www.maledatimes.com 33ቱ ፓርቲዎች ኢህአዴግን አስጠነቀቁ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

33ቱ ፓርቲዎች ኢህአዴግን አስጠነቀቁ

By   /   February 5, 2013  /   Comments Off on 33ቱ ፓርቲዎች ኢህአዴግን አስጠነቀቁ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 47 Second

33ቱ ፓርቲዎች “ኢህአዴግ ስለ አካባቢ ምርጫ የሰጠው መግለጫ የጥያቄዎቻችንን ትክክለኛነትና አግላይ አቋሙን ያረጋገጠበት ነው” በሚል ርዕስ መግለጫ አወጡ፤ ኢህአዴግን አቋሙን እንዲያስተካክልም አስጠነቅቀዋል፡፡
የኢህአዴግ ጽ/ቤት ኃላፊና የምርጫ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ የአቶ ሬድዋን መግለጫ ኢህአዴግ ዛሬም በአገራዊና ህዝባዊ ጉዳዮች ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች በሙሉ ወሳኝም፣ ባለመፍትሔም እኔ ብቻ ነኝ ከሚል የእብሪት ስሜት አለመላቀቁንና ሀላፊነት በጎደለው ጭፍን ጥላቻ እየተነዳ መሆኑን ያመለክታል ያለው የፓርቲዎቹ መግለጫ፤“ይህ አካሄድ ለማንም የማይጠቅም ከመሆኑም በላይ ብዙ ርቀት ሊያስኬደው እንደማይችል በድጋሚ ሊገለጽ ብቻ
ሳይሆን በህዝባዊ ሀይል ሊገታ የሚገባው መሆኑን እንረዳለን” የሚል አሳስቧል ።
ፓርቲዎቹ መግለጫቸው ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ቀላል እንደሆኑ አስገንዝቧል፡፡ ጥያቄያቸው ሲጠቃለል መንግስትና ኢህአዴግ ይለያዩ፣የመገናኛ ብዙሀን ፍትሀዊ አጠቃቀም ይኑር፣የፖለቲካ ፓርቲዎች በነፃነት የመንቀሳቀስ መብት
ይከበር፣ምርጫ ቦርድ ከገዥው ፓርቲ ተጽዕኖ ተላቅቆ በነፃነት ይደራጅ!የህግ የበላይነት ይረጋገጥ፣በገዥው ፓርቲ አማካይነት ለ አፈና የወጡ ህጎች ይከለሱ/ይሻሩ፣ በድምሩ የዜጎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ተከብረው
የህዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ይረጋገጥ ዘንድ የምርጫ ሜዳው ይስተካከል የሚሉ ናቸው በማለት የጥያቄዎቹን ዘርዝረዋል። የኢህአዴግ አቋምና አካሄድ የትም አያደርሰውም ማንንም አይጠቅምም በማለት አስጠንቅቀዋል፡፡
33ቱ የአዳማ ፔቲሽን ፈራሚ ፓርቲዎች ጥር 26 ቀን 2005 ዓ.ም ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ ቢያቅዱም የመሰብሰቢያ አዳራሾችን እንዳያገኙ በመንግስት ጫና እየተደረገባቸው በመሆኑ ስብሰባውን ለማራዘም መገደዳቸው ታውቋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on February 5, 2013
  • By:
  • Last Modified: February 5, 2013 @ 3:23 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar