www.maledatimes.com 2013 11:16 በህንፃ ግንባታ ላይ በደረሠአደጋ የ3 ሠዎች ህይወት ጠፋ አለማየሁ አንበሴ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

2013 11:16 በህንፃ ግንባታ ላይ በደረሠ አደጋ የ3 ሠዎች ህይወት ጠፋ አለማየሁ አንበሴ

By   /   March 9, 2013  /   Comments Off on 2013 11:16 በህንፃ ግንባታ ላይ በደረሠ አደጋ የ3 ሠዎች ህይወት ጠፋ አለማየሁ አንበሴ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 9 Second
በህንፃ ግንባታ ላይ በደረሠ አደጋ የ3 ሠዎች ህይወት ጠፋ

ባንቢስ አካባቢ ለረጅም ህንፃ ግንባታ እያገለገለ በነበረ “ሊፍት ክሬን” ላይ በደረሠ አደጋ 3 ሠዎች ህይወታቸው አለፈ፡፡ ባለፈው ረቡዕ ከቀኑ 9፡30 አካባቢ በደረሠው አደጋ የግንባታ ስራው አልቆ ሠራተኞች የመወጣጫ ሊፍቱን በማውረድ ላይ ሣሉ ነው አደጋው የደረሰው ብለዋል – የህንፃ ተቋራጩ ኩባንያ ጀነራል ፎርማን አቶ ግርማ ሚዳ፡፡ ብርሃኑ አለሙ የተባለው የጉልበት ሠራተኛ አስከሬን ከህንፃው ጀርባ በሚገኝ አንድ ፔንሲዮን ጣራ ላይ ቆርቆሮውንና ኮርኒሱን ደርምሶ በማለፍ አልጋው ላይ መገኘቱን የገለፁት አቶ ግርማ፤ አህመድ መሃመድ እና ክፍሌ ዋቢ የተባሉት ሠራተኞች በደረሰባቸው ከፍተኛ ጉዳት ጥቁር አንበሣ ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተደረገላቸው ሣለ ህይወታቸው ማለፉንና የሁሉም አስክሬን ወደየቤተሠቦቻቸው መላኩን አስታውቀዋል፡፡ የፔንሲዮኑ ግቢ ውስጥ ሆነው ከፍተኛ የጣራ ድብደባ ድምፅ መስማታቸውን የሚናገሩት የፔንሲዮኑ ባለቤቶች፤ ወዲያው የክፍሉን በር ከፍተው ሲመለከቱ በደም የተጨማለቀው የወጣቱ አስከሬን አልጋው ላይ ተጋድሞ ማግኘታቸውን ገልፀዋል፡፡ “ባማኮ” የተሠኘ የህንፃ ግንባታ ተቋራጭ በሚያስገነባው በዚህ ህንፃ ከዚህ ቀደም በደረሰ ተመሣሣይ አደጋ የአንድ ሠው ህይወት መጥፋቱን የአካባቢው ነዋሪዎች በግንባታ ወቅት አስፈላጊው የአደጋ ጥንቃቄ ሁሉ እንደሚደረግ የተናገሩት የድርጅቱ ጀነራል ፎርማን፤ ሠራተኞችም የአደጋ መከላከያ አድርገው እንደሚሠሩ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 9, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 9, 2013 @ 10:38 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar