www.maledatimes.com አርቲስት በሃይሉ መንገሻ አለፈ ከየካቲት 1-1948 እስከ የካቲት 24 2005 - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አርቲስት በሃይሉ መንገሻ አለፈ ከየካቲት 1-1948 እስከ የካቲት 24 2005

By   /   March 3, 2013  /   Comments Off on አርቲስት በሃይሉ መንገሻ አለፈ ከየካቲት 1-1948 እስከ የካቲት 24 2005

    Print       Email
0 0
Read Time:21 Minute, 0 Second

ለረጂም ዘመናት በኢትዮጵያ የቴትር ሙያ ውስጥ ከፍተኛ ብቃቱን ያሳየው እና ሙያዊ ችሎታውን ያበረከተው አርቲስት በሃይሉ መነገሻ ከዚህ አለም ተለየ ።ከትውልድ ሃገሩ ወደ ሰሜን አመሪካ እስከ ገባበት ጊዜ ድረስ ጤንነቱ ተጓድሎበት ለረጂም ዘመናት በህክምና ሲታገዝ የቆየው አርቲስት በሃይሉ ከጊዜ በኋላ የ መስማት መሳን እና እንዲሁም የኩላሊት ችግር ብሎም በኩላሊቱ ላይ ካንሰር በመውጣት በሙሉ ጤንነቱ ላይ ከፍተኛ ችግር ገጥሞት ለዘመናት ሲሰቃይ መቆየቱ የማለዳ ታይምስ ምንጮች ይጠቁማሉ በሃይሉ በሰሜን አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ኑሮውን ቢያደርግም ከሚወደው የቴአትር ስራ የተለየው በህመም ምክንያት መሆኑን ይናገር ነበር ።በቴአትር የማስተርስ ድግሪውን ይዞ እስከ ከፍተኛ ማእረግ ድረስ የሄደው በሃይሉ በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ህይወቱ እንዳለፈች ከዋሽንግተን ዲሲ የደረሰን ሪፖርት ያሳያል በሚወጥለው መጭው ሳምንት ማክሰኞ የስራተ ጸሎት በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው በደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ስራተ ጸሎት እንደሚደረግ እና ፍታት ሊከናወን እንደሚችል የደረሰን ዘገባ ያመለክታል አስከሬኑ ወደ ሃገር ቤት ይሄድ አይሂድ የሚለው መረጃ ያልታወቀ ሲሆን አጠቃላይ ፕሮግራሙ ግን በቀድሞዎቹ የስራ ባልደረቦቹ አለምጸሃይ ወዳጆ እና ተክሌ ደስታ በኩል በማስተባበር ስራተ ፍታቱን ከቤተሰቦቹ ጋር ለማድረግ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ሪፖርቱ ያመለክታል ።ስለ በሃይሉ አጠቃላይ የህወት ታሪክ እንዲህ ቀንጨብ አድርገን አቅርበንላችኋል ።  በአዲስ አበባ ከተማ የካቲት 8 948 ዓ.ም ነው ተወለደው። ውልደቱ 6 ኪሎ ቢሆንም እድገቱ ሙሉ በሙሉ ጉለሌ ሩፋኤል አካባቢ ነው። የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በአዲስ አበባ መድኃኔዓለም ት/ቤት ነው ያጠናቀቀው።ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ አርቲስት አለም ፀሐይ ወዳጆ ጓደኛው ስለነበረች ወደ ሃገር ፍቅር ቲያትር ወስዳ ከነ ተስፋዬ አበበና መላኩ አሻግሬ ጋር አስተዋውቃዋለች።” የቲያትር ሙያ ላይ እንዳተኩር ያደረገችኝ እሷ ናት”እያለ ምስክርነቱን ይሰጥ የነበረው አርቲስት በሃይሉ መንገሻ ። በኋላም ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን 22ሺ ብር መድቦ አማተር ተዋንያን መልምሎ ሲያሰለጥን ከነ አለምፀሃይ ወዳጆ ፣ አለሙ ገብረአብ ፣ አስራት አንለይ ፣ ሲራክ ታደሰ ፣ ተክሌ ደስታ ፣ ትሩፋት ገ/ኢየሱስ ፣ አልማዝ ሰይፉ ፣ ተዘራ ውብሽት ፣ መሰለች ከበደና በሃይሉ መንገሻ ሆነው ስልጠናውን ይጀምራል ። በመሃሉ ባገኘው ዕድል ለሁለት ዓመት ወደ ታንዛንያ ዳሬሰላም ሄዶ ወታደራዊ ሳይንስና ማኔጀርነት ይማራል።
በኋላም ሃገሩ ተመልሶ ቲያትር ቤትም እየሰራ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ይጀምራል በወቅቱ ” ትግል ይቅደም ትምህርት ይቅደም” የሚባል የፖለቲካ ትግል ስለ ነበር አቋርጦ ወደ ራሺያ ይሄድና በሞስኮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ለአንድ ዓመት ቀጥሎም በሞስኮ የቲያትር ኪነ ጥበብ አካዳሚ አምስት አመት ተኩል ትምህርቱን ተከታትሎ በቴአትር አዘጋጅነት “ዳሬክተር የማስተር ኦፍ አርት” ማስትሬት ዲግሪውን አግኝትቷል።በሞያው ለበካታ ዓመታት በሃላፊነት በቤሄራዊ ትያትር ፣ በሃገር ፍቅር ቲያትር ፣
በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ሰርቷል። ከዚህ በተጨማሪ በአዘጋጅነት ፣ በተዋናይነት በርካታ ቲያትሮችን ፣ የቴሌቭዥን ፕሮግራሞችን በመስራት ለዘርፉ እድገት ከፍተኛ አስተዋፆ አድርጓል። አርቲስት በሃይሉ መንገሻ።
ለአርቲስት በሃይሉ መንገሻ እዚህ ሃገር ከመጣ በኋላ የመስማት ችግር ስላጋጠመው ብዙም ወደ ሙያው ዘልቆ ለመግባት እና ለመስራት አልቻለም ነበር ከዚያም በላይ ሌሎችም በሽታዎች ቢጫጫኑትም ህይወቱ እስካለፈችበት እለት ድረስ በህክምና እየታገዘ መቆየቱ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል ።

በ1979 አመተምህረት ጋብቻቸውን ያደረጉት ባለቤቱ  ወ/ሮ አለም እሸት ከዱ ቀደም ብለው ወደ አሜሪካ መጥተው ስለነበር እኔም ወደሰሜን አሜሪካ የመጣሁት የሚለው አርቲስት በሃይሉ መንገሻ ። በሶስተኛው ቀን ነው ወደ ሃኪም ቤት ነበር የገባው ። ወዲያው ሁለቱም ኩላሊትህ ስራ አቁመዋል ተብሎ “ዲያልየሲስ “ደሜ ከሰውነቴ ወጥቶ ተጣርቶ መመለስ እንደሚያስፈልገኝ” ተነገረኝ። ቅድመ ዝግጅት ሰርጀሪ ተደርጌ አስፈላጊዎቹ የላስቲክ ቱቦዎችን ተገጠሙልኝ። ከዚያም ሰነባብተው አንዱ ኩላሊትህ ካንሰር (develope) እያደረገ ነው ብለው በቀዶ ጥገና አወጡት። እንግዲህ ለተለያዩ ሕመሞቼ ከምወስዳቸው ኪኒኖች ውስጥ አንዱ በከፍተኛ ፍጥነት ሁለቱም ጆሮዎቼን አደነቆረኝ። በዚህ ጊዜ ከፍተኛ ችግር ላይ ወደኩ። ስራመድ ሁሉ መንገዳገድ ጀመርኩ ባለቤቴ ሶስት ወር ያህል ከስራ ቀርታ በየሃኪም ቤቱ እያሳከመችኝ ለምጠየቀው ጥያቄ መልስ እየሰጠች አስታማ የጆሮዬ ነገር የሞተ ጉዳይ ሆነ። እንግዲህ ካለ ኢንፎሜሽንና ኮሚኒኬሽን መንቀሳቀስ የማትችልበት አገር በመሆኑ ችግር አለው። በአንጻሩ የመስሚያ መሣሪያ ተገጥሞልኝ ትንሽ ትንሽ ይረዳኛል። ቲቪ ካፕሽን ስላለው እያነበብኩ እከታተላለሁ ቴክኖሎጂው ህይወትን ለማቅለል በብዙ መንገድ ይረዳል። በኋላም ልቤን ከሦስት አርትሪዎች ሁለቱ ጠበው ከሁለቱ ደግሞ አንዱ በጣም ስለጠበበ ቀዶ ህክምና አደረኩ።( እስቴንት) የሚሉት የልቤ አርትሪ ብረት ለቀለበት ገጥመውልኝ አሁን ድህና ነኝ። እግዚአብሔር ይመስገን ጓደኞቼ አብሮ አደጎቼ የባለቤቴ ዘመዶች ጓደኞች እየተመላለሱ እየጠየቁኝ አስታመውኛል እግዚአብሔር ይስጣቸው። ውለታቸው በደስታ ይከፈል እላለሁ እያለ አጠቃላይ ምስጋናውን ከአንደበቱ የማይለየው በሃይሉ መንገሻ  ስለ ሥራ ሕይወቱ ጠቅለል አድርጎ በማቅረብም ስለ እራሱ እንዲህ የተናገራቸው ነገሮች እንዲህ እናቀርበዋለን በኃይሉ ፡በመሠረቱ ስራዬ የቲያትር አዘጋጅ በመሆኑ ከዚሁ ከሙያው ጋር ግንኙነት ያላቸው ሥራ ላይ ነው ብዙ አመት ያገለገልኩት። በብሄራዊ የቴያትር ክፍል ሃላፊ የፕላንና ፕሮግራም የህዝብ ግንኙነትህ ኃላፊ የትያትር ቤቱ ዋና አዘጋጅና አርቲስቲክ ዳሬክተር በመሆን አገልግያለሁ። ከ984 በኋላ የክልል 4 ባህልና ስፖርት ቢሮ የሥነ ጥበባት ማስተባበሪያ ቡድን መሪ በመሆን ቴያትርን ሙዚቃን ሥነ ጽሁፍን ስዕልና ቅርጻቅርጽን በሚመለከት በሃላፊነት ከባለሞያዎች ጋር በመሆን በማደራጀት የሙያ ፈቃድ በመስጠት በመገምገምና የተለያዩ ስልጠናዎች ጭምር በመስጠት አግለግያለሁ። በቴአትርቤቶች መድረክ ላይ የሚቀርቡትን የቴአትር ቤቶቻችንን የጥበብ ውጤቶች መገምገም ደረጃቸውን እንዲጠበቁ በመቆጣጠር በመደገፍ በማበረታት በመምራትና ሙያዊ አገልግሎት መስጠት ሌላውን የስራ ድርሻዬ ነበር በማለት የስራ ድርሻውን በብቃት ተወጥቶ አልፎአል ።
በ 990 የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት (city hall) የቴአትርና ባህል አዳራሽ ዋና ስራ አስኪያጅ በመሆን በኋላም የባህልና የማስታወቂያ ቢሮ የቴያትርና የሲኒማ ከፍተኛ
ኤክስፐርትነት ተመድቤ ፈቃድ በመስጠት በማሰልጠን በተለይ እያበበ የመጣውን የቪዲዮ ሲኒማ እየገመገምን በሪፍሌክተር በቴአተር ቤቶቻችን አዳራሽ እንዲታዩ በመፍቀድ ዘርፉ እንዲስፋፋ አስተዋጽኦ አድርጌያለሁ ብሎአል።
በአዘጋጅነት የሎሬት ፀጋዬ ገ.መድኅንን « ጴጥሮስ ያችን ሰዓት » በሃገር ፍቅር ቴአትር “የፊታውራሪ መኮንን ዶሪ“ “የእጮኛው ሚዜ” በብሔራዊ ቴአትር ያስታጥቃቸው ይሁንን “አንቺን አሉ” በብሔራዊ ቴአትር የማክሲም ጎርኪን በረዳት ፕሮፌሰር አቦነህ አሻግሬ የተተረጎመውን “ቅኝት” በብሔራዊ ቴአትር የሻምበል ታምራት ገበየሁን ”ውጫሌ 7” በብሔራዊ ቴአትር የዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳን “ፍቅር በአሜሪካ” በብሔራዊ ቴአትር የሻምበል ፈቃድ ዮሐንስ “እቡይ ደቀመዝሙር” የተስፋዬ አበበን “የደም ቀለበት” በቴአትርና ባህል አዳራሽ የሰራዊት ፍቅሬን “የከርቼሌው ዘፋኝ” የአሰፋው አፅማት “የምሽት ፍቅረኞች“ ቴአትሮችን በቲአትር ባህል አድራሽ መድረክ አቅርቦአል።
በተዋንያንነት በሃገር ፍቅር ቲአትር የብርሃኑ ዘሪሁን ” የአርባ ቀኑ መዘዝ” የተስፋዬ አበበ ሙዚቃዊ ድራማ በሃገር ፍቅር ቲያትር የፀጋዬ.ገ/መድን”ሀሁ በስድስት ወር” ሁለተኛው የገፀ ባህርይ ምድብ በመሆን የተስፋዬ ሣህሉን ፣ አለሙ ገ/አብ፣ ጠለላ ከበደን ፣ አለምፀሐይ ወዳጆ ፣ አውላቸው ደጀኔን ፣ ሲራክን ታደሰ ፣ ወጋየሁ ንጋቱን ፣ ተክሌ ደስታ ጀምበሬ ጥላሁን ፣ አስራት አንለይ፣ ጌታቸው ይበልጣል ፣ በኃይሉ መንገሻ ፣ በመሆን በኋላ በወጣት ተዋንያን የተገነባውን ቲአትር ይዘን ጅማ ፣ መቱ ፣ አሰላ ፣ ድሬዳዋና ቡድናችንም ለድል በቅቷል። በግል የተለያዩ የቴአትር ክለብ የሚያዘጋጃቸውን ቴአትር በመገምገም የቴአትር ድርሰት (ስክሪፕት በመገምገም ፣ በማሰተካከልና በማስተማር ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቻለሁ። ሆኖም በሃይሉ ከአንጋፋዎቹ አርቲስቶች ጋር በጣም ጥልቀት ያላቸውን ስራዎች በመስራት ለኢትዮጵያ የቴአትር እድገት የራሱን አሥተዋጾ አድርጎአል። በተለይም በወቅቱ ስላሉ ወጣቶች ሲገልጽ የድሮዎቹንም ስራዎች መነካካቱን አይቀሬ ሆኖበት እንዲህ ብሎ ተናግሮ አልፎአል “ከነ ሎሬት ፀጋዬ በኋላ በ “ሀሁ በስድስት ወር”ተአምር ታየ። በዚያው  ቀጠለ። በርግጥ የስክሪፕት ( የቴአትር ጽሁፍ) ድርቀት አለ። በቋንቋም በሴራም  በገፀ ባህሪ አሳሳልም ብዙ ጠንካራ ባይሆኑም  ተመልካቹን እያረኩ ነው። ከሩቅ ቦታ በፀሐይና በዝናብ ወደ ቴአትር ቤት አድራሽ ባለበት አካባቢ እየተመላለሱ ካለ ውሎ አበል አንድ ምግብ ለሁለት ለሦስት እየበሉ በክፍላት ሃገር ቴአትር እያቀረቡ ይገኛል። ወጣቶች እንግዲህ መድረክ ሳይኖራቸው  ተቀጣሪ ሳይሆን የጥበቡ ፍላጎትና ዝንባሌ ይዞአቸው ከፍተኛ ጥረት በማድረግ አንዳንዶቹም ትልቅ ቦታ እየደረሱ ውጤት እያስመዘገቡ ይገኛሉ። የኢትዮጵያን የቲያትር ዕድገት ከፍተኛ ነው ብለው ከሚሉት ሰዎች አንዱ የነበረው በኃይሉ ፡ ዮፍታሄ ንጉስ ናቸው የዘመናዊ ቲያትር አባት። አቶ ተስፋዬ ገሠሠ በጥናት ጽሁፍ እንዳቀረበው ታዲያ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ብዙ ልፋትና ድካም ተደርጎለት  ብዙ የወቅቱ ወጣቶች እድሜአቸውን  ጨርሰውበት በዚያን ዘመን የነ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድኅን ፣ ደራሲ መንግስቱ ለማና ዘመነኞቻቸው መፈጠር የወቅቱ ወጣቶች እንደ ተስፋዬ ገሰሰ ደበበ እሸቱ ፣ ወጋየሁ ንጋቱ፣ አባተ መኮንን ፣ ተፈሪ ብዟየሁ ና ሃይማኖት አለሙ ወደ ውጪም  ሄደው ሙያቸውን በከፍተኛ ትምህርት ተክነው ወደ አገር ቤት መድረክ መጥተው መሥራት መጀመር ሙያው እንዲያብብ እንዲበለጽግ አድርጎታል። 

ESAT YeHager Lij Artist Behailu Mengesha 27 December 2012 Ethiopia

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 3, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 3, 2013 @ 10:56 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar