www.maledatimes.com አንድ ማስታወሻ ለጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ መስፍን ነጋሽ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አንድ ማስታወሻ ለጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ መስፍን ነጋሽ

By   /   January 19, 2013  /   Comments Off on አንድ ማስታወሻ ለጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ መስፍን ነጋሽ

    Print       Email
0 0
Read Time:9 Minute, 42 Second

ይህ ጽሁፍቀደም ብሎ በተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀርቦ በአንባብያን ዘንድ ከፍተኛ ተነባቢነትን እንዳገኘ ከማለዳ ማህደር ውስጥ ብቻ ካነበቡት መረዳት ይቻላል ሆኖም ግን ወቅቱ የአፍሪካ እግር ኳስ ጨዋታ የሚካሄድበት ወቅት ስለሆነ እኛም እስኪ የኳስ ባለ ውለታችን ደምሴ ዳምጤን ለማስታወስ ይረዳን ዘንድ ጽሁፉን እንደገና ማተም እና በድጋሚ እሱን ከዚህ እግርኳስ ጨዋታ ጋር አብሮ በእዝነ ህሊናችን እንድናስበው ወደድን ስለሆነም ሁላችንም ባለንበት የህሊና ጸሎት እያደረግን እንድናስበው ቸሩ አምላካችን ይርዳን ለሃገራችን መልካም የዋሉትን ስማቸው ሁሉ በማወደስ እና በመዘከር ማመስገናችንን እንቀጥላለን ብንንችል በህይወት እያሉ መዘከር ካልቻልን ደግሞ ስራቸውን እያነሳን ብናወድሳቸው ምን ይለናል ? ስለዚህ ይህንን ጽሁፍ እንዲያነቡ ማለዳ ታይምስ መዘክሯን ለእርስዎም ትዘክርዎታለች »እኔ እድሜ የደምሴን ያህልአገራዊ የስፖርት ስሜትን፣ በተለይ እግር ኳስን ወደ ልባችን ያቀረበ ጋዜጠኛ አልነበረም።እንደዛሬው ኢንተርኔት መገልበጥ ማእረግ በማያሰጥበት ዘመን። በሳምንት ሁለትና ሦስትቀን ስታዲየም በምገባበት፣ ሁለቱን ሙሉጌታዎች፣ እነሚሊዮን በጋሻውን፣ እነቸርኬን(ጊዮርጊስ)፣ እነሙሉዓለም እጅጉን (ጦሩ)፣ እነአብዲን (መድን)፣ እነአፈወርቅን (እርሻ)፣ ያደሞ የአየር ኀይሉ አጥቂ ማን ነበር? … ረሳሁት ማለት ነው? (ይልቅ ተከላካያቸው መሰለ፣ጆን ቴሪን ቁጭ ነበር)፣ ከዛ ደሞ … ይህ ሁሉ ሲሆን ብቸኛው የስፖርት መረጃ ምንጫችንደምሴ ነበር፤ እርግጥ ሌሎችም ጋዜጠኞች ነበሩ በተለይ እነ … ማነው … ይንበርበሩመሰለኝ። ቢሆንም ደምሴ የተለየ መስህብ ነበረው።

ከሁሉም የማልረሳው የደምሴ ገጠመኝ በ1980 የምስራቅና መከካለኛው አፍሪካንዋንጫን ያሸንፍን (የበላን) ጊዜ የሆነው ነው። ብዙ ሰው የሚያስታውሰው ጨዋታውበፍጹም ቅጣት ምት ማለቁንና ዳኛቸው ደምሴ (ደምሴ “ዳኙ” እያለ ያቆላመጠው፣ አመለሸጋው ተጫዋች) የመጨረሻውን ምት አስቆጥሮ ማሸነፋችንን ነው። ለፍጹም ቅጣት ምትየደረስነው ግን 1 ለ 0 ስንመራ ቆይተን ባለቀ ሰዓት ባገባነው ጎል ነበር። ታዲያ ብዙተመልካች በመበሳጨቱ ጨዋታው ሳይጠናቀቅ መውጣት ጀምሮ ነበር። ለዋንጫመድረሳችን የፈጠረው ስሜት ከመናሩ የተነሣ፣ በገዛ ሜዳችን ሌላ ሲሸለም አናይም ብለውነው። ቀኑ ገብርኤል ነበር፤ ብዙ ሰው ተስሎ እንደነበርም አስታውሳለሁ።

እኔ መጨረሻውን ሳናይ አንሄድም ካሉት ወገን ሆኜ ቆየሁ፤ ጥቂት ጓደኞቼ ግንለመውጣት ጉዞ ጀመሩ፤ አንዳንዶቹም ከወጡ ቆዩ። በመጨረሻ (በትክክል አስታውሼውከሆነ) “ሙሉዓለም ያሻማትን፣ ገ/መድኅን ኀይሌ በጭንቅላት ገጭቶ ከመረብ አዋሃዳት”የምትለዋ ዝነኛዋ የደምሴ የምስራች መጣች። መቼም በዚያ ደቂቃ በስታዲየሙ የተሰማውንድምጽ መቼም አልረሳውም፤ እስከዛሬም አቻ ወይም መግለጫ አላገኘሁለትም። “ተመልካቹጮኸ” ማለት ተርታ ንግግር ነው፤ ቋንቋ ከስሜት ጠቦ የሚገኝበት።

ለማንኛውም ጎሉ ገብቶ፣ እኩል ሆነን፣ ለፍጹም ቅጣት ምት በቅተን፣ አሸነፍን።መንጌም ደስ ብሏቸው ዋንጫውን ለአገራቸው ልጆች ሰጡ፤ የተሸናፊዎቹ “አባት”ና አገርበኋላ መጠጊያ እንደሚሰጡዋቸው እንዴት ይጠርጥሩ። (እኛ ሰፍር ስታዲየም ሊሰራ ቃልየተገባውም ያን ጊዜ ነበር መሰለኝ።) ታዲያ ጨዋታው ሳያልቅ የወጣው አንዱ የት/ቤትጓደኛችን ጎሉን የሰማው ታክሲ ውስጥ እንደገባ ኖሯል። ግን በደንብ አልሰማም። ከዚያ”የውይይቱን” ወያላ ይጠይቀዋል፤ “ማን አገባ በናትህ?” ወያላው መለሰ “ደምሴ ዳምጤ”።እሱ ገ/መድኅንን የት ያውቀዋል፤ ደምሴ ዳምጤን እንጂ።
በ60 ዓመት መሞት እኩለ ቀን አለፍ እንዳለ እንደመሞት ነው። እርግጥ ደምሴ አመሻሽ ላይበ90 ቢሞትም ኖሮ ማዘናችን አይቀርም ነበር። ለማንኛውም፣ ድሃዋ አገር ከሰጠችውያላነሰ፣ መልሶ ሰጥቷት ስለሞተ ሕይወቱ የባከነ አልነበረም።
ደምሴ፣ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነትን እንደጦር በሚፈሩ ሁለቱ አምባገነኖች ዘመን በስፖርትጋዜጠኝነት ሰርቷል። ምን አጋጥሞት ይሆን? የጫረው ነገር ይኖር ይሆን? ደምሴ ያቺየገ/መድኅን ጎል ምንጊዜም ያንተ መዘከሪያ ናት፤ የታክሲ ረዳቱ ያጸደቀልህን ጎል አጽድቄአስታውሳለሁ፤ ከልጅነት የኳስና የስታዲየም ጓደኞቼ ጋራ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on January 19, 2013
  • By:
  • Last Modified: January 19, 2013 @ 11:04 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar