www.maledatimes.com በወሬኞች የሚፈታ ትግል አይኖርም - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በወሬኞች የሚፈታ ትግል አይኖርም

By   /   February 9, 2013  /   Comments Off on በወሬኞች የሚፈታ ትግል አይኖርም

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 51 Second

የኢሳት የፌብሪዋሪ 10፣2013 የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ በኢትዮጵያ አንድነት ሬዲዬ ከስቶክ ሆልም ሲዊድን ” የዴያስፖራው ኮሜዲያን በኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል እየነገደ ነው” በሚል መሪ ቃል የተላለፈው መልዕክት በዋነኛነት እውቁ የነፃነት ተሟጋች፣ አክቲቪስትና አርቲስት ታማኝ በየነ በአውሮፓ ከተሞች በመዘዋወር የኢትዮጵያ ሕዝብ አይንና ጀሮ ለሆነው የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዥን የሚያደርገውን የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ስኬታማ እንዳይሆን ለመቃወም ሆን ተብሎ የተጠነሰሰና በአውሮፓ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ በዚህ እኩይ ተግባር እንዲተባበር ለመቀስቀስ ታልሞ የተዘጋጀ ነው::
በኢትዮጵያ አገራችን ያለው አምባገነን ስርዓት የሚያደርስብንን የመብት ረገጣና ጭቆና በኢትዮጵያ የሚኖረው ወገናችን ነፃ ከሆነ የዜና አውታር የማግኘት መብቱን ለማሳካት ቀና አመለካከት ባላቸው ዜጐች የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዥን /ኢሳት/ የተቋቋመበትን ዓላማ በብቃት  እየተወጣ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው::
በዚህም ተግባሩ በኢትዮጵያ የሚኖረው ወገናችን ነፃነቱንና መብቱን ለማስከበር ለትግል ራሱን እንዲያዘጋጅ ባደረገው አስተዋጽኦ በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ተወዳጅና በስፋትም ተደማጭ የዜና አውታር ለመሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምስክር ነው:: ሀቁ የሄ ሆኖ እያለ ኢሳት ትግሉን ለማዳፈን የተቋቋመ ተቋም ነው ተብሎ መግለጫ መሰጠቱ የአብየን ወደ እምየ አሰኝቶናል::
በአምባገነኖች ጭቆና ሥር የሚሰቃየው ወገናችን የሚያደርስበትን የመብት ረገጣና ጭቆና በነፃነት ሀሳቡን የሚገልጽበትን ነጻ እና እውነተኛ ሚዲያ፣ ኢሳትን የማጠናከሩ ሀላፊነት፣ ፍትህ እና ነጻነት የተጓደለበት የወገኑ ስቃይ የሚያንገበግበው ኩሩ የኢትዮጵያዊነት ተግባር በመሆኑ ዴያስፖራው ሀላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል::
ስለሆነም ኢሳት የእግር እሳት የሆነበት የወያኔ ሥርዓት ይህንን የዜና አውታር ለማጥፋት የሚያድርገው ተልካሻ ትንኮሳ አልተሳካለትም፣ ይህንንም የወያኔ እኩይ ተግባር ተቋቁሞ ኢሳት በመላው ዓለም መደመጥ የቻለው ዴያስፖራው ለማንና ለምን ገንዘቡን እንደሚያወጣ ጠንቅቆ በማወቁ በመሆኑ መካሪ አያሻውም፣ በወያኔ አስተሳሰብ የደነዘዘ ዴያስፖራ በማለት በዴያስፖራው ላይ በጅምላ የተሰነዘረው ተራ ዘለፋ እና በአንድነት ሬድዮ የቀረበው መግለጫ አዘጋጆች በሥራቸው ብቃት ምን ያህል የወረዱና ተስፋ የቆረጡ እንዲሁም በኢሳት እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ የተረበሹ መሆናቸውን ያሳያል::
ይሁን እንጅ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ በራቀ መልኩ በወገኖቹ ተወዳጅ የሆነውን የእውቁ የነፃነት ተሟጋች፣ አክቲቪስትና አርቲስት ታማኝ በየነን ሥምና የተቀደሰ ተግባሩን ጥላሸት ለመቀባትና ብሎም
በዴያስፖራው ለማስጠላት የተደረገው ትንኮሳ ለኢትዮጵያዊነቱ የሚታገልን ሕዝብ ትግል ለማደብዘዝ የተጠነሰሰ መርዛማና ከወያኔ ባልተናነሰ መልኩ ትግልን ለማዳፈን የሚደረግ ከደረጃ የወረደ ደባ ነው::በተጨማሪም ይኸው መግለጫ በኢሳትና በታማኝ ሰበብ ለዲሞክራሲ ለነፃነት ለፍትህ የሚታገሉ ድርጅቶችን ለመወረፍ ታቅዶ የተሰጠ መግለጫ መሆኑ ከራሱ ከመግለጫው ይዘት መረዳት ይቻላል የትግሉ ሜዳ ለማንም ነፃ ነው ታግሎ ማታገል ግን ብቃትንና ቆራጥነትን ይጠይቃል ዋናው የህዝብ ልብ ማሸነፍ ነው የወያኔ የእንጠፋፋ ፕሮፖጋንዳ አራማጆች እነሱ ለመሆናችውም ተግባራቸው ይገልፃል::
ከዚህ ባለፈ የመግለጫው አዘጋጆች ሊያውቁት የሚገባ ነገር ዴያስፖራው ማን ምን እየሠራ እንደሆነ ጠንቅቆ በማወቁ በወሬ የሚፈታ ኢትዮጵያዊ አለመኖሩን ነው፣ ለእኛ እናውቅልሃለን የወሬ ጋጋታ ቦታ የሚሰጥ የለም በእውነት ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚያስቡ ከሆነ ጊዜው የሥራ እንጅ የወሬ ባለመሆኑ ጊዜያችውን ለትግሉ መሳካት ቢያውለት ጠቀሜታ እንዳለው ሊገነዘቡ ይግባል::
በማጠቃለያ ኢሳት ዛሬም ነገም እንዲሁም ሁሌም ለኢትዮጵያ እውነተኛ እና ታማኝ ድምጽ ሆኖ በውድ እና በቆረጡ የኢትዮጵያ ልጆች አገልግሎቱ በተጠናከረ መንገድ ይቀጥላል ነገር ግን ከዚህ
አገራዊ ጥሪ እራሳቸውን አግልለው በስመ ነጻ አውጭ የወያኔ ጅራፍ ሆነው የሚጮሁ የኢትዮጵያ ሕዝብ የማይቀረውን ነጻነቱን ሲጎናጸፍ ከተጠያቂነት እንደማያመልጡ ሊገነዘቡ ይገባል!!!
የኢሳት የፌብሪዋሪ 10፣2013 የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም አስተባባሪ ኮሚቴ
ኖርዌይ፣ ኦስሎ ፌብሩዋሪ 08፣2013

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on February 9, 2013
  • By:
  • Last Modified: February 9, 2013 @ 10:48 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar