www.maledatimes.com የሰማያዊ ፓርቲ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በመንግስት ሃይሎች እንዲበተን ተደረገ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሰማያዊ ፓርቲ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በመንግስት ሃይሎች እንዲበተን ተደረገ

By   /   March 10, 2013  /   Comments Off on የሰማያዊ ፓርቲ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በመንግስት ሃይሎች እንዲበተን ተደረገ

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 19 Second

በትላንትናው እለት በዋቢ ሸበለ ሆቴል ሊደረግ ታስቦ የነበረውን የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም  በመክፈቻው ሰአት የምንግስት ሃይሎች ከዋቢሸበሌ ሆቴል ባለቤት ጋር በመነጋገር እና በማስፈራራት ፕሮግራሙ እንዳይደረግ ማድረጋቸውን የማለዳ ታይምስ ዘጋቢ በስልክ ያነጋገራቸው የሰማያዊ ፓርቲ አባሎች ገልጸዋል ። በዋቢሸበሌ አዳራሽ ውስጥ ከ 15 ሰዎች በላይ ገብተው ሌሎቹ ደግሞ በሪሴፕሽን አካባቢ የዝግጅቱን መጀመሪያ ሰአት በመጠባበቅ ላይ ሳሉ ዝግጅቱ ባልተጠበቀ ሁኔታ እና በድንገተኛ ችግር እንደተቋረጠ ከባለቤቱ ከአቶ በእደማርያም (የቀዳማዊ ሃይለስላሴ የልጅ ልጅ) ለፓርቲው አመራር አካላቶች እና ደጋፊዎች መናገራቸውን ጠቁመው ሲናገሩም ከውስጣቸው ፍርሃት እና ድንጋጤ ይታይባቸው ነበር ብለዋል ።በወቅቱ ለሆቴሉ አዳራሽ የተከፈለውንም ክፍያ አስመልክቶ ለመናገር ባለመቻላቸው ከመንግስት አካላቶች የማስፈራሪያ ቃል እንደደረሳቸው የሚጠቁም ሲሆን እንዳትመልስ መባላቸውንም ያሳያል ብለዋል ።በሌላ በኩሉም እንደ ሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች አገላለጽ ከሆነ መንግስት እየተከታተለ ሆቴል ገብታችሁ እራት መብላት አትችሉም መባል እራሱ በሃገሪቱ ያለውን የመብትን መጋፋት እና የነጻነትን ማጣት በጉልህ ያሳያል ሲሉ አክለው ገልጸዋል ።ይህ በእንዲህ እንዳለ የሰማያዊ ባርቲ የዚህ ስብሰባ እቅድ ከ ሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ የገንዘብ ማሰባሰብ እቅድ ፕሮግራም የነበረው ሲሆን ባለ1000 ብር ትኬት 200 ሰዎች አካባቢ ገዝተው ዝግጅቱን ሲጠባበቁ እንደነበር ጠቁመዋል ። በዚህ ፕሮግራም ላይ የወጣውን ወጪ እንኳን የማይመልስ ገንዘብ እጃችንም ላይ ቢገባም ለሙዚቀኞች እና ለሌሎች ነገሮች ያወታናቸውንም ችምር እንድናጣ መንግስት አድርጎናል ሰማያዊ ፓርቲ እንዳያድግ እንዲቀጭጭና ከምድረ ገጽ እንዲጠፋ የሚያደርግ ስልት እየተጠቀመ ይገኛል እንዲህ ያለ አረመኔአዊ መንግስት አይተንም ሰምንተንም አናውቅም በማለት አክለዋል ።ከዚህ ይልቅ የመሰብሰብ መብት የላችሁም ብለው ቀድመው ቢነግሩን መፍትሄ እናፈላለግ ነበር ሲሉም ጠቁመዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 10, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 10, 2013 @ 11:00 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar