www.maledatimes.com እኔማ (ከዘ.ገ ማለዳ ታይምስ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

እኔማ (ከዘ.ገ ማለዳ ታይምስ)

By   /   January 12, 2013  /   Comments Off on እኔማ (ከዘ.ገ ማለዳ ታይምስ)

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 47 Second

እኔማ 
ለማያርፈው አይንሽ ለሚቅበዘበዘው
ፈርሃቱን ንዶ አገር የሚያደርሰው 
ረፍትሽን ነስቶ ቀልብሽ ላይገዛ 
ላላይሽ በቅጡ 
በጄ ላልጨብጥሽ እንዲያው እንደ ዋዛ
“ስሜት” ስትይ በውነት 
የማውቀውን ስሜትሽን 
ያ` የለመድኩት ገላ የማውቀው ሰውነት
በፍቅር ተግዳሮት 
ልቤ የወደቀበት
ሽሮ ላይድንልኝ 
በውድቅቱ ለሊት 
ያንቺን ነፍስ አድነሽ
የኔን ገድለሽብኝ 
ስውር ብለሽ ጠፍተሽ
መፍትሄው ሲጠፋሽ
ሁነቱን ስታውቂው 
ጥፋትሽ ሲቀጣሽ 
ዛሬ ሰሜት አልሽኝ »»»»»ያኔማ 
ሳታውቂኝ ኖሬብሽ 
በፍቅር አስሬሽ
ከውስጥሽ በቀዬ መሆኑን ስታውቂ 
ከህልም አለም ኑሮሽ ደግመሽ ስትነቂ
በብራና ቀለም በልብሽ ጽፈሽኝ
ዛሬ በውን አለም መኖሬን ስታውቂ 
ነው ወይስ ስሜትሽ አሁንም ገፍትሮሽ 
ተባታይ ፈልገሽ መዳራቱን መርጠሽ 
ፍላጎትሽ ንሮ እኔን አስፈልጎሽ 
ይሆን የጠራሽኝ ?
እረ ምኑ ይሆን ያንቺ ጉዳይ ከቶ 
ከምን ገብተሽ ይሆን ?
ከፍቅር ምናኔ ወይስ ካድባራቱ
በፍቅር ስልባቦት እንዲህ መዋተቱ »»
ስትይኝ ሰማሁሽ 
መሽቶም አይነጋልኝ 
አይኔም አይከደን 
ኑሮም አይሆንልኝ 
ያላንተ አልጣጣም 
ከማንም አልገጥም 
ጨለማው ምጥ ሆኖ 
እኔን ሲያስጨንቀኝ 
ባስበው ባልመው ያንተ ፍቅር ለኔ 
የውስጤ ህመም ነው “ያንተስ ?”
ብለሽ ያወራሽው 
ምድርና ሠማይ አብረሽ ቀላቅለሽው
የሰማዩን ዋልታ ንደሽ የሰበርሽው 
በቃላት ድርደራ የትላንቱን ዛሬ 
አፍርሰሽ አፍርሰሽ ይኼው ገነባሽው 
መች ሆነና ገነት ያንቺ ፍቅር ተምሳሌት
መች ሆነና ቀኑ የፍቅር ጥበቡ 
ያንች ፍቅር ምርኩዝ የምላስ ወለምታ 
ከሰው አያገናኝ ስላም የለው ደስታ 
ስለዚህ እኔም ላንቺ አልሆነሽ አንቺም ለኔ አቶሆኚ 
ሆነን አልተፈጠርን ከግራ ጎን አጥንት 
ልንኖር ባንድላይ በአንቺው ሴት`ነት 
ስሜት ሲያስጋልበው ፍቅሬ ለምትይኝ 
የበረደ ለታ ውሻ ብለሽ ጠርተሽ ለምታባርሪኝ ።
ለሜላት እስክንድር ግጥም ምላሽ የተሰጠ! ከዘ.ገ ማለዳ ታይምስ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar