www.maledatimes.com የልጆቼ የጎህዬና የሱመያ፣ የሩቴና የኦማር “ጩሃት” (አብዩ በለው) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የልጆቼ የጎህዬና የሱመያ፣ የሩቴና የኦማር “ጩሃት” (አብዩ በለው)

By   /   February 9, 2013  /   Comments Off on የልጆቼ የጎህዬና የሱመያ፣ የሩቴና የኦማር “ጩሃት” (አብዩ በለው)

    Print       Email
0 0
Read Time:9 Minute, 59 Second

Fri 10/09/2010 12:50 AM በኢሜል ለማገኛቸው የትየለሌ ወዳጆቼ ለ2003 ዓ.ም የአዲስ አመት መልካም ምኞት መግለጫ የላኩላቸው መልዕክቴ የሚከተለው ነበር፡፡

“መልካም አዲስ አመት ይሁንላችሁ! አንኳዋን ከዘመን ዘመን በጤና አሸጋገራችሁ!
አኔ ግን  ከሃሌ ጋር አንዲህ ብያለሁ:: ብርቱን ጥዬ አልሻገርም!”

ዛሬ ፍልቅልቋ ሃሌ ከመራራው የ“እናት ናፍቆት” ሰቆቃ ወጥታ አሜሪካን ሃገር በእናቷ እቅፍ ውስጥ ትገኛለች፡፡ ስለ ሃሌ እግዚአብሔርን ሁሌ አመሰግነዋለሁ፡፡ ሌላው ሁሉ ቢቀር በልደት ቀኗ የእናት ናፍቆት ሰቀቀኗን አስቀርቷልና ፡፡

እነሆ ዛሬ የተመስገን ደሳለኝ “የሀገር ጩሃትና የታሳሪ ልጆች… አውደ-ዓመት” መጣጥፍ እንደተለመደው “ተሜን” አንብቤ ወደ አልጋዬ መሄድ አልተቻለኝም፡፡እነ ናፍቆት፣ ኦማር፣ፍትህና፣ ጎህ … በአንድ ወገን እነ ሱመያ፣ ሩህና፣ ኢናስ፣… በሌላ ወገን በወላጆቻቸው ናፍቆትና ስስት ሌት ከቀን እየጮሁ እንዴት ይተኛል? እንዴትስ ሌለቱ በሰላም ይነጋል? የትኛው ህሊና ያርፍ ይሆን?

እስክንድርም ሆነ አንዷለም ወይም ውብሸት አሊያም አቡበክርና አህመዲን ይልቁንም ካሚልና የሱፍ ዛሬ በግፈኛው የህወሃት እስር ከመማቀቃቸው እጅግ አብዝቶ የሚያደማቸው እነዛ የሚያሳሱ እምቦቀቅላ ፍሬዎቻቸው ፍፁም ንፁኃን ሆነው እያለ የህወሃት የግፉ በትር ለእነርሱም ተርፎ እንዲያ በናፍቆት ሲጨነቁና ሲዋትቱ ማየቱ የመስለኛል፡፡ እንኳንስ ጣፋጯ ሱመያ በናፍቆት ስታለቅስ ይቅርና አልበላም አልጠጣም ስትል ምንኛ እንደምታስጨንቅና እንደምታሳቅቅ ለማወቅ ሰው መሆን ይበቃል፡፡ ወላጅ ሲኮን ደግሞ…

ታላቁ መፃህፍ “አንዱ ስለ ሁሉም…” እንዲል የእነ ጎህዬና የሩቴ “ጩሃት” ተመሳሳይ አንድምታ ያለው ይመስለኛል፡፡ ለምንስ ቢሉ፡-

አንድም እንደ ህፃን – ወላጆቻቸው ንፁሃን ሆነው እያለ አንዴ ነፍጠኛ፣ ሌላ ጊዜ ኦነግ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ቅንጅት፣ አሁን ደግሞ አሸባሪ እየተባሉ በ“አይንህ ቀለም አላማረኝም” ስይጥንና በወያኔ ሲኦሎች ውስጥ ለዘመናት ተቆልፎባቸው የወላጅ እቅፍ ፍቅር እጦት ለሚያናውዛቸው የኢትዮጵያችን “የራሔል ልጆች” ተገብተው ሲጮሁላቸው በማየቴ፣

አንድም እንደ ህዝብ – ሰሚ ስላጣው የኢትዮጵያውያን የፍትህ፣ የነፃነት፣ የዲሞክራሲና፣ የእኩልነት እጦት ስለ እኛ ተገብተው እንዲጮሁልን ወላጆቻቸው ስለፈረዱባቸውና በእውነትም ሳይገባቸውና ሳይገባቸው ስለእኛ ሲጮሁልን በማየቴ፣

ይልቁንም የእነ ናፍቆትም ሆነ የእነ ሩቴ ሰቆቃ ልዩ የሚሆንብኝ ዛሬ ወላጆቻቸው ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲያድጉ “ባይፈርዱባቸው” ኖሮ እንደ አብዛኛዎቻችን ልጆች ሁሉ ቢያንስ በዚህቺው በፈረደባት “ሃገረ-አሜሪካ” በሰላም መኖርና ከወላጆቻቸው ጋር በቅንጦት የመማር ሙሉ እድሉ የነበራቸውና ዛሬም መብቱ በእጃቸው መሆኑ ሲታሰበኝ ጭምር ነው፡፡

እጅግ ይልቁንም- እርግጥ ነው አብዛኛዎቻችን (ሁሉም ማለት በሚያስደፍር ሁኔታ) ከሃገር ከወጣንና በስደት መኖር በጀመርን ማግስት እንደ ተሞሸርንና ልጆችም እንደወላለድን ይታወቃል፡፡ህዝባችንም በአርምሞ ያያል(ምስጋና ለፌስ ቡክ)፡፡ ታዲያ እኒህ ልጆቻችን በአብዛኛው የተወለዱት ቢያንስ እንደ ሰው በክብር በሚያድጉበት ሃገርና እንደ “ዜጋ” በሚሳሳላቸው የሰለጠነው ዓለም ህዝብ እቅፍ ውስጥ ሲሆን እኛ የእነ አንዷለምና የእነ እስክንድር…. ጓዶች በእነርሱ የእስር ዋጋና በብልጣብልጥ ስደተኝነት ለልጆቻችን እንደ ዘመኑ አባባል  “አወዳደቃቸውን” እንዳሳመርንላቸው?  በተሰማኝ ጊዜ ነው፡፡

ከዛም ምን አለበት ታላቁ ደራሲ አቤ ጉበኛ ዛሬ በህይወት ቢኖሩልንና በወያኔ የግፍ አለንጋ የሚሰቃዩትን የአምላክ ንፁሃን ህፃናት በነፃነት፣ በፍቅርና፣ በሰላም እንዲኖሩና እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በወላጆቻቸው እቅፋና በፍቅራችን ልናሳድጋቸው የማንችል ከሆነ ከቶውንም ወደዚህ የሰቆቃ ህይወት እንዳናመጣቸው የሚመክርና የሚዘክር በ“አልወለድም” ፋንታ “አልወልድም”ን ቢከትቡልን እላለሁ፡፡ ማን ያውቃል እኛን “ስለደላን” ብቻ ወላልደን ከአላማ ማፈግፈግና የነፃነት ትግሉን ከማኮላሸት እንድን ይሆን ይሆናል፡፡

በመጨረሻም ስለ ውድ ወገናቸው ክብር፣ ነፃነትና፣ አንድነት ሲሉ ዘወትር የሚሳሱላቸውን እነዚያን ፍቅር የሆኑ ልጆቻቸውን ወላጅ አልባ፣ ደካማና፣ ጎስቋላ አድርገው እራሳቸውን ለወያኔ የማሰቃያ ካምፕ አሳልፈው የሰጡት የጀግኖቻችንን የአብራክ ክፋዮች ሰቆቃና እንግልት በምድራችን እስኪያከትምና ይልቁንም ነፃነት፣ እኩልነት፡ ፍትህና፣ ሰላም በኢትዮጵያ ሃገራችን እስኪሰፍን ድረስ በትግሉ እንፀና ዘንድ የእነ ናፍቆት፣ ኦማር፣ፍትህና፣ ጎህ … የእነ ሱመያ፣ ሩህና፣ ኢናስ… ጩሃት ሁላችንንም ግድ ሊለንና ዛሬም ከነፃነት ትግሉ ጎን እንድንሰለፍ ሊያስገድደን ይገባል እላለሁ፡፡ ለዛሬ አበቃሁ፡፡

ልጆቼ ናፍቆት፣ ኢናስ፣ ፍትህ …  ሁሌም እወዳቹሃለሁ! እግዚአብሔር አምላክ በሞገሱና በፍቅሩ ያሳድግልኝ፡፡ አሜን!

ጥር 2005 ዓ.ም ኮሎምበስ/ኦሃዮ

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on February 9, 2013
  • By:
  • Last Modified: February 9, 2013 @ 10:36 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar