www.maledatimes.com አቶ ስብሓት ነጋ ፍርዳቸውን ሲጨርሱ. . . - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አቶ ስብሓት ነጋ ፍርዳቸውን ሲጨርሱ. . .

By   /   February 9, 2013  /   Comments Off on አቶ ስብሓት ነጋ ፍርዳቸውን ሲጨርሱ. . .

    Print       Email
0 0
Read Time:10 Minute, 49 Second
  • ‹‹ዕርቅ ለመፈጸም በማለት ሰዎችን ሲልኩ የነበሩ ቄሶች መሰቀል አለባቸው፡፡›› 

    Sebhat's Clock ticking to. . .

    ባለቀ ሰዓት፣ በተቆጠረ ዕድሜ.….

  • ‹‹ታምራት ቤተ ክርስቲያኒቱን ይቅርታ ሊጠይቅ አይችልም፡፡››
  • ‹‹[ሲኖዶስ ማቋቋም] በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከግራኝ ከጉዲት የባሰ ትልቅ  ወንጀል ነው፡፡››

(አቶ ስብሓት ዛሬ ለንባብ ከበቃው ላይፍ መጽሔት ጋራ ካደረጉት ቃለ ምልልስ)

ላይፍ፡- አንድ ጉዳይ እናንሣ፡፡ በአሜሪካን አገር የሚገኘው የኦርቶዶክስ ሲኖዶስም ኾነ አራተኛው ፓትርያሪክ ወደ አገር መምጣት የለባቸውም በማለት ደጋግመው ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ ይህ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባት አይኾንም?

አቶ ስብሓት፡- የተናገርኹት እንደ አማኝ እና እንደ ዜጋ የግል አመለካከቴን ነው፡፡ መጀመሪያ ፓትርያሪኩን ከኢትዮጵያ የሚያወጣቸው ምክንያት አልነበረም፡፡ ፓትርያሪኩ ኢሕአዴግ ይነካኛል የሚል እምነት አልነበራቸውም፤ ምክንያቱም እንደማንነካቸው ያውቃሉ፡፡ ብንነካቸው እንኳን መሰየፍ ነበረባቸው ወይም ገዳም ገብተው መመነን ነበረባቸው ወይም ኢየሩሳሌም መሄድ ነበረባቸው፡፡

Sebhat Nega

አቶ ስብሓት ነጋ

ይህንን ሁሉ ትተው በመጨረሻ ግን ወደ አሜሪካ ወሰዷቸው፡፡ ይህም ሳያንስ በቤተ ክርስቲያኒቷ ላይ ትልቅ ወንጀል በመፈጸም ሲኖዶስ አቋቋሙ፤ የእስልምና አክራሪ እንቅስቃሴን ደገፉ፡፡ እነዚህን ነገሮች ስሰማ ሐሳቤን ገለጽኹ፡፡

ይህ አድራጎት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከግራኝ ከጉዲት የባሰ ትልቅ ወንጀል ነው፡፡

ላይፍ፡- በአቡኑ ስደት ግን የመንግሥት እጅ እንደነበረበት የቐድሞው ጠቅላይ ሚኒትር አቶ ታምራት ላይኔ በመናገር ቤተ ክርስቲያኒቱን ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡

አቶ ስብሓት፡- /ሣቅ/ ታምራት ቤተ ክርስቲያኒቱን ይቅርታ ሊጠይቅ አይችልም፡፡ታምራት እንኳን ይህንን ሌላ ለመከታተል ጊዜ የነበረው አይመስለኝም፡፡ በእኔ እምነት ግን ኢሕአዴግ አቡኑን የሚነካበት ምክንያት አልነበረውም፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ የዕርቅ ምክክር አልነበረበትም፡፡ የአሜሪካውን ሲኖዶስ አውግዞ ሲያበቃ ዕርቅ ለመፈጸም ወደ አሜሪካ መሄዱ ስሕተት ነው፡፡ ዕርቅ ለመፈጸም በማለት ሰዎችን ሲልኩ የነበሩ ቄሶች መሰቀል አለባቸው፡፡ ዕርቅ ከነዚህ ጋራ መደረግ የለበትም፡፡ አሁን ቤተ ክርስቲያኒቱ የምትገኝበትን ኹኔታ ለፖሊቲካ ፍጆታ ለመጠቀም የሚጥሩ ብዙ ናቸው፡፡

ላይፍ፡- እናንተ ሥልጣን እንደያዛችኹ በጳጳስ ላይ ጳጳስ መሾማችኁስ ወንጀል አልነበረም?

አቶ ስብሓት፡- (በሣቅ አለፉት)

ሐራዊ ማስታወሻ፡- ቀድሞ የህወሓት መሥራችና አሁን የኣረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ሉዓላዊነት ፓርቲ አመራር አቶ ኣስገደ ገብረ ሥላሴ በዚህ ሳምንት ለወጣው ኢትዮ ምኅዳር ጋዜጣ በጻፉት ጽሑፍ÷ አዛውንቱን አቦይ ስብሓትን እንዲህ ሲሉ መክረዋቸዋል፡- ‹‹ሰውና ሰው ከሚያለያዩ ምናለ ወደ ቤተ ክርስቲያን ቢሄዱ?!››

መጨመርያ፡-

የቅዳሴ ተሰጥኦ ለድምፅ ፕራክቲስ ወይስ. . መዝሙር እና ዘፈንስ ምንና ምን ናቸው?

  • ‹‹እዛ ሁሌ ቤተ ክርስቲያን ስለማገለግል፣ ተሰጥኦ ስለምቀበልና ስለምጮኽ ያው ፕራክቲስ  እያደረግኹ ነው ማለትነው፡፡››
  • ‹‹መዝሙርና ዘፈን ለእኔ አይለያዩም፤ አንድ ናቸው›› /ነጻነት መለሰ ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ/

አዲስ አድማስ፡- ከሙዚቃው ብዙ ርቀሽ ስትመለሽ በድምፅሽ ላይ የተፈጠረ ችግር የለም? ምክንያቱም አሁን የነጻነት ድምፅ ትንሽ ጐርነን ብሏል የሚሉ አድማጮች አሉ፡፡

Netsanet Melese

ነጻነት መለሰ

ነጻነት፡- እውነት ለመናገር በድምፄ ላይ የተፈጠረ ችግር የለም፤ ምክንያቱምእዛ ሁሌ ቤተ ክርስቲያን ስለማገለግል፣ ተሰጥኦ ስለምቀበልናስለምጮኽ ያው ፕራክቲስ እያደረግኩ ነው ማለት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ድምፅ ሁሌም ካልሠራሽበት ክራክ እያደረገ ይመጣል፤ የታወቀ ነው፡፡ የምታንጐራጉሪና የምትዘፍኚ ከኾነ ድምፅሽ እንደተጠበቀ ይቆያል ማለት ነው፡፡ እንዳልኩሽ ቤተ ክርስቲያን ተሰጥኦ ስቀበል በጣም እጮኻለሁ፡፡ እዛ ማሪያም ቤተ ክርስቲያን አለች፡፡ በኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ የተሠራች እዛ አገለግላለሁ፤ ድምፄ በዚህ ምክንያት አላረፈም፡፡ የድምፄ ነገር ትንሽ ወፈር ብሏል፣ ግን የተጋነነ አይደለም፡፡

አዲስ አድማስ፡- ቀደም ሲል መንፈሳዊ መዝሙር ሠርተሽ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት በቃ ነጻነት ወደ ዘፈን አትመለስም የሚል አስተያየት ሲሰጥ ነበር፡፡ አንቺ አሁን “ልቤን” ብለሽ ወደ ዘፈን መጥተሻል፡፡ ከመዝሙር ወደ ዘፈን መምጣት ምን ዐይነት ስሜት አለው?

ነጻነት፡- መዝሙርና ዘፈን ለእኔ አይለያዩም፤ አንድ ናቸው ዋናው ልዩነታቸው የምንጠቀምባቸው ቃላት ናቸው እግዚአብሔር ለእኛ ድምፃችንን መክሊት አድርጐ እስከሰጠን ድረስ እግዚአብሔርን ልናመሰግንበት ይገባል የሚል እምነት አለኝ፡፡ እግዚአብሔር ፍቅር ነው፤ አታፍቅሪ አትባይም አግብተሽ በአንድ ተወስነሽ ኑሪ ነው ትእዛዙ፡፡
ስለዚህ የምትሰሪያቸው ነገሮች ትምህርታዊ እስከሆኑ ድረስ ከሃይማኖት ጋር የሚያጋጭ ነገር የለም፡፡ እኔም ብኾን ዕድገቴ በቤተ ክርስቲያን እንደመኾኑ መጠንና ቤተ ክርስቲያንን መርዳት ስላለብኝ የማገለግለው እግዚአብሔር በሰጠኝ ድምፅ በመኾኑ በተሰጠኝ ጸጋ እግዚአብሔርን እና ቤተ ክርስቲያንን አገለግላለኹ፡፡ በዚህ መሠረት ሁለቱም ለእኔ ልዩነት የላቸውም፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on February 9, 2013
  • By:
  • Last Modified: February 9, 2013 @ 8:27 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar