www.maledatimes.com በደብረብርሃን ነዋሪዎች በፖሊሶች የተፈፀመን የመብት ጥሰት አጋለጡ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በደብረብርሃን ነዋሪዎች በፖሊሶች የተፈፀመን የመብት ጥሰት አጋለጡ

By   /   February 5, 2013  /   Comments Off on በደብረብርሃን ነዋሪዎች በፖሊሶች የተፈፀመን የመብት ጥሰት አጋለጡ

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 22 Second

በአማራ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ዋና ከተማ በሆነው ደብረብርሃን ከተማ ፖሊስ በነዋሪዎች ላይ የመብት ጥሰት እየፈፀመ መሆኑ ተጠቆመ፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች ዝግጅት ክፍላችን ድረስ በመምጣት በሰጡት መረጃ
ፖሊስ በፀጥታ ማስከበር ስም በወንጀል ድርጊት ላይ መሰማራቱን አጋልጠዋል፡፡ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ፖሊስ ራሱን ከህግ በላይ አድርጐ ስለሚቆጥር የዜጐችን ህገመንግስታዊ መብት በሚጥስ አሰራር ላይ ተሰማርቷል፡፡ ነዋሪዎቹ ጨምረው እንደሚያስረዱት “ፖሊሶች ከካድሬና ከደህንነት በሚሰጣቸው ትዕዛዝ ንፁሐን ዜጐችን በፖለቲካ አመለካከታቸው እያስጠሩ ያሸማቅቃሉ፣ ያስፈራራሉ፣ ይደበድባሉ፣ ያስራሉ፡፡” ነዋሪዎቹ በምሳሌነት ሲገልፁም “የካቲት 18 ቀን 2005 ዓ.ም ከቀበሌው ኮሚኒቲ ፖሊስ፣ ከወረዳው ፖሊስ፣ ከክልሉ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ እና ከፌዴራል ፖሊስ የተውጣጣ ቡድን ከለሊቱ 8 ሰዓት ቀበሌ 06 ቀጠና 4 ውስጥ የጌታ ወ/ሚካኤል የተባሉን ግለሰብን ግቢ ከበቡ፡፡ የግቢው ነዋሪዎች ለአካባቢው ነዋሪ በስልክ በማሳወቃቸው የአካባቢው ህዝብ ወጥቶ ምንድነው? ብሎ ጠየቀ፡፡ እዚህ ግቢ የሚኖር አቶ አበበ በቀለ የተባለ ግለሰብ አካባቢውን በጥብጧል የሚል መረጃ ደርሶን ነው ብለው መለሱ፡፡ የመላው አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ የሰሜን ሸዋ ተጠሪ የሆኑት አቶ አበበ ከነጐረቤቶቹ በሠላም ተኝቷል፡፡ በአካባቢው የተፈጠረም የፀጥታ መጓደል የለም፡፡
ማነው እንዲህ ብሎ የነገራችሁ በዚህን ሰዓት ከተለያየ ቦታ የተውጣጣ ፀጥታ አስከባሪዎችስ እንዴት ተቀናጅታችሁ ልትመጡ ቻላችሁ ብለን ብንጠይቃቸው መልስ ሳይሰጡ አቶ አበበንና ለፖሊሶቹ ጥያቄ ያቀረቡትን ወደ ፖሊስ ጣቢያ
ወሰዱ፡፡ የፍ/ቤት ትዕዛዝን ብንጠይቅ ምን አገባችሁ፡፡ የመጠየቅ መብት የላችሁም አሉን፡፡ ለሊቱኑ ለተለያየ ሚዲያ ደውለን በማሳወቃችን ንጋት ላይ በ12 ሰዓት ስትጠሩ ትመጣላችሁ ብለው ታሳሪዎቹ ለቀዋቸዋል” ብለዋል፡
፡ ታሳሪዎቹ “የታሠርንበት ወንጀል ይነገረን፤ የከሰሰን ሰው ማነው” ብለው ቢጠይቁም መልስ እናዳለገኙ መረጃ ሰጪዎቻችን ጠቁመውናል፡፡ ያለ አንድ ምክንያት ዜጐችን በአመለካከታቸው ለማዋከብና በሐሰት ለመወንጀል
ሲባል የአካባቢው ህዝብ ሠላም ማጣቱም እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ የቀበሌው ኮሚኒቲ ፖሊስ አስተያየት እንዲሰጥበት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ ይሁን እንጂ የወረዳውን ፖሊስ አዛዥ ኢ/ር ምንውዬለትን
በስልክ አግኝተን ጠይቀናቸው ጉዳዩን አጣርተው እንደሚደውሉ ቢነግሩንም ዜናው እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ምላሽ አልሰጡንም፡፡finot netsanet

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on February 5, 2013
  • By:
  • Last Modified: February 5, 2013 @ 3:32 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar