www.maledatimes.com ከታምራት ገለታ የተወረሱት ከ1ሚ.ብር በላይ የሚያወጡ ወርቆች ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ተደረጉ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ከታምራት ገለታ የተወረሱት ከ1ሚ.ብር በላይ የሚያወጡ ወርቆች ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ተደረጉ

By   /   March 9, 2013  /   Comments Off on ከታምራት ገለታ የተወረሱት ከ1ሚ.ብር በላይ የሚያወጡ ወርቆች ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ተደረጉ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 34 Second

በሰው ግድያና በማታለል ወንጀል ሞት ተፈርዶበት የነበረውና በይግባኝ ወደ እድሜ ልክ እስራት ተቀይሮለት በማረሚያ ቤት የሚገኘው ታምራት ገለታ ወርቆች በየካራታቸው ተለይተውና ተጨፍልቀው ለብሔራዊ ባንክ ገቢ መሆናቸውን በፌደራል መንግስት የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አቶ አወቀ አበራ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ ወርቆቹ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ አላቸው ተብሏል፡፡

እንደ አቶ አወቀ ገለፃ፤ የግለቡ የንብረት ጉዳይ እስከ ሰበር ችሎት ድረስ ተኪዶ የፍርድ አፈፃፀም ውሳኔ ካገኘ በኋላ የርክክብ ሂደቶቹ በኤጀንሲው በኩል መከናወናቸውንና እስካሁንም በመንግስት ግዥና ንብረት አወጋገድ አገልግሎት በኩል ሁለት ተሽከርካሪዎቹ መወገዳቸውን ገልፀው፣ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ወርቆቹም በየካራታቸው ተለይተውና ተጨፍልቀው ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ሆነዋል – ብለዋል፡፡ አቶ አወቀ አክለውም በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን ፍቼ ከተማ ውስጥ የሚገኙት የግለሰቡ “አቢዶ” የተባለ ባለ ሶስት ኮከብ ሆቴልና መጠነኛ መኖሪያ ቤቱን ኤጀንሲው የተረከባቸው ሲሆን ለማስወገድ ጨረታ እንደወጣባቸውም ገልፀዋል፡፡ addis admass

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 9, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 9, 2013 @ 10:37 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar