www.maledatimes.com ይህ የወያኔ እንስሳዊ ባህሪ እንጂ ሌላ አይደለም ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ይህ የወያኔ እንስሳዊ ባህሪ እንጂ ሌላ አይደለም !

By   /   February 5, 2013  /   Comments Off on ይህ የወያኔ እንስሳዊ ባህሪ እንጂ ሌላ አይደለም !

    Print       Email
0 0
Read Time:14 Minute, 52 Second

ይህ የወያኔ እንስሳዊ ባህሪ እንጂ ሌላ አይደለም !

ኮሚቴዎቻችን መርጠን 3 ጥያቄዎችን በአደራ አስይዘን ወደ መንግሰት አካላት ስንልካቸው ዛሬ እያየነው ያለው የጠነከረ ጭቆና እና ረገጣ ይፈጣራል ብለን አላሰብንም ነበር፡፡ ከአንድ ዓመት በላይ መብታችን ይከበር ድምጻችን ይሰማ እያልን ስንጮህ መንግስት መብታችን ረግጦ ድምጻችንን አፍኖ በተፋጠጥ እየተያየን እዚህ ደረሰናል፡፡ እኛ በቅን ልቦና መንግስት ከዛሬ ነገ ይገባው ይሆናል ጥያቄያችንንም ይመልስልናል በማለት በርካታ ሰላማዊ ተቃሞዎችን ስናደርግ ብንቆይም በመንግስት ስም የተደራጁ ሽፍታዎች ግን ሙስሊሙን ህረተሰብ ሲያምሱት እና ሲያሳቃዩት ቆይተዋል፡፡ ሙስሊሙን ህብረተሰብ ለማጥፋት ቆርጠው ተነስተዋል፡፡ለዚህም የጥፋት ዘመቻቸው ሙስሊሙን ለመምቻነት እንዲያግዛቸው “ኢስለማዊ መንግሰት” ሊመሰርቱ የሚል የውሸት ካባ በሙስሊሙ ላይ ጫኑበት፡፡ ይህን ቅዠት የሆን ፍልስፍና ይዘው ህዝቡ ላይ ሽብር መንዛት ጀመሩ ፡፡  በሀይማኖት ሽፋን ድብቅ አጀንዳቸውን ለማስፈጸም የሚሞክሩ ጥቂት አክራሪዎች በማለት ህዝቡ እሰኪሰለች ድረስ ቀን በቀን በኢቲቪ አስተጋቡት፡፡ ይህን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ እውነት ለማስመሰል በስርቤት ያሉ ወንድሞች ላይ ከባድ ድብደባ በማድረግ ያልሰሩትን ሰርተናል ብለው እንዲሉ አስገድደዋቸዋል፡፡ የዚህም ግፋዊ ድብደባ የመጀመሪያዎቹ ሰለባዎች በፊርማችን አረጋግጠን ከሞቀቤታቸው አስወጥተን በአደራ የላክናቸው ኮሚቴዎቻችን ነበሩ፡፡

 

ወያኔ በሚሊዮኖች እውቅና የተሰጠውን ይህን ህጋዊ ኮሚቴ ይዳፈራል ብሎ ያሰበ ማንም አልነበረም፡፡ አይደለም መደብደብ እና ያስራቸዋል ተብሎ እንኳን አይታሰብም ነበር፡፡ ግን ወያኔ ዓላማ የሙስሊሙን ጥያቄ መመለስ ሳይሆን በተቃራኒው ሙስሊሙን ማዳከም እና ማትፋት ስለነበር ግፋዊ ድብደባውን በኮሚቴዎቻችን ላይ ጀመረ፡፡በዚህም ድርጊቱ ለሙስሊሙ ህብረተሰብ ያለውን ጥላቻ እና ንቄት በግልጽ አሳይቷል፡፡መንግስት ይባስ ብሎ ኮሚቴዎችን ያልሰሩትን ሰርተናል ብለው እንዲናገሩ የስቃይ ማዕበል አውርዶባቸዋል፡፡ የራሱን እኩይ ዓላማ ለማሳካት በወኪሎቻችን ላይ የግፍ ውርጂብኝ አወረደባቸው፡፡ ኮሚቴዎቻችን ቀን ከሌሊት በስቃይ አለጋ ተገረፉ፤ አካላቸውም መንፈሳቸውም ደማ፡፡ ነፍሳቸው ልትወጣ እስክትቃረብ ድረስ ጭካኔ በተሞላበት ድብደባ ተሰቃዩ፡፡ ስቃዩ እጅግ የበረታ ስለነበር በሚደበደቡበት ሰዓት በዚያው ከሞትንም በማለት ሸሀዳ ይሉ ነበር፡፡ በኤሌክትሪክ ሾክ በመግረፍ፤ በፈላ ውሀ ውስጥ በመንከር፡ በኤሌክትሪክ ወንበር ላይ በማስቀመጥ፤ ለረዥም ሰዓታት እንዲቆሙ እና ቁጭ ብድግ እንዲሉ በማድረግ ፤ ከወገባቸው ላይ በተኙበት ከባድ ነገር በመጫን፤ እጅ እግራቸውን በካቴና አስረው በቦክስ እየተቀባበሉ በማሰቃየት መከራቸውን አሳይተዋቸዋል፡፡ የነበው ስቃይ ሞት ምን አለበት ያስብላል፡፡

እንዲህ የሚያሰቃዩቸው “ስንቀሳቀስ የነበረው ኢስላማዊ መንግሰት ለመመስረት ነው ብላቸሁ ተናገሩ በማለት ነበር”፡፡ኮሚቴዎቻችን በመጀመሪያው አካባቢ ይህን ስቃይ ተቋቁመው ቢቆዩም አካላቸው በጣም እየተጎዳ ሲመጣ ግን ስቃዩን ከሚቋቋሙት በላይ ሆነባቸው፡፡ከአካላዊ ስቃይ በተጨማሪ መንፈሳዊ ስቃይም ያደርጉባቸው ስለነበር ሰዉ ናቸውና አቅማቸው እየተዳከመ መጣ፡እንደዚህ እየተሰቃዩ መቆየቱም ለውጥ እንደሌለው ሲገነዘቡ ያልሰሩትን ስርተናል ብለው እንዲናገሩ ቀን ከሌሊት የሚወርድባቸው ስቃይ አስገደዳቸው፡፡ አይደለም በውናቸው በህልማቸው አስበውት የማያውቁትን ነገር ተናገሩ፡፡እነዚያ የስልጣን ግዜያቸውን ለማራዘም ብለው ኮሚቴዎቻችንን ሲሰቃዩ የነበሩት የሚፈለግትን ነገር አገኙ፡፡ይህን እኩይ ሴራ ለህዝብ አስመስሎ ለማቅረብም በቪዲዮ ካሜራ ቀረጹት፡፡ አሳፋሪው መንግስትም ይህን በድብቅ እና በግዳጅ የተቀረጸ ቪዲዮ በመቆራረጥ እና ከሌሎች ቪዲዮች ጋር በማገናኘት እጅግ አሳፋሪ የሆነና ከእውነት ፍጹም የራቀ የሆነ ዶክመንታሪ ፊልም በማሰራት ለህዝብ ለማቅረብ ወስኗል፡፡
እጅ እግር አስሮ በኤልክትሪክ ሾክ በመግረፍ እና የፈላ ውሀ ውስጥ እየነከሩ በመደብበድ ያልሰሩትን ሰርተናል እንዲሉ ማድረግ ወንድነት አይደለም፤ ጀግንነትም አይደል፤ ይህ የወያኔ እንስሳዊ ባህሪ እንጂ ሌላ አይደለም ፡፡ ማንኛውም ሰብዓዊነት የሚሰማው ሰውም ይሄን ድርጊት አያደርገውም፡፡ ይሁን እንጂ በመንግሰት ስም የተደራጁ ሽፍቶች በኮሚቴዎቻችን ላይ አሰቃቂ ድብደባ ፈጽመውባቸዋል፡፡ እኛ ኮሚቴዎቻችንን እና ወንድሞቻችንን ከማንም በላይ እናውቃቸዋለን፡፡ ስቃዩ ካቅማቸው በላይ ሆኖ ያልሰሩትን ሰርተናል ብለው ሲናገሩ ብንሰማቸው በነሱ ላይ ሲደረግ የነበረው የስቃይ መዓብል ምን ያክል ከባድ መሆኑን እንድንረዳ ደርገናል እንጂ ኮሚቴዎቻችንን በሌላ እንድናስባቸው አያደርገንም፡፡ ስቃዩ ምን ያክል ከባድ እንደነበር ከኮሚቴዎቻችን ፊት ገጽታ ላይ ይነበባል፡፡ በኮሚቴዎቻችን ላይ ይታይ የነበረው የፊታቸው ኑር ዛሬ ገርጥቶ እና ጠቁሮ ስናየው ውስጣችን ይቃጠላል፡፡

መንግሰት ያለ መስሎን ለሽፍቶች ሰጥተን አስደበደብናቸው ፡፡ አካላቸው ከስቶ እና ተጎሳቆሎ፤ ያዬ  በወኔ የተሞላ ንግግራቸው ዛሬ ከጆራችን ሲርቅ ልባችን በሀዘን ዓይናች በደም እንባ ይታጠባል፡፡

የወያኔ  መንግሰት ጠላትነቱን ከመቼም ግዜ በበለጠ አረጋግጦልናል፡፡ ገደለን፤ አሰረን ፤ አሰቃየን፤ አሁን ደግሞ ይባስ ብሎ እጅግ አስናዋሪ የሆነ የሀሰት ፊልም በመስራ በአደባባይ ስማችንን ሊያጠፋ እና ክብራችንን ዝቅ ለማድረግ ተዘጋጅቷል፡፡ መንግሰት የኮሚቴዎቻችን እና የህዝበ ሙስሊሙን ክብር በሚያንቋሽሽ መልኩ የሀሰት ፊልም በማዘጋጀት ጠላትነቱን በግልጽ አረጋግጦልናል፡፡ ከዚህ በላይ ምንም ሊያደረገን አይችልም፡፡ ገድሎናል፤ አስሮናል አሰቃይቶናል፡፡ አሁን ግን ከግድያ በባሰ መልኩ ተወልደን በኖርንባት ሀገራችን ተዋርደን እና ተሸማቀን እንደንኖር ወይም ሀገር ለቀን እንድንሄድ እያስገደደን ይገኛል፡፡ ያለስማችን ስም በመለጠፍ ያለ ስራች ስራ በመስጠት ተሸማቀን እንደንኖር አድርጎናል፡፡ ይህንም ነገ ማክሰኞ በአደባባይ በማውጣት በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ ያለውን ንቄት ዳግም ሊያሰዩን ተዘጋጅቷል፡፡በአደባባይ ኮሚቴዎቻችን ሲያንቋሽሹ ማየቱ ምን ያህል ያሳምማል፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብ በአደባባይ ሲሰደብ መስማቱ ምን ያህል ልብ ያቆስላል፤ በጣም ልባችን ቆስሏል፤ ትዕግስታችንም እየተሟጠጠ መጥቷል፡፡

ስለሆነም ብዙ እየተባለለት ያለው ይህ አዲስ ፊልም ከመውጣቱ በፊትና በኋላ በመላው አገሪቱ ያሉ ሙስሊሞች ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ለክርስቲያን ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ፍቅር እንዲሰጡና ኢህአዴግ ሊፈጥረው ያሰበውን የጥርጣሬ አመለካከት መስበር እንደሚገባ ጠንቅቀን ማወቅ ይኖርብናል ። ከዚህ  በተጨማሪ መላው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች አምባገነኑ የወያኔ  መንግሰት  የሚያደርግብንን እጅግ አስቀያሚ ሴራ ተረድተን ሁላችንም ከሌሎች  ወገኖቻችን ጋር በመተባበር በቁርጠኝነት ለመታገል ከልባችን ቆርጠን መነሳት ይኖርብናል፡፡ በእርግጠኝነት እስከ ህይወታችን ፍጻሜ እንፋለማቸዋለን !!! በትግላችን ላይ አሏህ (ሰ.ወ) ጽናቱን እና ብራታቱን እንዲሰጠን በመጨረሻም ድሉን እንዲያጎናጽፈን አጥብቀን እንለምንዋለን ፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !

ለአስተያዬትዎ = abnuye2001@gmail.com

 

 

 

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on February 5, 2013
  • By:
  • Last Modified: February 5, 2013 @ 3:04 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar