www.maledatimes.com በሐረር ከፎቅ የተገፈተረችው የቤት ሠራተኛ በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ ነች - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በሐረር ከፎቅ የተገፈተረችው የቤት ሠራተኛ በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ ነች

By   /   March 9, 2013  /   Comments Off on በሐረር ከፎቅ የተገፈተረችው የቤት ሠራተኛ በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ ነች

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 38 Second

ጥርሶቿ ረግፈዋል፤ ጉልበቷ ተሰባብሯል ተጠርጣሪዋ ከእስር እንድትለቀቅ ተደርጓል መታሰቢያ ካሣዬ (ከድሬዳዋ) በሐረር ከተማ፣ ፈረስ መጋላ አንደኛ መንገድ በተሰኘው አካባቢ በቤት ሠራተኛነት የተቀጠረች የ12 ዓመቷ ሰሚራ አብዲ በአሠሪዋ ከፎቅ ላይ ተወረወረች፡፡ ታዳጊዋ በውርወራው ጥርሶቿ ረግፈው፣ ጉልበቷም ተሰባብሯል፡፡ ተጠርጣሪዋ ከእስር መለቀቋን ፖሊስ ተቃውሟል፡፡ በመቶ ብር የወር ደሞዝ ለመስራት ገብታ ሁለት ሳምንት እንደቆየች ነው ችግር የተፈጠረው፡፡

አሰሪዋ ሶፍያ መሃመድ መቶ ብር ጠፍቶባት ህፃኗን ወስደሽብኛል ትላታለች፡፡ ህፃኗ ሰሚራ ገንዘብ እንዳልሰረቀች ብትናገርም ተፈተሸች። ምንም አልተገኘም፡፡ በዚህ ተበሳጭታ ልጅቷን ከ3ኛ ፎቅ መኖሪያ ቤት ወርውራታለች ተብላ የተጠረጠረችው ሶፍያ መሃመድ፣ በፖሊስ ከተያዘች በኋላ ተለቃለች፡፡ ሠሚራ አብዲ ጥርሶቿ በሙሉ የረገፉ ሲሆን ጉልበቷም ተሰባብሯል፡፡

ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባት ኮማ ውስጥ የነበረችው ሰሚራ፤ ድሬዳዋ ተወስዳ በኢትዮ ጅቡቲ የምድር ባቡር የፈረንሳይ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላት ነው። በቦታው ያገኘናት ሲስተር ሂሩት እንደምትለው፤ ሰሚራ ወደ ሆስፒታል ስትመጣ እጅግ ተዳክማ ራሷን አታውቅም ነበር፡፡ ህጻኗ የመሻሻል ሁኔታ እየታየባት መሆኑን የተናገረችው ሂሩት፤ ስለ ጉዳቷ መጠንና ስለ ጤንነቷ ሁኔታ ሙሉ መረጃ መስጠት የሚችሉት ህክምና የሚያደርጉላት ዶክተሮች እንደሆኑ ጠቁማ፤ በጥቅሉ ግን ጉልበቷ መሰባበሩን እና 12 ጥርሶቿ መርገፋቸውን ገልፃለች፡፡

በተጠርጣሪነት በፖሊስ ተይዛ የተለቀቀችው ወ/ሮ ሶፍያ መሃመድ ሆስፒታሉ በመምጣት ሰው በሌለበት አሳቻ ሰዓት ገብታ ህፃኗን ለማባበልና ለማስፈራራት እንደሞከረች ሲስተር ሂሩት ገልፃ አሁን ግን ለህፃኗ ጥበቃና ክትትል እየተደረገላት ነው ብላለች፡፡ መርማሪ ፖሊስ ምክትል ሳጅን ኻሊድ አብድልፈታ የሱፍ፤ ምርመራው ሳይጠናቀቅ ተጠርጣሪዋ እንድትለቀቅ የከተማው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቃል ትዕዛዝ እንደሰጠ ገልፀዋል፡፡ ተጎጂዋ ህፃን አደገኛ ሁኔታ ውስጥ እያለችና የፖሊስ ምርመራው ሳይጠናቅቅ ተጠርጣሪዋ ከእስር መለቀቋ አግባብ አይደለም፤ በህጻኗ ደህንነት ላይም አደጋ ሊያመጣ ይችላል ብለዋል – መርማሪ ፖሊሱ፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 9, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 9, 2013 @ 10:45 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar