www.maledatimes.com ጎል ባይቆጠርም የትናንት ምሽቱ የሞሮኮና የአንጎላ ጨዋታ ጥሩ ነበር።2 ለ 2 የተለያዩት ዲሞክራቲክ ኮንጎና ጋናም ጥሩ ጨዋታ አሳይተዋል።ደረጀ ሃብተወልድ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ጎል ባይቆጠርም የትናንት ምሽቱ የሞሮኮና የአንጎላ ጨዋታ ጥሩ ነበር።2 ለ 2 የተለያዩት ዲሞክራቲክ ኮንጎና ጋናም ጥሩ ጨዋታ አሳይተዋል።ደረጀ ሃብተወልድ

By   /   January 20, 2013  /   Comments Off on ጎል ባይቆጠርም የትናንት ምሽቱ የሞሮኮና የአንጎላ ጨዋታ ጥሩ ነበር።2 ለ 2 የተለያዩት ዲሞክራቲክ ኮንጎና ጋናም ጥሩ ጨዋታ አሳይተዋል።ደረጀ ሃብተወልድ

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 1 Second

ጎል ባይቆጠርም የትናንት ምሽቱ የሞሮኮና የአንጎላ ጨዋታ ጥሩ ነበር።2 ለ 2 የተለያዩት ዲሞክራቲክ ኮንጎና ጋናም ጥሩ ጨዋታ አሳይተዋል።
አንዲት የልጅነት ማስታወሻ
መቼም ኢትዮጵያውያን ስለ እግር ኳስ ሲወራ፦<< ሞሮኮና ጊኒ>> አዲስ አይሆኑብንም። ከልጅነታችን ጀምሮ ቴሌቪዥን እንዳሁኑ በስፋት ባልነበረበት ጊዜ የራዲዮ የስፖርት ጋዜጠኞቻችን እነዚህን አገሮች በአዕምሯችን ቀርጸውብናል።ልጅ ሆነን ኳስ ልንጫዎት ስንቧደን እንኳ ብዙውን ጊዜ ለቡድን አባቶቻችን የምናደርገው ምርጫ ፦<<ከጊኒና ከሞሮኮ>>የሚል እንደነበር ትዝ ይለኛል።
ይህን በተመለከተ ከማስታውሳቸው ነገሮች አንዱ ከድር የተባለ የኳስ ፍቅር እንጂ ችሎታው የሌለው የሰፈራችን ልጅ እንደተኛ ሌሊት ፦<< ወይኔ! ወይኔ !አቤት ጨዋታ!አቤት ጨዋታ!..” እያለ ይቃዣል። እናቱም ደንገጥ ብለው ፦”ምንድነው የምትለው?ምን እያየህ ነው አንተ ?” ይሉታል። እሱም ፦” ጊኒና ሞሮኮ ሲጫዎቱ እያየሁ ነው” አላቸው።ወንድሞቹ ጠዋት ስለ ቅዠቱ ለሰፈሩ ልጅ ሁሉ አውርተውበት ሢሳቅበት ሰነበተ።
ከድር ፤ማናቸውም የታዳጊዎችን ተሳትፎ በሚጠይቁ ነገሮች ላይ ቀድሞ መገኘት የሚወድ ልጅ ነበር።ለምሳሌ የቀበሌ ታዳጊ ኪነት ቡድን ውስጥ ተወዛዋዥ ሆኖ በፍላጎቱ አንድ ዓመት ሠርቷል። ከዚያም የዓለም ዋንጫ ሰሞን ኪነቱን እርግፍ ትቶና ሙሉ ትጥቅ ቤተሰቦቹን አስገዝቶ ሌሊት እየተነሳ ኳስ መለማመድ ጀመረ።የሰፈራችን የታዳጊ ቡድን ሊቋቋም የተጫዋቾች ምርጫ ሊደረግ ሲል ከ 30 የሚበልጡ ታዳጊዎች ተሰበሰቡ። ከነሱ መካከል የሚፈለጉት 16 ሲሆን 14ቱ የሚቀነሱ ናቸው።ለምርጫ ከሄድነው 30 ልጆች አንዱ ከድር ነው።
ልምምዱ ተጀመረ። የመጀመሪያው ልምምድ ክብ ሠርተን እየሮጥን አሰልጣኛችን (መራጩ) መሀከል ላይ እንደ በረኛ ሆኖ በእጅ የሚሰጠንን ኳስ በቴስታ፣አለያም በደረት አቁሞ በእግር፣ አለያም በጉልበት፣ መልሶ መስጠት ነው።ሁሉም እንደዚያ እያደረገ የከድር ተራ ደረሰ።… እንዳልኳችሁ ክብ ሰርተን ዱብ ዱብ እያልን ነው… አሰልጣኙ ኳሷን ወደ ከድር ወረወሩ።ኳሷ ለከድር ከጭንቅላቱ ዝቅ ብላ፤ከ ጉልበቱ ደግሞ ከፍ ብላ መጣችበት። በደረት ማቆም ደግሞ ከድር ጋር አይሞከርም። ግራ እንደመጋባት ይልና በቴስታም፣በጉልበቱም ሊመታ እኩል ጭንቅላቱን ዝቅ፤ጉልበቱን ከፍ ሲያደርግ.. በጉልበቱ የራሱን አፍንጫ ደህና አርጎ አቀመሰው። ኳሷንም ሳያገኛት በመሀከል ሾለከች።ኪነቱን ጥሎ የመጣው ከድር በጣም አመመውና በራሱ ጉልበት የመታውን የራሱን አፍንጫ በእጆቹ ይዞ ቆመ። አሰልጣኛችንም ጨመሩለት፦”አንተ ምን ልታ’ረግ እዚህ መጣህ? ሂደህ እዛው እስክታህን ውረድ!” በማለት። ሁላችንም ሳ…ቅ… በሳቅ ሆንን። በዚህ ሁኔታ ከድር የመጀመሪያው ተቀናሽ ሆነ።
ከዚያም ጠቅላላ ኳስ መለማመድ አቆመ። በሳምንቱ የቀበሌያችን ታዳጊ ኪነት ቡድን ባሳየው አንድ ዝግጅት ላይ አፍንጫውን በፕላስተር ለጥፎ እስክስታ ሲል ታዬ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on January 20, 2013
  • By:
  • Last Modified: January 20, 2013 @ 12:04 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar