www.maledatimes.com ይህ ለአፋና እጅ የማይሰጥ የህዝብ ድምፅ ነው፡፡ ዳግም ተመልሰናል!! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ይህ ለአፋና እጅ የማይሰጥ የህዝብ ድምፅ ነው፡፡ ዳግም ተመልሰናል!!

By   /   March 9, 2013  /   Comments Off on ይህ ለአፋና እጅ የማይሰጥ የህዝብ ድምፅ ነው፡፡ ዳግም ተመልሰናል!!

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 56 Second

ይህ ለአፋና እጅ የማይሰጥ የህዝብ ድምፅ ነው፡፡
ዳግም ተመልሰናል!!
ለዜጎች ክብር የማይሰጠው ኢህአዴግ፣ ህዝብ በሚከፍለው ግብር መልሶ የሚያፍነው ኢህአዴግ፣ የሀይማኖት ተቋማትን ወደ ‹‹አጋር ፓርቲ››ነት እየቀየረ ያለው ኢህአዴግ ፍትህ ጋዜጣን እና አዲስ ታይምስ መፅሄትን በጉልበት ከነጠቀን በኋላ፣ ለሶስተኛ ጊዜ በሌላ ጋዜጣ ተመልሰናል፡፡ ጋዜጣዋ ‹‹ልዕልና›› ትባላለች፡፡ ከተመሰረተች ጊዜ ጀምሮ ለአንዴ ብቻ ታትማ ተቋርጣ ነበር፡፡ አሁን ግን የነበረባት የመንግስት ዕዳ ተከፍሎ፣ አሳታሚ ድርጅቱ በሀገሪቱ የአክሲዮን ሽያጭ ህግ መሰረት ወደ እኛ መዞሩን አበስራለሁ፡፡ እናም ዛሬ በዕለተ ቅዳሜ ለአንባቢያን ትደርሳለች፡፡ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ግን ‹‹አርብ አርብ ይሸበራል፤ …›› እንዲል ንጉስ ቴውድሮስ፣ ልዕልና ጋዜጣም የዕለት አርብ ድምፅ ሆና ትቀጥላለች፡፡
እንደመውጫም ይሆነኝ ዘንድ በአዲሷ ጋዜጣችን ላይ ‹‹ከተዘጋው በር ጀርባ›› በሚል ርዕስ ላቀረብኩት ፅሁፍ መግቢያ ያደረኩትን እዚህም ልድገመው፡-
እነሆ በሶስተኛው በር ተገናኝተናልና አብዝቼ አላማርርም፡፡ ባማርርስ የት እደርሳለሁ? ማነው አገዛዙንስ ከስሶ የረታ? ደግሞስ ከመቼ ወዲህ ነው በሀገሬ መሬት ላይ ህግ የበላይ ሆኖ የሚያውቀው? ለማንኛውም የጠፋው ብርሃን በዚህ መልኩ ዳግም ይፈነጥቅ ዘንድ ስለተከፈለው ዋጋ ወይም ውጣ ውረድ ገድል የመፃፍ ፍላጎት የለኝም፡፡ ፍላጎቴ ከባልደረቦቼ ጋ በፀና መንፈስ በጀመርነው ጎዳና እንተም ዘንድ የመንግስትን አፈና አውግዛችሁ የሞራል ድጋፍ ለሰጣችሁን ኢትዮጵያውያን፤ እንዲሁም የአለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት ተሟጋች ተቋማት ላሳያችሁት አጋርነትና ተቆርቋሪነት፣ በሀገሬ ላይ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ይሰፍን ዘንድ ዋጋ በከፈሉና እየከፈሉ ባሉ ወንድምና እህቶቼ ስም ልባዊ ምስጋናዬን ማቅረብ ነውና-ቺርስ ለነፃነታችን!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 9, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 9, 2013 @ 7:32 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar