www.maledatimes.com የ፮ኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ የምርጫ መርሐ ግብር ዋና ዋና ነጥቦች - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የ፮ኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ የምርጫ መርሐ ግብር ዋና ዋና ነጥቦች

By   /   February 9, 2013  /   Comments Off on የ፮ኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ የምርጫ መርሐ ግብር ዋና ዋና ነጥቦች

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 23 Second

የ፮ኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ ዛሬ፣ ጥር 30 ቀን 2005 ዓ.ም በጽ/ቤቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ በዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪኩ ቡራኬ ሥራውን እንደጀመረ ያስታወቀውና በብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ሰብሳቢነት የሚመራው አስመራጭ ኮሚቴው፣ ዛሬ ከቀትር በኋላ በሰጠው ባለዘጠኝ ነጥብ ጋዜጣዊ መግለጫ ለ፮ኛው ፓትርያሪክ ምርጫ ሂደት የወጣውን የምርጫ መርሐ ግብር ይፋ አድርጓል፡፡

በዐቃቤ መንበሩ ጸሎት የተከፈተው የዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫው አስፈላጊነት÷ ‹‹የምርጫውን ሂደትና 6ኛው ፓትርያሪክ የሚሾሙበትን ቀን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን ግልጽ ለማድረግ›› እንደኾነም ተመልክቷል፡፡

ኮሚቴው ባወጣው የምርጫ መርሐ ግብር መሠረት፡-

  • እግዚአብሔር የወደደውን በመንበሩ ያስቀምጥ ዘንድ ከየካቲት 1 – 8 ቀን የጸሎት ጊዜ ነው፡፡
  • ከየካቲት 1 – 8 ቀን ከሊቃነ ጳጳሳት መካከል ከካህናትና ምእመናን ይፋዊ የዕጩ ፓትርያሪክ ጥቆማ በአካል በመቅረብና በፋክስ ይካሄዳል፡፡
  • የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በአስመራጭ ኮሚቴ ተጣርተው በቀረቡለት ዕጩ ፓትርያሪኮች ላይ ለመጨረሻ ጊዜ ለመወሰን የካቲት 16 ቀን ይሰበሰባል፡፡
  • በአስመራጭ ኮሚቴው ቀርበው የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤን ይኹንታን ያገኙት አምስት ዕጩ ፓትርያሪኮች የካቲት 18 ቀን 2005 á‹“.ም ለሕዝብ ይፋ ይደረጋሉ፡፡
  • የ፮ኛው ፓትርያሪክ ምርጫ ኀሙስ የካቲት 21 ቀን ተካሂዶ በዚሁ ዕለት ምሸት 12፡00 የተመረጠው አባት በብዙኀን መገናኛ ይፋ ይደረጋል፡፡
  • የተመረጠው አባት በዓለ ሢመት የካቲት 24 ቀን 2005 á‹“.ም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የልዩ ልዩ አብያተ ክርስቲያን መሪዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች፣ የኢ/ኦ/ተ/ቤያን ካህናትና ምእመናን በተገኙበት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል፡፡

ሌሎች የመግለጫው ዐበይት ነጥቦች፡-

  • አስመራጭ ኮሚቴው መሪ ዕቅዱን ለቋሚ ሲኖዶስ አቅርቦ አጸድ     ቋል፡፡
  • በምርጫ የሚሳተፉት ብ    ፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጥንታውያን ገዳማትና አድባራት፣ ካህናትና ምእመናን፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች እንዲሁም የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ጠቅላላ ቁጥር 800 ነው፡፡
  • የ6ኛው ፓትርያሪክ መራጮች ቁጥር ካለፉት አምስት የፓትርያሪክ መራጮች ቁጥር ጋራ ሲነጻጸር በእጅጉ የላቀ ነው፡፡
  • በውጭ የሚገኙ ካህናትና ምእመናን ለዕጩ ጥቆማ በፋክስ ቁጥር 011- 156-77-11 እና 011-158-0540 መጠቀም ይችላሉ፡፡
  • የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በወሰነው መሠረት የአራቱ አኀት አብያተ ክርስቲያን፣ የዓለም አብያተ ክርስቲያን ማኅበር፣ የአፍሪካ አብያተ ክርስቲያን ም/ቤት ተወካዮች እና በቋሚ ሲኖዶስ የሚመረጡ ምእመናን የአስመራጭ ኮሚቴ በሚሰጣቸው ልዩ መታወቂያ ምርጫውን እንዲታዘቡ ይጋበዛሉ፡፡
  • ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ሠራተኞች፣ ከአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ከሰንበት ት/ቤት እና ከማኅበረ ቅዱሳን የተውጣጡት 13 አባላት ያሉት አስመራጭ ኮሚቴ የተቋቋመው ታኅሣሥ 10 ቀን ነው፡፡

በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ የተገኙት የአስመራጭ ኮሚቴው አባላት፡-

asmerach com

ፎቶ ማኅበረ ቅዱሳን

ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ (ሰብሳቢ)፣ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ (ምክትል ሰብሳቢ)፣ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ (አባል)፣ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጩ (ጸሐፊ)፣ መልአከ ሰላም ዓምደ ብርሃን ገ/ጻድቅ፣ ጸባቴ ኀይለ መስቀል ውቤ፣ ንቡረ እድ አባ ዕዝራ ኀይሉ፣ አቶ ዓለማየሁ ተስፋዬ፣ ቀኝ አዝማች ኀይሉ ቃለ ወልድ፣ አቶ ታቦር ገረሱ፣ አቶ ባያብል ሙላቴ (ጋዜጣዊ መግለጫውን አስተናብረዋል) እና ዲያቆን ኄኖክ ዐሥራት ናቸው፡፡

ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መካከልም ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ፣ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ፣ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እና ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ተገኝተዋል፡፡

በጋዜጣዊ መግለጫው መጨረሻ የተለያዩ ስሜቶች ተነበዋል፤ ተደምጠዋል፡፡ አብዛኞቹ ጋዜጠኞች መርሐ ግብሩ በእጅጉ የተቻኮለ መኾኑን ከመተቸታቸውም በላይ ተመራጩ አስቀድሞ መታወቁን ሲነጋገሩ ተሰምተዋል፡፡

ተጨማሪ ዜናዎችን ይከታተሉ፡፡

የመግለጫውን ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ይመልከቱ

 

Page 01page 02page 03page 04 page 05

Share this:

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on February 9, 2013
  • By:
  • Last Modified: February 9, 2013 @ 8:32 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar