www.maledatimes.com በየመን ስደተኛው ላይ ግፉ ቀጥሏል፡፡ ብልቱን የተቆረጠ፣ አይኑ የጠፋ፣ጆሮው የተቆረጠ፣ እግር እጃቸው የተሰበረ ልጆች ሀረጥ IOM ካምፕ ውስጥ ያለ ህክምና ይሰቃያሉ በግሩም ተ/ሀይማኖት - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በየመን ስደተኛው ላይ ግፉ ቀጥሏል፡፡ ብልቱን የተቆረጠ፣ አይኑ የጠፋ፣ጆሮው የተቆረጠ፣ እግር እጃቸው የተሰበረ ልጆች ሀረጥ IOM ካምፕ ውስጥ ያለ ህክምና ይሰቃያሉ በግሩም ተ/ሀይማኖት

By   /   January 30, 2013  /   Comments Off on በየመን ስደተኛው ላይ ግፉ ቀጥሏል፡፡ ብልቱን የተቆረጠ፣ አይኑ የጠፋ፣ጆሮው የተቆረጠ፣ እግር እጃቸው የተሰበረ ልጆች ሀረጥ IOM ካምፕ ውስጥ ያለ ህክምና ይሰቃያሉ በግሩም ተ/ሀይማኖት

    Print       Email
0 0
Read Time:16 Minute, 2 Second

ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች በአረብ ሀገር…
በየመን ስደተኛው ላይ ግፉ ቀጥሏል፡፡ ብልቱን የተቆረጠ፣ አይኑ የጠፋ፣ጆሮው የተቆረጠ፣ እግር እጃቸው የተሰበረ ልጆች ሀረጥ IOM ካምፕ ውስጥ ያለ ህክምና ይሰቃያሉ
በግሩም ተ/ሀይማኖት
ዕለት ከዕለት በየመን ኢትዮጵያዊያን ስደተኛ ላይ የሚሰራው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊትና ግፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ወደ ሀገሬ የገቡት በየመን በኩል ነው እና ወደ ሀገራቸው ሳይሆን ወደ የመን ነው የምመልሰው ብሏል፡፡ ማለት ብቻም አይደለ አፍሶ እያመጣ የመን መሬት ቀይ ባህር ዳርቻ እየጣላቸው ነው፡፡ ከሳዑዲ ተመላሾቹን ገንዘብ ይዘዋል፡፡ ባይዙ እንኳን እዛ ካለ ጓደኛ ወዳጅ ዘመድ ያስልካሉ ብለው እያፈኑ ማሰቃየቱን በግሩፕ የተደራጁት የመናዊያን ገፍተውበታል፡፡ ከሳዑዲ ተመላሾቹ ለማምለጥ ሲሮጡ በጥይት ከመምታት ጀምሮ በመኪና ሁሉ እየገጩ በመግደል መጫዎቻ አድርገዋቸዋል፡፡ ይህን ስራ በትብብር አብረዋቸው የሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን እንዳሉ ያነጋገርኳቸው ልጆች ነግረውኛል፡፡
እንዲያውም ኢትዮጵያዊያኑ ሆን ብለው ሳዑዲ በመግባት ይታሰሩና ሲመለሱ የት የት ጋር እንደደረሱ ደበቅ ብለው እየደወሉ ለታጣቂዎቹ ይነግሩዋቸዋል፡፡ ተዘጋጅተው ይጠብቃሉ፡፡ ያናገርኩት ልጅ ሲነግረኝ..‹‹ከሳዑዲያ እስር ቤት ከአራት መቶ በላይ ነን የተመለስነው፡፡ አብረውን ከነበሩት ሁለቱ ደበቅ እያሉ ሲደውሉ ገንዘብ ሊያስልኩና ሊመለሱ ነበር የመሰለን፡፡ በኋላ ግን አፋኞቹ ሲመጡ አወቁባቸው እና ሁለት ትግሬ ልጆች ተናደው ሊመቷቸው ሲሉ ከአፋኞቹ መኪናው ላይ መሳሪያ አንስተው ታጠቁና እንዳትንቀሳቀሱ አሉን፡፡ ስንበታተን የመናዊያኑ ወደ ሰማይ ሲተኩሱ ኢትዮጵያዊያኑ ወደ እኛ ተኩሰው ብዙ ሰው አቆሰሉ፣ ገደሉ፡፡ የመናዊያኑ አፋኞች የደረሱበትን ያዙ፡፡ በመኪና እያባረሩን ያቃታቸውን እየገጩ ጥለው ሄዱ፡፡..›› ብሎኛል፡፡
ከባህር ወርደው ታግተው እህታቸውና ወንድማቸው ከሳዑዲ አረቢያ ገንዘብ ልከውላቸው የተለቀቁ ሶስት ልጆች ሀረጥ ካምፕ ገብተው እንደነበር ስለነገሩኝ ስላለውን ሁኔታ ጠየኳቸው፡፡ ‹‹ብልቱን የተቆረጠ፣ አይኑ የጠፋ፣ጆሮው የተቆረጠ፣ እግር እጃቸው የተሰበረ፣ የተደፈሩ፣ በመኪና ተገጭተው የቆሰሉ..ልጆች IOM ካምፕ ውስጥ ያለ ህክምና ይሰቃያሉ፡፡…›› አሉኝ፡፡ እንዲያውም ብልታቸውን ከተቆረጡት ሁለት ልጆች አንደኛው ከጥቂት ሳምንታት በፊት እዛው ካምፕ ውስጥ ራሱን ሰቅሎ እንዳጠፋ ነገሩኝ፡፡ ይህ ሁኔታ ምን ያህል እውነት እንደሆነ እዛ ያለ የማውቀው ሰው ደውዬ ጠየኩት፡፡
‹‹እውነታው የነገሩህ ነው፡፡ ጉዳት ከደረሰባቸው ውስጥ በሞባይል እያናገርኩ የቀዳኋቸው እና ፎቶ ያነሳኋቸው አሉ፡፡ ኢሜልህን ስጠኝ እልክልሀለሁ፡፡ በጣም ዘግናኝ ነው፡፡ እንዲያውም የሚገርምህ ነገር ካምፑ ውስጥ ያሉት በመቶ ቤት ሳይሆን በሺህ የሚቆጠሩ ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው፡፡ ያለ ህክምና ያለ ምግብ እንዲሁ ተቀምጠዋል፡፡..›› ሲለኝ አንድ ሾፌር የመናዊያ ሀረጥ ደርሶ ሲመለስ ያለኝ ትዝ አለኝ እና ጠየኩት፡፡ ካምፕ ውስጥ ያሉት IOM ምግብ አልቻልኩም ከአቅሜ በላይ ነው በማለቱ በርሃብ አልቀዋል፡፡ ከተማ ውስጥ እየለመኑ ነዋሪው ተማሮባቸዋል፡፡ ምግብ ቤት ገብተህ አዘህ ልትበላ ስትል ከየት መጡ ሳይባል ኢትዮጵያዊያኑ ወረውህ ምግብህን ይበላሉ ይባላል፡፡ ይህን ከአምስት ወር በፊት ወደዛ የመጣሁ ጊዜ አይቻለሁ፡፡ አሁን ግን ብሶባቸው ሆቴሎች በራቸው ላይ ዱላ የያዘ ሰው ለማቆም ተገደዋል፡፡ በርሃብ መንገድ ላይ ሁሉ ወድቀው ይታያሉ ብለውኛል እውነት ነው?›› አልኩት፡፡
‹‹ይሄ እውነት ነው፡፡ አንተ ከመጣህበት ጊዜ አሁን በጣም የከፋ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት መረራቸው ምንም የሚሰጣቸው ነገር የለም፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ዛሬ በ28/1/2013 ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ፡፡ መፍትሄ ይሰጠን ወደ ሀገራችን መልሱን ነው ሰልፉ..›› ሲል ትላንትና አረጋግጦልኛል፡፡ በወቅቱ ይሄን ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠው በማለት ለVOAው ጋዜጠኛ አሉላ ከበደ ደውዬ ስልኩ አልነሳ ቢለኝ መልዕክት ጽፌ ላኩለት፡፡ ለDW ሬድዬ የሳዑዲ አረቢያ ዘጋቢ ነብዩ ሲራክም መልዕክት ላኩኝ፡፡ በእርግጥ ነብዩ በኢሜል ለላኩለት መልዕክት ወዲያው ምላሹን ጽፎልኛል፡፡ በሬድዬው ባይችል ብዕሩ ስለሚዳስሰው እጠብቃለሁ፡፡ ሀረጥ ውስጥ ያሉ ቁስለኛ ስደተኞች ከሳዑዲ የተመለሱ ብቻ አይደሉን እንዲያውም አብዛኛው ከባህር ሲወርዱ በተደራጁት አፋኞች ተይዘው ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው፡፡ ከአመት እና ከዛ በላይ የቆዩ ከአራት ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን አሉ፡፡
ባለፈው ጊዜ በገመድ ታንቀው ተደብድብው የመጡት ሁለት ልጆች እንደነገሩኝ ከሆነ ገና አፋር ሰመራ ደላላው ቤት እያለን ሚስቱ እናንተ እኮ እቃ ናችሁ፡፡ የኮንትሮባንድ እቃ!..ለምን ትሄዳላችሁ ስትል እንድንመለስ ነግራን ነበር፡፡ አልገባንም ቢገባንም ለመመለስ አልፈለግንም፡፡ በኋላ በእስር በስቃይ እያለን ‹‹ለእየአንዳንዳችሁ በጀልባ ላመጧችሁ የሳዑዲ 200 ሪያል ከፍለናል፡፡ ስለዚህ ብር ሳይላክላችሁ አንለቃችሁም እያሉ ነው ያሰቃዩን ብለውኛል፡፡ የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ ተምረው ዲግሪ፣ ዲፕሎም ይዘው ስራ አጥተው ስደትን ለመሞከር የወጡ ሁሉ አሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ታደሰ አብሯቸው የነበረ የትግራይ ልጅ ነው፡፡ የ2004 አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ዲግሪ ምሩቅ ነው፡፡ ሰውነቱ ጥሩ የስፖርተኛ አይነት ፈርጠም ያለ ስለሆነ ይማታ ይሆናል ብለው ፈሩት፡፡ ቀደመው እጅ እና እጁን እግርና እግሩን በብረት ሰባበሩት፡፡ ሽንት ቤት ሲሄድ እየተንፏቀቀ ነበር፡፡ ሳዑዲ ዘመዶች ስላሉት 1000 የሳዑዲ ሪያል ላኩለት ሲለቁት እንዴት ይሂድ በጣም ሲሰቃይ ለሽንት እንኳን ደግፌ የምረዳው እኔ ነበርኩ ሲል ወርቅዬ የተባለው ልጅ ነግሮኛል፡፡
አሁን ያለው አማራጭ አንድ እና አንድ ብቻ ነው፡፡ እነዚህን ወገኖች በምን መንገድ እንርዳ? መሰባሰብ ግድ ይላል፡፡ ባለፈው ጽሁፌ ላይ ቴዲ ምስጋናው የተባለ ውዳጄ…
Teddy Mesganaw
እንደተረዳሁት ከሆነ በመደራጀት ለውጥ እንደሚመጣ ብዙ ሰው ያምናል ግን ችግሩ ያለው ማነው የሚያደራጀን? እንዴትስ ብለን ነው የምንደራጀው? ተደራጅተንስ ምንድን ነው የምናደርገው? የሚሉት ጥያቄዎች ይመስለኛል ።ግን እስከመቼ እንዲህ ወገን እየተሰቃየ እኛን ሌላ ሰው እስኪ ያስተባብረን እስኪቀሰቅሰን እንጠብቃለን? ራሳችንን አሳንሰን እያየን ገና ዶክተሮቹ እና ፕሮፌሰሮቹ መጥተው በልመና እስኪያስተባብሩንስ ለምን እንጠብቃለን? ሌላው ይቅርና እኛ ከላይ እስከታች comment የሰጠነው እና ስሜታችን የተነካው ወገኖች በሙሉ ከንፈር ከመንከስ አለፍን ለተግባር ከተዘጋጀን ለውጥ ማምጣት እንችላለን። እንዴት? ለሚለው ግን መጀመሪያ እኛው እራሳችን መደራጀት እና መነጋገር አለብን።
የሚል መልዕክት አስፍሮልናል፡፡ 100 በመቶ ያስማማኛል፡፡ፕሮፌሰሮቹ እስኪያደራጁን ላልከው ትክክል ነህ እነሱ እኮ ጠረጴዛ ይዘው ማውራት ካልሆነ ሲሰሩ ያየነው ነገር የለም፡፡ ለምን አንተዋቸውም፡፡ድረሱልን ጥሪ ስንቴ አነሳሁ ግን ጆሮ የላቸውም፡፡ የመን ዶላር የለ ሀንበርገር ፡፡
በዚህ ዙሪያ Feti Berihun …….የተባለ ውዳጄ ህዝቡ እያለቀ ዝም የሚል ሀገር ወዳድነት ምኑ ላይ ነውሀገር ወዳድነቱ፡፡ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችሽ ይህን ጉድ ዝም ካላችሁ ለየትኛው ህዝብ ነጻነት ነው የምትታገሉት? አሜሪካ ላለው? አውሮፓ ላለው? ለኢንቨስተሩ?….ኪሱን ላደለበው?…ዝም ካላችሁ ድምጽ ማሰማትም ሆነ መፍትሄ መፈለግ ግድ ካልሰጣችሁ ስልጣል ላይ ተቀምጦ ከለው ስርዓት በምን ትሻላላችሁ?….
ብሎ አስተያየቱን አስፍሯል፡፡ ከዚህ በፊት እኔም ደጋግሜ ያስፍርኩት ሀሳብ ነው፡፡ እነሱን ግን መርሳቱ ይሻላል፡፡ እኛ እንደራጅ ወገን ለወገኑ ካልደረሰ ኢትዮጵያን እንወዳለን ማለት ባዶ አፈሯን አይደለም፡፡ መሬት ድንጋዩን አይደለም፡፡ ህዝቡን ያልወደደ የሀገር ፍቅር አይኑረን፡፡ እባካችሁ ፍላጎት ያላችሁ እንሰባሰብ፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar