለመድኳት ጨረቃ ከዳመና ተላቃ።የሀሳቤን እርግጠኝነትና የጨረቃን ውበት አድኜ ቁልቁል በደረጃ ወረድኩ።መልበሻ ክፍል ስደርስ ከላይ የለበስኩትን አውልቄ በሸሚዝ ሽክ አልኩ አጀንዳዬን አንግቤ ወደ ሥራ ቦታዬ ላይ ተወዘፍኩ ውስጡ ይሞቃል ሰውነቴን ፈታ አረገው።ወዳጄ ያቀረብልኝ ትኩስ ቡና እያጣጣምኩ ትንሽም መረጋጋት አቅቶኝ ብዕሬን መዘዝኩ እንደሚጽፍ ሰው።ባዶ ወረቀት ፊት ለፊቴ አፍጥጦል።ሀሳቤም ልውጣ እያለኝ ነው።እጄም ለመፃፍ አቆብቁቦል።ግን ድፍረት አጣው ሰውን ያላመንኩ እንዴት ይሄን ጅል ወረቀት ልመን ማመን ከበደኝ እምነት ከበደኝ።በእደዚ ስሞገት ደቂቃዋችን ገደልኩኝ።ፍርሀቴን ለመደገፍ ጽፌ ማስቀምጠው ለማን ነው?ራሴን ጠየኩ መቼስ ለራሴ አይደለም ለራሴውማ እኔ ውስጥ አለ ስለዚህ አሁንም ዞሮ ዞሮ ለማካፈል ነበር ፍርሀቴን አበረታውት።ይሄኔ እኮ ጽፌው ቢሆን ኖሮ ፌስቡክ ላይ እለጥፈው ነበር ሀሳቡ ራሱ ዘገነነኝ።አማተብኩ ባለመፃፌ ፈጣሪን አመሰገንኩት በስን ጊዜዬ ።ሰዓቴ ስቃኝ ከገባው አርባ ደቂቃ እንደሆነኝ ይነግረኛል በባዶ ወረቀት ፊት።ደረቅ ቅጠል ፈልፍዬ ጎንጉኜ ወደ ደጅ ልወጣ ነው ስመለስ………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………….. እነሆ እንደዚህም ሆነ ውጪ ላይ ትቻት የመጣሁት ቀይና ግዙፎ ጨረቃ በቦታዋ የለችም በምትኳ ሁልጊዜ የማያት እንስ ያለችዋ የምታቀኝ የማውቃት ጨረቃ በፍጥነት ዳመናው እየመጣ እያለፋት ብልጭ ድርግም ያደርጋታል።ያለችበትን ሁኔታ መፍረድ ስላልቻልኩ አርቄ ደመናውን አየሁት።ድፍድፍ ብሎ ጥቁር ያለ ነው።ይሸፍናት ይሆን? ልቤን ስጋት ገባው። እያንጎራጎርኩ ተመለስኩ….. ‘’ከአገር ከሰፈሩ እኔ አንቺን ወድጄ ጨረቃ
አይንሽን አያለው ከሁሉም አብልጬ ጨረቃ’’ …… …ግን ግን እንኳንም አልፃፍ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on January 4, 2013
  • By:
  • Last Modified: January 4, 2013 @ 1:01 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar