www.maledatimes.com የኤርትራ የጸጥታ ሃይሎች ሃገሪቱን ተቆጣጥረዋል ሁለት ዔታማዦር ሹሞች በስናይበር ተገድለዋል ።”አልጀዚራ የአረብኛው ክፍል” - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኤርትራ የጸጥታ ሃይሎች ሃገሪቱን ተቆጣጥረዋል ሁለት ዔታማዦር ሹሞች በስናይበር ተገድለዋል ።”አልጀዚራ የአረብኛው ክፍል”

By   /   January 21, 2013  /   Comments Off on የኤርትራ የጸጥታ ሃይሎች ሃገሪቱን ተቆጣጥረዋል ሁለት ዔታማዦር ሹሞች በስናይበር ተገድለዋል ።”አልጀዚራ የአረብኛው ክፍል”

    Print       Email
0 0
Read Time:11 Minute, 1 Second

የኤርትራ የጸጥታ ሃይሎች ሃገሪቱን ተቆጣጥረዋል ሁለት ዔታማዦር ሹሞች በስናይበር ተገድለዋል ።”አልጀዚራ የአረብኛው ክፍል”

በዛሬው እለት በዋለው ከፍተኛ የጦርነት አመሳ ከተማይቱ እረፍት ያጣች ቢሆንም ሁለት ኤታማዦር ሹሞች መገደላቸውን የአልጀዚራ የአረብኛው ክፍል አትቶአል በሌላም በኩል የተቃዋሚ አንጃዎች ከሚጠይቁት ጥያቄዎች ውስጥ ዋነኛው ሆኖ የተወሰደው የህሊና እስረኞች ይፈቱ የሚለው ዋናው አላማቸው ይሁን እንጂ ቀጣዩ ግን ከተማዋን ከተቆጣጠሩ በኋላ ወደ በትረ ስልጣን ለመቆጣጠር መፈለጋቸውን ተጠቁሞአል ።በተለይም በመንግስት ስር የሚተዳደረውን ዋነኛ  የመገናኛ ብዙሃን ከተቆጣጠሩ በሁዋላ ማንኛውም መረጃ ከሃገሪቱ እንዳይሾልክ በማገድ በቁጥጥራቸው ስር ማዋላቸውን በተለያዩ አለም አቀፍ መረጃ መረቦች ውስጥ እየተላለፈ መሆኑ ይታወቃል ።የአለማቀፍን ቀልብ የገዛው ይሄው የመፈንቅለ መንግስት ሂደት ጅምሩ እስረኞችን የማስፈታት ይሁን እንጂ በቀጥጣ የኢሳያስ አፈወርቂን ስርአት  ማስወገድ አስፈላጊ ነው ሲሉ የተቃዋሚ ሃይሎች ይገልጻሉ ።

እንደ ውጭ መገናኛ ብዙሃኖች ምንጭ መሰረት የታጣቂ ሃይሎች የመገናኛ ሚንስትሩን በማስገደድ የፖለቲካ እስረኞችን በአስቸኳይ ጥሪ እንዲያደርግ ካደረጉ በሁዋላ መረጃ ማእከሉ እንዲዘጋ አድርገዋል ሲሉ የሃገሪቱ ሰለላ ዋና መሪ ተናግረዋል።መረጃ ማእከሎቹን አስገድደው ጥሪ እንዲያደርጉ ታዘዋል ይህንንም በበቂ ሁኔታ አድርገው ለጊዜው ከአገልግሎት ውጭ ሆነዋል ሲሉ የተደመጡት እኝሁ የሰለላ ዋና አዛዥ “የ ኤርትራ መንግስት እስረኞቹን የመፍታት ግዴታ አለበት ሲሉ ደግሞ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ አመራሮች ገልጸዋል።የተለያዩ ታንኮች በሚንስትሮች መስሪያቤት ከበው ይገኛሉ በማለት ደግሞ የተለያዩ የውጭ አምባሳደሮች ለሃገሮቻቸው ሚዲያዎች እና ለመንግስቶቻቸው በስልክ ማሳወቃቸውን ከአልጀዚራ ጣቢያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል በተለይም የአሜሪካ መንግስት ከአስመራ ምንም መግለጽ ባንችልም በሚንስትር መስሪያቢእቶች ላይ ከባድ መሳሪያዎች ተደቅነው በዙሪያዎቻቸው ሰራዊቶች ከበዋቸው ይገኛሉ ሲሉ አሳውቀዋል ።

በኤርትራ መንግስት ላይ የመጣው ነገር ምንም ይሁን ምን አጋጣሚ እና  ምንም አመላካች ባይሆንም ይህን ሁሉ ጊዜያት ሲሚሩ የነበሩት በተለይም ለሁለት ትውልድ ርዝመት የቆዩትን የ66 አመቱን የኤርትራውን መሪ ኢሳያስ አፈወርቂን ጊዜ አልባ እንደማይሆንባቸው ግልጽ ነው ሲሉ ይናገራሉ ።ከ20 አመታት በላይ ለዘመናት አብረዋት ከኖሩት የቀድሞ ዜጎቿ ጋር ማለትም የኢትዮጵያን ወገኖች ጋር ከተለያየችበት የነጻነት ዘመን ጀምሮ የኤርትራው መንግስት በአጠቃላይ በሰበአዊ መብት ገፈፋ እና ዜጎቻቸውን ያለአግባብ በማሰር እና በመግደል እንዲሁም የመገናኛ ብዙሃንን በማፈን በሚል በአለም አቀፉ የሰበአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂውማን ራይት ዎች እና እንዲሁም በጋዜጠኞች ተከራካሪ ኮሚቴ ሲፒጄ በየጊዜው ወቀሳ ሲሰነዘርባቸው ሰንብተዋል ።በአፍሪካ ጋዜጠኞችን በማሰር ግንባር ቀደምነቱን ሲይዙ ኢትዮጵያ ትከተላለች ።የ እንግሊዙጋዜጠኛ ሚሼላ ሮንግ እንደተናገሩት ከሆነ ደግሞ ምንም እረፍት አልባ ያልሆኑ ሰራዊቶች በከተማዋ ላይ ነግሰዋል ሲሉ ተደምጠዋል ስለዚህ ለአቶ ኢሳያስ ከፍተኛ የሆነ አበሳ ይገጥማቸዋል ስለሆነም ከአርሚው ጎን ሆኜ ልመጣ እችላለሁ “በኤርትራ ላይ ምን እየተፈጸመ ነው በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ነገር ሁሉ መመልከት ይገባናል ስለሆነ የአውሮጵውያኑ እና አሜሪካውያኑ አይኖቻቸውን በቅርበት ማሳረፍ ይገባቸዋል ሲሉ እንግሊዛዊቷ ጋዜጠኛ ሃሳበቸውን አስምረውበታል ።

ሰላም ሰለሞን የተባለች የኤርትራ ተወላጅ በአሜሪካ ዜግነት ያላት እንደተናገረችው ከሆነ በአጠቃላይ የአጠቃላይ የአስመራ ሰራዊት  በተጠንቀቅ ያለ ሰራዊት ከ200.000 እስከ 300.000 እንደሚጠጋ ገልጻ፣እየተደረገ ያለው በሚስጥር ካልሆነ በቀር ምንም ምልክት ምን እንደሚመስል በሃገሪቱ ላይ  ምን እንዳለ የሚያሳይ ነገር ለማወቅ ያስቸግራል ብላለች ።ምንም የተኩስ ልውውጥ በመንግስትም ሆነ በተቃዋሚዎች ጎራ የለም ሰላማዊ ሁኔታ ነው ያለው ያለችው ሰላም ሰለሞን  ሆኖም ግን ለዚህ ጉዳይ ላይ በትኩረት እየመጡ ያሉት በውጭ የሚገኙት የተቃዋሚ ሃይሎች እራሳቸውን በማጠናከር ሳይሆን አይቀርም ሆኖም ግን የህዝቡ እና ሰራዊቱ በጋራ በመሆን የተቃዋሚው ሃይል ሰራዊት በቁጥጥር ስር አውለውታል ስትል ገልጻለች ።ምንም  ሃይል ያላቸው አይመስልም ስትል አክላለች ።

የዩናይትድ ኔሽን ባለፈው አመት እንደገለጸው ከሆነ ከ5.000 እስከ 10.000 የሆኑ የፖለቲካል እስረኞች እና ሰበአዊ መብታቸው የተገፈፉ ዜጎች በተለያዩ የአስመራ የእስርቤት ካምፖች ውስጥ መታጎራቸውን ገልጦአል ።አብዛኞቹም በግፍ እንደሚገደሉ የአለአግባብ ቶርች እንደሚደረጉ በሪፖርቱ ያሳወቀው ይሄው ድርጅት በቀይ ባህር ዳርቻ ላይ አብዛኞቹን እስረኞች በ እስር ግዞት ውስጥ እንደሚያሰቃዩአቸው ሃተታውን ያትታል።

በኢትዮጵያ ድንበር በስደት ላይ የሚገኙት የ ኤርትራ ዜግነት ያላቸው ሰዎች ደግሞ እንደሚሉት ከሆነ ፣በኢኮኖሚም ሆነ በምንም ነገር ሃገሪቱ እደገቷ ወደ ኋላ የቀረ ነው ስለዚህ የኢኮኖሚያችን ጉዳይ በጣም አሳፋሪ ነው ሲሉ ስደተኞች አክቲቪስቶች ይጠቁማሉ ።

አቶ አረአርያ ደስታ የዩኤን ቋሚ መል እክተኛ ከአስመራ እንዳሉት ከሆነ  ምንም ችግር የለም ሁሉም ነገር ጸጥ እንዳለ ነው ነገር ግን ሁሉንም ያሉብንን ችግሮች በሰላማዊ ሁኔታ ሊፈቱ ይችላሉ ሁሉም ነገር ለበጎ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

 

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on January 21, 2013
  • By:
  • Last Modified: January 21, 2013 @ 8:44 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar