www.maledatimes.com እራሷ ክርስትና አልተነሳች ልታቋቁም ወጣች - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

እራሷ ክርስትና አልተነሳች ልታቋቁም ወጣች

By   /   February 5, 2013  /   Comments Off on እራሷ ክርስትና አልተነሳች ልታቋቁም ወጣች

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 50 Second

እራሷ ክርስትና አልተነሳች ልታቋቁም ወጣች

መቅደስ አበራ (ከጀርመን)

የወያኔ አንባገነኖች  በስልጣን ላይ በቆዩባቸው ያለፉት 21 ዓመታት እና በትጥቅ ትግል ወቅት የጠፋውን ህይወትና የወደመውን ንብረት ለኢትየጵያ ህዝብ መንገር ለቀባሪ ማርዳት ነው፡፡ ለመሆኑ ሁሉም እድሉን አግኝቶ  ስላልተናገረው  ብእርና ወረቀት አዋህዶ ከትቦ በጽፈው ስንት መጽሐፍ እንደሚወጣው ቤት ይቁጠረው፡፡ ወይም ጽፈውት  ጊዜውን እየጠበቀ ይሆናል አንድ ቀን ያወጡታል፡፡ከሁሉ የሚከፋው ደግሞ የስልጣን ተቀናቃኞችን ብቻ ሳይሆን በጭፍን ትላቻ ተነድተው

በአንድ ብሄርና እምነት ላይ  ሌላውን በማነሳሳት ለጅምላ ግድያና በመቶ በሺዎች የሚቆጠሩን ለማፈናቀል የሚሰራውን ተንኮል ላየ እነዚህ ሰዎች እውነት ኢትጵያዊ ናቸው ብሎ እንዲጠይቅ ያደርገዋል፡፡ ሰው እንዴት ሀገርን እመራለሁ ብሎ የተቀመጠ ሀይል የራሱን ህዝብ በጅምላ ይጨፈጭፋል;ይግድላል ያፈናቅላል አላማቸውስ ምንድን ነው ብሎ ይጠይቃል

ይህ እንግዲህ ግር የሚለው ለባእዳን እና ነፍስ ላላወቁ ህፃናት ካለሆነ በስተቀር  የእድሜውን ግማሽ  የወያኔ/ኢህአዴግ የስቃይ ሰለባ ሁኖ ላሳለፈው ኢትዮጵያዊ አደለም፡፡ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ጅግራ ናት ይሏታል  እንደሚባለው ሲላቸው አስቀድመው በደንብ የተጠና ድራማ ይሰራና በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በኩል ህዝቡን ለማደናገር በተደጋጋሚ እንዲቀርብ ይደረጋል፡፡ለምሳሌ ያህል አደስ አበባን እንደባገገዳድ አኬልዳማ ወዘተ የመሳሰሉትን ማሰታወስ ይቻላል፡፡  የመጀመሪያውን ትይንት አስጠልቶት  ህዝቡ ባያየውም በተመልካቾች አስተያየት ተደጋጋሚ ጥያቄ ስለቀረበልን  የተመልካቾችን ፍላጎት ለማርካት በሚል የንጹሀን ዜጎች ሀጢያት ተደርድሮ ይቀርባል፡፡ይኸኔ መገመት የሚቻለው እነዚህን ንጹሀን ወይ እድሜ ልክ እስራት ወይ ጸና ሲልም የሞት ፍረድ ሊያስፈርድ መዘጋጀቱን  ነው፡፡ ቀላል ሲባል ከ15-25 አመት ጽኑ እስራተና በርካታ የገንዘብ ቅጣት ይጠብቃቸዋል፡፡

ወያኔዎች ቀደም ሲል የጀመራቸው የስልጣን ጥማት ምኒልክ ቤተ ምንግስትን በመቆጣጠር  ሊረካ ባለመቻሉ ጵጵስናውም ፤ ሲኖዶሁም ፤መጅሊሱም መስጊዱም በወያኔ ቅጥጥር  ስል ውለዋል፡፡ በዚህም አይወሰኑም ለብዙ መቶ አመታት በፍቅር የኖሩትን የእስልምናና የክርስትና እምነት ተከታዮች እንደ እስራኤልና ፍልስጥኤም ታሪካዊ ወንድማማችነታቸውን  በታሪካዊ ጠላትነት ለመቀየር የጥላቻ ፖለቲካውን በዶክሜንታሪ ፊልም አስደግፎ ያቀርባል፡፡  ሰሞኑንም የእስልምና እምነት ተከታንና ለማዋጋት ከፍተኛ ዝግጅት እተደረገ እንዳለ በርካታ ምንጮች እየጠቆሙ ይገኛሉ፡፡አርቆ አስተዋዩ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉንም ችሎ ሆድ ካገር ይሰፋል በሚለው ሀገረኛ ፈሊጥ መሰረት ታገሰው እንጂ እንደወያኔ ተንኮልና ቴራ እስካሁን እስልምና እና ክርስትና እምነት ተከታየች አንድ ቤት ውስጥ ቀርቶ ባናድ ሀገር ውስጥ ከማይችሉበት ደረጃ ይደርሱ ነበር፡፡ወያኔዎች እስካሁን ያልገባቸው ነገር ቢኖር የኢትዮጵያ ህዝብ ከጥላቻ ይልቅ ሰላምንና ፍቅርን እንደሚሻ አለማወቃቸው ነው፡፡ከሰላም እንጅ ከጦርነት ምንም እንደማይገኝ መረዳት አለመቻላቸው ነው፡፡”እራሷ ክርስትና አልተነሳች ልታቋቁም ወጣች “አሉ አበው ሲተርቱ የራሱን የውስጥ ሰላም የሌለው የወያኔ መንግስት ሱማሊያ፣ ኡጋንዳ እና ሱዳን ሰራዊት ከመላኩ በፊት፤ ከኤርትራ ጋር አስታርቁኝ እያለ ከመማጸኑ በፊት ምናለበት ከራሱ እና  ከራሱ ህዝብ ጋር ቢታረቅ፡፡ምናለበት በየአደባባዩ እየወጡ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ከማውራት ለነጻነትና ለእኩልነት መስፈን የተሰውትን የትግራ ይተወላጆች እና የሌሎችን ሰማእታት ደም የውሻ ደም ባያደርጉት፡፡

እነሆ እሳት እና ውሃን ፈጠርኩልህ እጅህን ወደፈለግህበት ጨምር ተብሎ በነጻነት የተፈጠረ ፍጡር ዛሬ በወያኔ በነጻነት እምነቱን እንዳያካሂድ ፤የፈለገውን የፖለቲካ አመለካከት እንዳይደግፍ ቢደረግም የኢትየጵያ ህዝብ ተባብሮ ነፃነቱን የሚያስመልስበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡የተለያዩ አፋኝ ሰው ሰራሽ ህጎች እና የስለላ መዋቅሮች አቋቁሞ በርካቶችን ለእስራትና ለሞት ቢዳርግም በፈጣሪያችን እገዛና በህዝቦች የጋራ ትግል ነጻ እንወጣለን፡፡

እግዚያብሄር ኢትዮጵያንና ህዝቦችዋን ይባክ!

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on February 5, 2013
  • By:
  • Last Modified: February 5, 2013 @ 3:01 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar