www.maledatimes.com ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ የጥይት ድምጽ ስለሌ ነው እንጂ ኑሮው እራሱ ጦርነት አይደል እንዴ?›› ጽዮን ግርማ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ የጥይት ድምጽ ስለሌ ነው እንጂ ኑሮው እራሱ ጦርነት አይደል እንዴ?›› ጽዮን ግርማ

By   /   March 10, 2013  /   Comments Off on ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ የጥይት ድምጽ ስለሌ ነው እንጂ ኑሮው እራሱ ጦርነት አይደል እንዴ?›› ጽዮን ግርማ

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 42 Second

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ የጥይት ድምጽ ስለሌ ነው እንጂ ኑሮው እራሱ ጦርነት አይደል እንዴ?›› ጽዮን ግርማ
ከአንድ ወር በፊት ይመስለኛ አንዲት ጓደኛዬ ቤት ቡና ከምሳ ጋር ተጋብዤ ጎራ አልኩ፡፡ ለወትሮው እንግዳ በማስተናገዷ የምትደሰተው ቀላ ያለችው ልጅ መልክ የጓደኛዬ የቤት ሠራተኛ ለቡናው የሚያስፈልጉትን ዕቃዎች እያቀራራበች ትጉረመረማለች፤‹‹ዛሬ ምን ሆነሻል ትዕግስት?›› አልኳት ‹‹ምን ያልሆንኩት አለ ሁሉን ነገር ከጨረስኩ በኋላ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ እኮ ፍቃድ አልሰጥም አለ›› አለችኝ ወደ አረብ አገር ለመሄድ እንቅስቃሴ መጀመሯን አውቃለሁና ‹‹ለምን የሚወስድሽ ድርጅት ፍቃድ የለውም?›› አልኳት ጓደኛዬ ቤት በሄድኩ ቁጥር ይቺ ልጅ አረብ አገር የመሄድ ሐሳቧን እንድትለውጥ ብዙ ወትውተን ፈቃደኛ ባለመሆኗ ቢያንስ በሕጋዊ ድርጅት በኩል እንድትሄድ አብዝተን መክረናት ነበርና ለዚህ ነበር ስለሕጋዊነቱ የጠየኳት፤‹‹ኧረ በደንብ ነው ፈቃድ አለው›› አለችኝ፡፡ ‹‹ታዲያ ለምን ተከለከልሽ?›› ስላት ‹‹ኢራቅ ውስጥ ጦርነት ስላለ አንፈቅድም አሉ›› አለችኝ፡፡ ቀጠል አድርጋም ‹‹ደግሞ ተቆጣጥረው ልባቸው ወልቋል በአጭር ቀን ውስጥ ሄጄ ካላሳየኋቸው›› ስትል ዛተች ‹‹መንግሥት ተከታትሎ እንዲህ ጦርነት ያለበት አገር ዜጎቼን አልክም ካለማ ጥሩ ነው፤ ጦርነት ነው ከተባለ ደግሞ ብትቀሪ ይሻላል›› ስል እንደለመድኩት ልመክር አፌን አሾልኩ፡፡ትዕግስት በንዴት እየተርገፈገፈች ‹‹ውይ ድንቄም አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የጥይት ድምጽ ስለሌ ነው እንጂ ኑሮው እራሱ ጦርነት አይደል እንዴ?›› ስትል በአንድ ጊዜ መልስ አልባ አድርጋኝ ነበር፡፡የትዕግስት መልስ እንዲሁ እንደገረመኝ ለጓደኞቼ ጭምር ሳወራው ከረምኩ ዛሬ የእግረመንገድ ቡና በዚችው ጓደኛዬ ቤት ተጋብዤ ጎራ አልኩ፡፡ ቡናው በአዲስ ፊት እየተፈላ ነው፡፡‹‹ትዕግስትስ?›› ስል ጠየኩ ‹‹ውይ ሄደች እኮ›› አሉኝ የት ስል ‹‹ኢራቅ›› ተባልኩ ክው አልኩ ለካ እውነቷን ነው ‹‹…ድንቄም ጥበቃ…›› ያለችው ያንቀን ያለችኝን ዛሬ መልሼ አስታወስኩ ‹‹ውይ ድንቄም አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የጥይት ድምጽ ስለሌ ነው እንጂ ኑሮው እራሱ ጦርነት አይደል እንዴ?››

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 10, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 10, 2013 @ 11:18 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar