www.maledatimes.com ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት በጀግናዉ አበበገላዉ ላይ በወያኔ ስርአት የተቃጣዉን የግድያ ሴራ አስመልክቶ የተሰጠመግለጫ ጥር 10/2013 ዓ/ም (እኤአ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት በጀግናዉ አበበ ገላዉ ላይ በወያኔ ስርአት የተቃጣዉን የግድያ ሴራ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ ጥር 10/2013 ዓ/ም (እኤአ)

By   /   January 12, 2013  /   Comments Off on ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት በጀግናዉ አበበ ገላዉ ላይ በወያኔ ስርአት የተቃጣዉን የግድያ ሴራ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ ጥር 10/2013 á‹“/ም (እኤአ)

    Print       Email
0 0
Read Time:7 Minute, 14 Second

ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት በጀግናዉ አበበ ገላዉ ላይ በወያኔ ስርአት

የተቃጣዉን የግድያ ሴራ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

ጥር 10/2013 ዓ/ም (እኤአ)

በቅርቡ ጀግናዉ አበበ ገላዉን ለመግደል በህወሀት/ኢህአዴግ የተጠነሰሰ ሴራ በአሜሪካ በFBI መጋለጡንና ተጠርጣሪዎቹም መያዛቸዉንና ምርመራ ላይ መሆናቸዉ ተገልጿል። ይህን እጅግ አሳፋሪ ተግባር የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት አጥብቆ ያወግዛል። የፋሽሽቱና ዘረኛዉ ህወሀት/ኢህአዴግ ስርአት ምርጫ 97ትን ተከትሎ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተረቆ በአዉሮፓ አሜሪካና በሌሎች ሃገሮች ለሚገኙ የኢትዮጽያ ኤምባሲዎች በሚስጢር የተሰራጨው ባለ 52 ገጽ  በአለም ዙሪያ የሚገኙ ተቃዎሚዎችን ለመምታትና ለማዳከም ያወጣዉን እቅድና ዝርዝረ ጉዳዮችን የያዘ የስርአቱ ሰላዮች ሰነድ ሾልኮ በመውጣቱ ለኢትዮጵያኖችና ለአለም አቀፍ ህብረተሰቡ ይፋ መሆኑ የታወሳል። ስርአቱ  በሀገር ውስጥ የሚያደርገውን የሽብርተኝነት ተግባራት በጎረቤት ሀገሮች በማስፋፋት በኬንያ፤ በሱዳን፤ በጅቡቲና ዩጋንዳ በሚገኙ ኢትዮጽያዉያን ስደተኞችና ተቃዋሚዎች ላይ የሚሰራቸዉ ያሸባሪነት፤ የገዳይነትና፤ ከስደተኞች ካምፖችና ከያሉበት አፍኖ በመዉሰድ በኢትዮጵያ እስር ቤቶች እንዲሞቱ የማድረግ ተግባራቶች ያለምንም ተጠያቂነት እየቀጠለ እያለ፤ በታላቋ አሜሪካን ሀገር እጅግ አሳፋሪና ፍፁም የአሸባሪነትና የእብሪት ተግባር ለመፈጸም ሙከራ አድርጓል። ይህም ተግባሩ የስርአቱን ማንነት በገሀድ ያጋለጠ ብቻ ሳይሆን አለም አቀፍ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በሚል ሽፋን በቢሊዮኖች የሚቆጠር የግብር ከፋዮች ገንዘብ ለሚያፈስለት የአሜሪካን ሀገር መንግስት ያለዉን ንቀት በተግባሩ ያረጋገጠ ነው። ለነገሩ ወያኔ/ህወሃት በግድያና፤ የዘር ማጥፋት ፤ እኩይ ተግባሩ በአሜሪካን መንግስት እኤአ ከ 1975 እስከ 1991 ዓ/ም ድረስ በአለም አቀፍ የሽብርተኛ ድርጅትነት መመዝገቡን ለምናስታዉስ ይህ አጸያፊ ተግባሩ ሊገርመን አይገባም።

 

ስለነጻነት የጻፉ ጋዜጠኞችን ሽብርተኛ ናቸዉ በማለት ለረዥም አመታት ያሰረ፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ለመብታቸዉ የሚታገሉትን የሙሰሊም ወገኖቻችንን በሽብርተኝነት ከፈረጀ፤ በደቡብ፤ በአኝዋክ፤ በኦሮሞና በአማራ ህዝብ ላይ የእልቂት ተግባሮችን እራሱ ፈጽሞ የገደላቸዉና ደማቸዉን ያፈሰሰዉ በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ኢትዮጵያዉያንን  ሽብርተኞች እያለ ከሚፈርጅና ህጻን ልጆችን ከሚገድል ስርአት ምን የተሻለ ተግባር ይጠበቃል? ዋናዉ ቁም ነገር ይህ በአሜሪካን ሀገር የተቃጣዉ የንቀት እኩይ የግድያ ሙከራ የአሜሪካን መንግስትን ሰለወያኔ ስርአት ያለዉን አመለካከትና ፖሊሲውን እንደገና በጥሞና እንዲያጤን ማስገደድ አለበት በማለት ባፅንኦት እንለምናለን። ሁላችንም ተቃዋሚ ሀይሎችና በዉጭ ሀገር የምንገኝ ሀገርና ወገን ወዳድ ዜጎችም ይህንን አለም አቀፋዊ የሽብርተኝነት ተግባር የአሜሪካን መንግስት ከስር መሰረቱ በማጣራት አስፈላጊዉን እርምጃ እንዲወስድ ያላሰለሰ ግፊትና ጫና እንድናደርግና የስርቱን ሰላዮች በማጋለጥ መረጃዎችን ለሚመለከተው ከፍል እንድናስተላልፍ እንጠይቃለን። በዚህ አጋጣሚ ከጀግናዉ አበበ ገላዉ ጋር የምንቆምና ለእሱ ያለንን ክብር በድጋሚ በማረጋገጥ ለወያኔ ስርአት የምናስተላልፈዉ ግልጽ መልእክት በአበበ ላይ የተቃጣዉ የፈሪዎች እኩይ ተግባር ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ጀግና አበበዎችን በቅርቡ በመፍጠር ይህንን ጨካኝ ስርአት ጠራርጎ ከሀገራችን ለማስወገድ በቆራጥነት እንደምንታገል እናረጋግጣለን።

 

በጋራ ትግላችን ገዳዩንና ዘረኛዉን ስርአት እንስወግዳለን።

 

የሽግግር ም/ቤቱ አመራር

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on January 12, 2013
  • By:
  • Last Modified: January 12, 2013 @ 10:06 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar