www.maledatimes.com ህወሀት ከኔ ጋር ነው ያለው፤አደረጃጀቱም ከኔ ጋር ነው ያለው…(አቶ ስብሀት ነጋን )Dereje Habtewold - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ህወሀት ከኔ ጋር ነው ያለው፤አደረጃጀቱም ከኔ ጋር ነው ያለው…(አቶ ስብሀት ነጋን )Dereje Habtewold

By   /   January 31, 2013  /   Comments Off on ህወሀት ከኔ ጋር ነው ያለው፤አደረጃጀቱም ከኔ ጋር ነው ያለው…(አቶ ስብሀት ነጋን )Dereje Habtewold

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 19 Second
ያልገባኝ ጥያቄ
ስለ ህወሀት መከፋፈል በስፋት እየተነገረ ባለበት ሰዓት ፍኖተ ነፃነት በጉዳዩ ዙሪያ አቶ ስብሀት ነጋን አናግሯቸዋል።
አቦይም፦<<በዚህ ምድር ላይ ሊሆን ከማይችል ነገር አንዱ የህወሀት መሰንጠቅ ነው። …ህወሀት ከኔ ጋር ነው ያለው፤አደረጃጀቱም ከኔ ጋር ነው ያለው…>> የሚል አስገራሚ ምላሽ ሰጥተዋል፤ ወይም ለማስተባበል ሞክረዋል።
በመቀሌ ተበትኗል በተባለው ወረቀትም ሆነ ዛሬ ፍኖተ-ነፃነት ባጠናቀረው ዘገባ እንደተመለከተው በነአቶ ስብሀት ቡድን እና በነ አቶ አባይ ወልዱ ቡድን መካከል የጎላ ልዩነት የተፈጠረው፤ እነ አቶ ስብሀት (ስዩም፣አባይ፣ቅዱሳን ወዘተ)- ቀደም ሲል ከህወሀት የተባረሩት የድርጅቱ የቀድሞ አመራሮች መመለስ አለባቸው” የሚል አጀንዳ በማራመዳቸው ነው።
እዚህ ላይ ያልገባኝ ነገር ህወሀት ለሁለት በተከፈለ ጊዜ ፦”አንጃ”ተብለው በአቶ መለስ ቡድን ከድርጅቱ የተባረሩት ሰዎች ”ወደ ድርጅታችሁ ተመለሱ”ቢባሉ ለመመለስ ፈቃደኛ ይሆናሉ ? እነ አቶ ስብሀት በዚህ አቋም ምክንያት እስከመቃቃር የደረሱትስ ከተባረሩት ጋር ስምምነት ላይ ከደረሱ በሁዋላ ነው? ወይስ “እኛ እንስማማ እንጂ እነሱ መመለሱን ይፈልጉታል” ከሚል ግምት ተነስተው? “የተባረሩት ይመለሱ” ሲባልስ ከመካከላቸው የተወሰኑት (እነሱ እንደሚሉት ነፍጠኞች ጉያ ያልገቡት እነ ስዬና ገብሩን ሳይጨምር) ተመርጠው ነው? ወይስ “ሁሉም ይመለሱ” ነው እየተባለ ያለው? እንበልና ህወሀት በስምምነት “ይመለሱ”ቢልስ በእርግጥ የተባረሩት የቀድሞው አመራሮች ይመለሳሉ? ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on January 31, 2013
  • By:
  • Last Modified: January 31, 2013 @ 1:03 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar