www.maledatimes.com መድረክ ማኒፌስቶውን አጸደቀ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

መድረክ ማኒፌስቶውን አጸደቀ

By   /   February 5, 2013  /   Comments Off on መድረክ ማኒፌስቶውን አጸደቀ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 37 Second

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) 7ኛ መደበኛ ጉባኤውን አደረገ፡፡ጉባኤው የተሻሻለውን ማኒፌስቶ አጽድቆ ከዚህ በፊት በዙር ይደረግ የነበረው የመድረክ ሊቀመንበር ምርጫ በውድድር በድምጽ
ብልጫ እንዲመረጥ የተወሰነ ሲሆን የግንባሩን መተዳደሪያ ደንብ በስራ አስፈፃሚ ደረጃ ተጨማሪ ውይይት እንዲደረግበት ስምምነት ላይ በመድረስ እንዳፀደቀው ለዝግጅት ክፍላችን የደረሰው መረጃ ያመለክታል፡፡
የዜና ምንጮቻችን አንደገለጹልን ከስብሰባው በፊት ተዘጋጅቶ በቀረበው ረቂቅ ማኒፌስቶ ላይ ውይይት ተደርጎ ሰፊ ማሻሻያ ከተደረገበት በኋላ እንዲጸድቅ ተደርጓል፡፡ ከዚህ በፊት በመድረክ ውስጥም ሆነ በህብረተሰቡ ዘንድ ቅሬታ ሲያስነሳ የነበረው የመድረክ አመራር በተራ ወይም በዙር እንዲዳረስ የተደረገው አሰራር ነበር፡፡ በዚህ ጉዳይ ጠቅላላ ጉባኤው ሰፊ ውይይት አድርጎበት በውድድር ብቃት ያለውና  አብላጫ ድምጽ ያገኘ ሊቀመንበር
ሆኖ እንዲሰራ ተወስኖዋል፡፡
ሌላው የቀረበው አጀንዳ መተዳደሪያ ደንቡ ነበር ፡፡ ጉባኤው ላይ በተሻሻለው ረቂቅ ደንብ ላይ ጠንካራና አከራካሪ ነጥቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡በመጨረሻም ጉባኤው እየተግባባበት ተጉዞዋል፡፡ ይሁን እንጂ ደንቡ እንደገና በዝርዝር መታየት እንንደሚገባው ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ለዚሁ ሲባል በመተዳደሪያ ደንቡ ለሌላ ተጨማሪ የውይይት ጊዜ ተላልፏል ፡፡መድረክ ያፀደቀው ማኒፌስቶ የኢህአዴግን መሰረታዊ ስህተቶች የገመገመና አማራጭ የመፍትሄ
ሃሳቦችንም ያካተተ ነው፡፡ግንባሩ በጠቅላላ ጉባኤውና ባፀደቃቸው መተዳደሪያ ደንብና ማኒፌስቶ ላይ በቅርቡ መግለጫ እንደሚሰጥም ለማወቅ ተችሏል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on February 5, 2013
  • By:
  • Last Modified: February 5, 2013 @ 3:27 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar