www.maledatimes.com የቅ/ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልአተ ጉባኤ የዕርቀ ሰላም አጀንዳ ዋና ዋና የውሳኔ ነጥቦች - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የቅ/ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልአተ ጉባኤ የዕርቀ ሰላም አጀንዳ ዋና ዋና የውሳኔ ነጥቦች

By   /   January 16, 2013  /   Comments Off on የቅ/ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልአተ ጉባኤ የዕርቀ ሰላም አጀንዳ ዋና ዋና የውሳኔ ነጥቦች

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 53 Second

በዕርቀ ሰላም ሂደቱ ላይ በማተኰር ጥር 6 ቀን 2005 ዓ.ም የተጀመረው የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አስቸኳይ ስብሰባ÷ ዋነኛ የመነጋገሪያ ነጥብ ባደረገው የዕርቀ ሰላም ሂደት ላይ የደረሰበትን ውሳኔ ዛሬ፣ ጥር 8 ቀን 2005 ዓ.ም በዘጠኝ ሰዓት በሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በትላንትናው ዕለት ለመግለጫው በተዘጋጀው ረቂቅ እና በጋዜጣዊ መግለጫው አሰጣጥ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት ከፍተኛ ውዝግብ ታይቶበት የነበረው ምልአተ ጉባኤው÷ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ እንደሚሰጠው በሚጠበቀው ጋዜጣዊ መግለጫ÷ በሰሜን አሜሪካ በስደት የሚገኙት ብፁዓን አባቶች በፓትርያሪክ ምርጫው እንዲሳተፉ በጊዜ የተገደበ ጥሪ እንዲደረግ መወሰኑ ተሰምቷል፡፡ የልዩነቱ ማእከላዊ ጉዳይ ኾኖ የኖረው የአራተኛው ፓትርያሪክ ወደ አገር የመመለስ ጉዳይ ላይ ቀድሞ ከተወሰነው ውሳኔ የተለወጠ ነገር አለመኖሩ ተመልክቷል፡፡

ትላንት ውዝግብ ቀስቅሶ የነበረው የመግለጫው ረቂቅ÷ ከፓትርያሪክ ምርጫው አስቀድሞ ለዕርቀ ሰላሙ ሥምረት መሠራት የሚገባቸውን ተግባራት እና በውጭ በስደት ያሉ ብፁዓን አባቶችን ተሳትፎ ጨርሶ ከግምት ባለማስገባት ለምርጫው ብቻ ትኩረት በመስጠት የተዘጋጀ ነበር ተብሏል፡፡ በዚህም ሳቢያ የቅ/ሲኖዶሱ የዕርቀ ሰላም ልኡካን ጨምሮ ‹‹በምርጫው ለውጮቹም ጥሪ ተደርጎ በአንድነት እንሳተፍ›› የሚል አቋም የያዙት የቅ/ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል÷ የመግለጫውን ረቂቅ ካቀረቡት ከእነ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ጋራ ከፍተኛ ክርክር ውስጥ ገብተው እንደነበር ተገልጧል፤ በመግለጫው ዝግጅት ንቡረእድ ኤልያስ ኣብርሃ ተሳትፈዋል፤ ዋና ጸሐፊውም ስብሰባውን ጥለው መውጣታቸው ተዘግቧል፡፡ በኀባር የተደረሰበት የስምምነት አቋም ሳይኖር ከቀኑ 11፡00 ላይ በእነ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በጎን ተጠርቶ ነበር ለተባለው ጋዜጣዊ መግለጫ ጋዜጠኞች ተገኝተው የነበረ ቢኾንም መግለጫው በዋና ሳይሰጥ ቀርቷል፡፡

ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ ምልአተ ጉባኤው የልዩነት ነጥቦቹን በማገናዘብ መግለጫውን ዳግመኛ አዘጋጅተው እንዲያቀርቡ ሦስት ብፁዓን አባቶችን (ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም) የመደበው፡፡ ከዛሬው መግለጫ መካተተቸው ከተገለጹት ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡-

  • በስደት የሚገኙት አባቶች በምርጫው እንዲሳተፉ በጊዜ የተገደበ ጥሪ ይደረግላቸዋል
  • ብፁዓን አባቶች ለጥሪው ምላሽ እስኪሰጡ የምርጫው ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ይቆማል
  • ለጥሪው አዎንታዊ መልስ ተገኝቶ በአንድነት ወደ ምርጫው ከተገባ የዕርቀ ሰላም ሂደቱ ፍጻሜ ይኾናል፤ የፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንቡና አስመራጭ ኮሚቴው ዳግመኛ በጋራ ሊታይ ይችላል
  • የቅ/ሲኖዶሱን ጥሪ የሚያደርሱ ሽማግሌዎችና ታዋቂ ሰዎች ይመደባሉ የሚሉት ይገኙባቸዋል፡፡

የመግለጫውን ሙሉ ይዘት እንደደረሰን እናቀርባለን፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on January 16, 2013
  • By:
  • Last Modified: January 16, 2013 @ 2:07 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar