www.maledatimes.com ቤልተዋረደ፥ናባውተሰባበረ /Bel boweth down, Nebo stoopeth/ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ቤልተዋረደ፥ናባውተሰባበረ /Bel boweth down, Nebo stoopeth/

By   /   January 13, 2013  /   Comments Off on ቤልተዋረደ፥ናባውተሰባበረ /Bel boweth down, Nebo stoopeth/

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 46 Second

ቤልተዋረደ፥ናባውተሰባበረ

/Bel boweth down, Nebo stoopeth/

በአንድ ወቅት ገጣሚና ደራሲ በዕውቀቱ ስዩም “ይህ አዲስ አበባ አይደለም፥ይህ የገጠር ቀበሌ ነው” የተሰኘ መጣጥፍ ፅፎ ነበር።እናም በዚያች “ሥርዓት አልበኝነት” በነገሰባት የገጠር ቀበሌ ውስጥ የሂሳብ መምህሩ ከመቅፅበት ተነስተው የስዕል መምህር ሲሆኑ ይታያል።በርግጥም የህግ የበላይነት ባልሰፈነባት በዚያች የገጠር መንደር የሂሳብ መምህሩ የስዕል መምህር መሆን ሳያንሳቸው ተማሪዎቻቸውን ሲያሰቃዩ ይስተዋላል።እንግዲህ እስኪ ይህን ትንሽ ከድርሰትነቱ ወጣ ብናደርገውና የገጠር ቀበሌዋን የሂሳብ መምህር ወደ አዲስ አበባ ብናመጣቸው እንዲሁም እሳቸውም በለመዱት “ህገ-አራዊት” ልመራ ቢሉ በአንፃራዊ ዕድገትና ሥልጣኔ ላይ ያለው የአዲስ አበባ ሰው እንዲህ የሚላቸው ይመስለኛል፦”ይህ የገጠር ቀበሌ አይደለም፥ይህ አዲስ አበባ ነው!”

በተመሳሳይ ወደ መንበረ መንግስት ከመጣ ከሁለት አሥርት አመታት በላይ ያስቆጠረው የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያ የዜጎችን ሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በመጣስ ብዙዎችን ለእስር፣ለእንግልትና ለስደት ከማብቃቱም በላይ በግፍ የገደላቸው ዜጎች ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም።በመሆኑም የወያኔ አገዛዝ ሀገራችን ኢትዮጵያን የፍትህ አልባና የአፈና ተምሳሌት አድርጓት ይገኛል።

ይሁን እንጂ ይህ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን በኃይል የመጨፍለቅ ወያኔአዊ አባዜ ባህር ተሻግሮ በምድረ አሜሪካ በቅጥር ነፍሰ ገዳዮቹ አማካኝነት በጋዜጠኛና አክቲቪስት አበበ ገላው ላይ ሊፈፀም የነበረውን የግድያ ሙከራ የአሜሪካ የፌደራሉ የምርመራ ቢሮ እንዳከሸፈው ኢሳት በጃንዋሪ 08, 2013 የዘገበው።እዚህ ጋር ነው እንግዲህ ለወያኔ “ይህ አዲስ አበባ አይደለም፥ይህ አሜሪካ ነው!” ማለት።

የህግ የበላይነት በሰፈነባት ሀገር በሀይልና በህገ-አራዊት በመነዳት ንፁሃን ዜጎችን ለመግደል መሞከር አለማቀፋዊ አሸባሪነት ነው!!!በህግ ሽፋን አንቀፅ 652/2009ን እየጠቀሰ ንፁሃን ጋዜጠኞችን በአሸባሪነት በመወንጀል ወደ እስር ቤት ሲወረውር የነበረው ወያኔ ዛሬ ቅጥር ነፍሰ-ገዳዮችን በመመልመል በአንዲት ሉዓላዊት ሀገር ውስጥ የሽብር ተግባር ሊፈፅም ሲያሴር መገኘቱ መለስ ዜናዊ በሮናልድ ሬገን ህንፃ ከተዋረደበት የሜይ አስራስምንቱ ስብሰባ ቀጥሎ ወያኔን እርቃኑን ያጋለጠ ሌላ አጋጣሚ ሲሆን ለወያኔ ተጨማሪ የፖለቲካ ኪሳራ፥ለአባላቱም ሌላ ስብራት ሆኗል።ቤል ተዋረደ፥ናባው ተሰባበረ እንዲል ነብይ በመፅሐፉ።

በዚህ አጋጣሚ የወያኔን የሽብር ተግባር በእንጭጩ በመቅጨት የአበበ ገላውን ህይወት ለታደጓት የአሜሪካኑ የፌደራል የምርመራ ቢሮ ሠራተኞች ያለንን አክብሮት እየገለፅን “የወይናችንን ቦታ የሚያጠፉትን ቀበሮዎች፥ጥቃቅኑን ቀበሮዎች አጥምዳችሁ ያዙልን” መልዕክታችን ነው!!!ቸር እንሰንብት።

 

Dawit Fanta

January 13, 2013

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on January 13, 2013
  • By:
  • Last Modified: January 13, 2013 @ 12:43 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar