www.maledatimes.com የሰማዕታት መታሰቢያ ቀን – ሀ ,የሰማዕቶቻችን መታሰቢያ ቀን ያለንበትን ሀቅ እንድንመረምር ይጠይቀናል፤ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሰማዕታት መታሰቢያ ቀን – ሀ ,የሰማዕቶቻችን መታሰቢያ ቀን ያለንበትን ሀቅ እንድንመረምር ይጠይቀናል፤

By   /   March 13, 2013  /   Comments Off on የሰማዕታት መታሰቢያ ቀን – ሀ ,የሰማዕቶቻችን መታሰቢያ ቀን ያለንበትን ሀቅ እንድንመረምር ይጠይቀናል፤

    Print       Email
0 0
Read Time:40 Minute, 45 Second

semaetatየሰማዕታት መታሰቢያ ቀን –  ሀ ግጥም ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ

የሰማዕቶቻችን መታሰቢያ ቀን ያለንበትን ሀቅ እንድንመረምር ይጠይቀናል፤
ዛሬ የካቲት ፲ ፯ ቀን ፳ ፻ ፭ ዓመተ ምህረት ነው። ያለቀኑና ያለቦታው የምናከብረውን የሰማዕቶቻችንን መታሰቢያ ቀን ልትዘክሩ የተገኛችሁ ውድ ኢትዮጵያዊያን እንኳን ደህና መጣችሁ።
የጣሊያን ፋሽስት ወራሪ በኢትዮጵያዊያን ላይ ያደረሰውን ግፍ በየዓመቱ ስናስታውስ፤ የወደቁ ሰማዕቶቻችንን እንዘክራለን፣ ከዚያ የምንማረውን ደግመን ደጋግመን እንመረምራለን እናም ወገናችን በዚያ ሁኔታ በድጋሜ እንዳይወድቅ እናሰላለን። እኛ በዛሬው ቀን የሰማዕቶቻችንን መስዋዕትነት የምንዘክረው በስደት ሆነን ነው። በስደት በምናከብርበት ቦታ፤ በስደት ላይ መሆናችን ያንገበግበናል። ስደታችንን ከሰማዕቶቻችን መስዋዕትነት ጋር ማዛመዱ የግድ ነው። ሕይወታቸውን የሰጡት እኛ በስደት እንድንሆን አልነበረም። ሕይወታቸውን የሰጡት በስደት ሆነን እንድንዘክራቸው አልነበረም።
አሁን ያለንበትን ሀቅ ስንመረምር፤ በጣሊያን ቅኝ ገዥዎች ዘመን ከኖሩት ወገኖቻችን ኑሮ ጋር የሚመሳሰሉ ብዙ ክስተቶች እናያለን። ጣሊያን ኢትዮጵያን ለመግዛት መሠረታዊ መመሪያ ያደረገው፤ ሕዝቡን መከፋፈልና አንዱ ባንዱ ላይ እንዲነሳ በማጣላት ነበር። ለጣሊያን ፋሽስቶች፤ የእምነት ተከታዮችን ባጠቃላይ፤ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት እና የእስልምና ተከታዮችን በተለይ ነጥሎ ማጥቃት፤ የአስተዳደራቸው መመሪያ ነበር። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥትስ ምን እያደረገ ነው? የጣሊያን ፋሽስት በበተናቸው በራሪዎቹ፤ የሸዋ አማራ ገዥዎችና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሰባኪዎች ዋና ጠላቶቼ ናቸው ብሎ ነበር። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር አባት፤ ስብኀት ነጋ ደግሞ፤ በ፲ ፱ ፻ ፹ ፫ ዓመተ ምህረት ለፈረንሳዩ ጋዜጠኛ ሬኔ ሌ ፎርት በሠጡት ቃል፤ “እኛ የስክሱም የዘውድ ሥርዓት ወራሾች ነን። ከዚህ የሸዋ አማራ መንግሥት ጋር የሚያገናኘን አንዳችም ነገር አይኖረንም።” ብለዋል። ቀጥሎም አማራንና ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን አንበረከክነው ብለው ፎክረዋል። ይኼ ያመሳስላሉቸው ይሆን?
ጣሊያን ኢትዮጵያን ለመግዛት አስተዳደሩን የከፋፈለው በቋንቋ መሠረት ነበር። አሁን ሀገሪቱን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት እንዴት ከፋፍሎ እየገዛት እንደሆነ እኔ ከናንተ የበለጠ አላውቅምና ለናንተ እተወዋለሁ። በርግጥ፤ የፋሽስቱ የቅኝ ግዛት ዘመን ነበር። ኢትዮጵያ የምትባል የለችም፤ ያለው የጣሊያን ንጉሠ ነገሥት ግዛት ነው፤ ነበር ያለው።የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ደግሞ፤ ኢትዮጵያዊ የሚባል ሕዝብና ሀገር የለም ያለው የብሔርና ብሔረሰቦች ሀገርና ሕዝቦቻቸው ነው ብሏል። እናንተው ፍረዱ። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር አባላት አዲስ አበባ የገቡት፤ የደርግ አረመኔነትና ደደብነት መንገዱን ክፍት ስላደረገላቸው እንጂ፤ ኢትዮጵያን ፈልገው ወይንም ተልመውት አልነበረም። ስለ ትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት አገዛዝ ካነሳን ዘንዳ፤ ፋሽስቱ ጣሊያን፤ አስካሪሶቹን ይዞ፤ በኢትዮጵያዊያን ላይ፤ ማንነትን የሚያራክስ ስድብ እያወረደ፣ ኢሰብዓዊ የሆነ ድብደባ፣ ማጉላላት፣ ማሰቃየት፣ ያለሕግ ማሠር፣ ንብረት መውረስ፣ ሴትን መድፈር፣ ቤት ማቃጠል፣ ሬሳ መጎተት፣ ሰውን ማንጠልጠል፣ ሰውን ገደል መክተት፣ ሰብዓዊ ዕርዳታን መንፈግ፣ የእምነት ቤቶችን ማቃጠል፣ ረሃብን ማስፋፋት፣ ሰዎችን በግልፅና
በድብቅ መግደል፣ ሁሉንም በየዓይነቱ በሞሶሎኒ ስም አካሂዷል። የፋሽስቱን ግፍ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ፤ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው ስንዘክረው እንገኛለን። ታዲያ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥትስ፤ በትግሬዎች ነፃ አውጪነት ስም ምን የተለዬ እያደረገ ነው? የጣሊያኑ ፋሽስት ወራሪ ከአርባ ዓመት በፊት፤ በአፄ ሚኒሊክና በእቴጌ ጠሀይቱ ብጡል በአድዋ ላይ ድል መደረጉ ዘለዓለም እየቆጨው፤ ቂም ይዞ፤ ኢትዮጵያን ለማጥፋት እንደገና እየበረረ መጣ። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባርም አፄ ሚኒሊክና እቴጌ ጠሀይቱ ብጡል በአድዋ ላይ ጣሊያንን ድል ሲያደረጉ በትግራይ ላይ ዘመቱ የሚል ቂም ይዞ፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያዊነት ለኛ ምን ያደርግልናል በማለት የተነሳ ለመሆኑ፤ መሥራችና መሪያቸው የነበረው ዶክተር አረጋዊ በርሄ ተናግሯል።
የጣሊያኑ ፋሽስት የሀገሪቱን አስተዳዳሪዎች፣ የኢኮኖሚውን ዘርፍ ሥራ አስኪያጆች፣ ገዳዮችና ዘራፊዎች በሙሉ ጣሊያኖችንና አስካሪሶቹን ነበር ያደረገው። አሁንስ በትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ሥር የሀገራችን አስተዳደር፣ የኢኮኖሚው ዘርፍ ሥራ አስኪያጆች፣ ገዳዮቻቸውና ዘራፊዎቻቸው የጣሊያን ሹምባሽና ቁልባሽ ልጅና የልጅ ልጆች አይደሉምን? ከሕጻንነታቸው ጀምሮ በየቤታቸው ግድግዳ ላይ ተለጥፎ እያመለኩ ያደጉት የፋሽስቶቹ ፎቶግራፍ ያስተማራቸው ነው። የመለስ ዜናዊን ባንዳ አያት፤ የአቶ ዜናዊ አስረስን ባንዳ አባት፤ ካለቆቻቸው ፋሽስቶች ጋር የተነሱት ፎቶግራፍ በበሩ ላይ ተሰቅሏልና፤ ይመልከቱ። የጣሊያን ፋሽስት፣ የተማሩ ኢትዮጵያዊያንን ጨርሷል። ጣሊያን አስካሪሶቹንና ተላላኪዎቹን፤ በቅኝ ግዛት አስተዳደሩ፤ ከአራተኛ ክፍል በላይ እንዲማሩ አይፈቅድላቸውም ነበር። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥትም ከተማሩት ወገኖቻችን ጋር ምን ዓይነት ግንኙነት እንዳለው እኔ ለናነተ አልሰብክም፤ ታውቁታላችሁና። የተማሩ ኢትዮጵያዊያንን ከሥራ ቦታቸው ማባረር፤ ስማቸውን ማጥፋት፣ በማንኛውም የሥራ መስክ ሠርተው እንዳይተዳደሩ ማድረግ፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት እኩይ ተግባሩ ነው። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት፤ ኢትዮጵያዊያን ከአሥረኛ ክፍል በላይ እንዳይማሩ ገደብ አድርጓል።
የኢትዮጵያን ለም መሬት በሚመለከት፤ የጣሊያን እቅድ የነበረው፤ የሀገራችንን ለም መሬት ከልሎ፤ እህል ማምረቻ በማድረግ፤ እህሉን ወደ ጣሊያን በማጓዝ ጣሊያንን ለመመገብ ነበር። አሁን ደግሞ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት፤ ነዋሪዎቹን ነጥቆ በማባረር፤ ለሙን መሬት ለሕንድ፣ ለአረቦች፣ ለፓኪስታንና ለቻይና በመስጠት፤ እህል እንዲያመርቱበት በማድረግና እህሉን ወደ ሀገሮቻቸው ጭነው ሕዝባቸውን እንዲመግቡ መፍቀዱ ያመሳስላቸዋል እላለሁ።
ጣሊያን የኢትዮጵያዊያንን ጳጳስ ረሽኖ የራሱን የሃይማኖት መሪ አስቀመጠ። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ቀኖና ሽሮ፤ በሕይወት ያሉትን ፓትርያርክ ደፍሮ የራሱን አባል አስቀመጠበት። ከላይ እስከ ታች፤ የኢትዮጵያ ተዋሒዶ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የቤተክህነት መሪዎች ማን እንደሆኑ ታውቃላችሁ። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት፤ በእስልምና ሀይማኖት ተከታዮቻችን የውስጥ
አስተዳደር ገብቶ፤ የራሱን ምልምሎች መሪዎች አድርጎ በመመደብ እያሰቃያቸው መሆኑን፤ እኔ ለናንተ አልነግርም።
እንግዲህ አንድ ነገር ከዚህ፤ ሌላ ነገር ከዚያ፤ በተቃውሞ የተጀመረው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ፤ ወደ ከፍተኛ አመፅ እየተሸጋገረ ነው። በግንቦት ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ ዓመተ ምህረት ምርጫ፤ ድምፃችን ይሰማ፤ ምርጫችን ይከበር ነበር ሕዝቡ ያለው። የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከመጀመሪያው አንስተው፣ በኤርትራ ጉዳይ አልፈው፣ በየቅጥር ግቢያቸው ውስጥ ባሉና ሀገራዊ በሆኑ ጉዳዮች መጮኻቸውን አቁመው አያውቁም። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሒዶ ክርስትያን እምነት ተከታዮች ዘንድ፤ ገና ሀ ሲባል፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ማጥቃቱን፤ መነኮሳት፣ ቀሳውስትና የዕምነቱ ተከታዮች ደግሞ አቤቱታቸውን አላቆሙም። በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የሚያደርገው ዘመቻ፤ ታላቅ አመፅ አስነስቶበት፤ መፋጠጡ አድጓል።
ይህ ሁሉ የተለያዬ የሚመስለው ሕዝባዊ መነሳሳት፤ ወደ አንድ አቅጣጫ በፍጥነት እየተጓዘ ነው። ልብ ብሎ ላጤነው፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥትን ፍፃሜ ሊሠጠው በር እያንኳኳ ነው። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት እንደማንኛውም የአምባገነን መንግሥት በዱላ አምልኮ፣ በዱላ ገዝቶ፣ በዱላ ለማለቅ ማተቡን አስሯል። ይኼ የዱላ አባዜ የአምባገነኖች ያንገት ማተባቸው ብቻ ሳይሆን፤ በደም ሥሮቻቸው የሚፈስ አንቀሳቃሽ ሕይወታቸው ነው። እናም ፍፃሜያቸው እየተቃረበ መሆኑን እያወቁ፤ አሁንም በጡንቻችን የታሪክን ወደፊት ጉዞ፤ ወደኋላ እንመልሳለን ብለው ይሟገታሉ። በዚህ አድራጎታቸው ወጣት ኢትዮጵያዊያንን ገዳዮችና ተገዳዮች እያደረጉ ነው። እነሱ የሀገሪቱን ሀብት እየቦጫጨቁ ወደ ጉያቸው፣ ወደ ወገናቸውና ወደ ውጪ እያጓዘ፤ ወጣቱን ለነሱ እንዲሞትላቸው እያሠለፉት ነው። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት በዚህ እንቅስቃሴ ማግሥት፤ አቸናፊ ሆኖ አይወጣም። በሰላም ሥልጣኑን በመጋራትና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን በማስፈን ታሪኩን ማሳመር የሚችልባቸው ዕድሎቹ በተደጋጋሚ ከፊቱ እየቀረቡለት፤ ገፍትሮ ጥሏቸዋል። አምባገነኖች ከታሪክ አይማሩምና፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥትም የኢትዮጵያን ሕዝብ፤ “ምን አባታቸው ሊሆኑ?” “የት ሊደርሱ?” “ምን አቅም አላቸው!” በማለት እብሪቱን እየገፋበት ይገኛል።
ራሱን ወካይ አድርጎ ያቀረበውን የትግራይ ወገናችንን ብንተውለት እንኳ፤ ከሞላ ጎደል ዘጠና አራት ከመቶ የሚሆነውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በፖለቲካው ማኅደር ያላካተተ ሥርዓት፤ እድሜው በአጭር መቀጨቱ አስገራሚ አይሆንም። በዚህ አጭር ሕይወቱ፤ የሀገራችንን ንብረት አሟጦ መሸልቀቁ፣ ሕዝቡን ከፋፍሎ እንድንናከስ መርዝ መርጨቱ፣ እንድንተላለቅ እሳቱን ማጋጋሉ፣ ወጣቱን በጎጥ ስም፣ በአውራጃ ስም፣ በክፍለ ሀገር ስምና በሃይማኖት ስም ሕይወቱን እንዲሠጥ መቀስቀስ፤ ዓይነተኛ ተግባሩ ሆኗል። እናም አሁን የሰላሙ መንገድ፤ በሩ ተጠርቅሞ ተዘግቷል። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መሪዎች፤ መጨረሻቸው፤ ተሰብስበው እስር ቤት መወርወር ወይንም በቆፈሩት ጉድጓድ መከተት መሆኑን ስለሚያውቁ፤ እስከመጨረሻቸው ድረስ፤ ጠላቴ ያሏቸውን በመግደል ቀናቸውን ለማራዘም መፍጨርጨር
የሚጠበቅ ነው። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት የሚፈልገውና በተደጋጋሚ ያስመዘገበው እውነታ ያሳየው ሀቅ፤ የትግራይን ወገናችንን እወክለዋለሁ ብሎ ራሱን ሰይሞ፤ ከሞላ ጎደል ዘጠና አራት ከመቶ የሚሆነውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በተቃዋሚነት መድቦ፤ ይህ ክፍል፤ ትጥቁን አውልቆ እንዲጥል፣ የትግሬዎችን ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት የሚያወጣውን ሕግ፣ ደንብና መመሪያ እንዲከተልና የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥትን አምላኬ ብሎ ተቀብሎ፤ ከግሩ ሥር ወድቆ እንዲሰግድለት ነበር። ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ስለማይዋጥለት፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ያላጃቢ ብቻውን ወደ መቃብሩ መጓዙን መርጧል። የኢትዮጵያ ሕዝብም ይኼን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት፤ የትንሿን የእግሩን ጥፍር ታክል እንኳ አያምነውም። እናም አስገድዶ ሥልጣኑም መንጠቁ ግዴታ ነው። ሲነጥቀው በዘር መከፋፈልና በዘር ሥልጣን መያዙ ያከትማል። የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ ሆኖ፤ በአንድነት ኢትዮጵያን ከወደቀችበት ያነሳታል።
ተጨባጩ የወገናችን የኑሮ ሀቅ ከመቼውም በበለጠ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ስለደረሰ፤ የሚፈነዳ ትንታግ በሀገራችን ላይ አንዣብቧል። ጥያቄው መቼ? እና እንዴት ያለ መልክ ይይዛል እንጂ፤ ይሆናል አይሆንም አይደለም። በሚሆንበት ጊዜ ምን ዓይነት መልክ ይኖረዋል? ነው ጉዳዩ። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር አዲስ አበባ ሲገባ ያውለበለበው፤ የብሔሮችን ነፃ መውጣትና የወያኔን ጀግንነት እያወጀ ነበር። እስኪ እውነቱን እንመረምረው፤ የትኛው “ብሔር” ነፃ ወጣ? ኢትዮጵያ? አፋር? ሶማሌ? ኦሮሞ? አማራ? ትግሬ? ቤንሻንጉል? የደቡብ ሕዝብ? የትኛው? ለኔ ትግራይ እንኳ ነፃ አልወጣችም። ኤርትራ እንደሆነች፤ “የቅኝ ግዛት ነበረች።” ነው ያለው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት። የብሔሮች ጉዳይ የተነሳው፤ ሀገራችንን ለመበታተንና የተጠናከረ ሀገራዊ ተቆርቋሪ እንዳይነሳባቸው እንጂ፤ በርግጥ አሳቢዎች ሆነው አይደለም። ቢሆንማ ኖሮ፤ ከሁሉም እኩል የተውጣጣ መንግሥት አይመሠርቱም ነበር? ስለዚህ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ያላቸው ጥላቻ ግልፅ ነው። ባጠቃላይ ሀገራችን፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር በገባበት ሰዓት ያለችበትንና፤ አሁን ያለችበትን ስናመዛዘን፤ የትግሬዎችን ነፃ አውጪ ግንባር መሠሪ ተንኮልን በግልፅ መረዳት እንችላለን።
ማሰር፣ መግደል፣ ካገር ማሳደድ፣ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መደበኛ ተግባሩ ነው። “እኛ” እና “ሌሎች” ብሎ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከፋፍሎ መድቦ፤ “ሌሎች”ን መፍራትና ማጥቃት፤ የሕልውናው መሠረት ነው። “እኛ” የሚለው ክፍል አነስተኛ በመሆኑ፤ “ሌሎች” የሚላቸውን መከፋፈልና እንዳይስማሙ ማድረግ የሕልውናው መሠረት በመሆኑ፤ መዋቅሩ በዚህ ላይ የቆመ ነው። የጣሊያን ፋሽስት የቅኝ ገዢዎቹ ይኼንኑ ነበር ያደረጉት። የብሔሮች ነፃነት ከዚህ የመነጨ የፖለቲካ ስሌት ነው። ወታደራዊ ኃይሉን “እኛ” በሚላቸው ክፍሎች መቆጣጠር፣ የሃይማኖት ዘርፎችን “እኛ” በሚላቸው ወገኖቹ መምራት፣ የትምህርት ዕድሉን “እኛ” ለሚላቸው ብቻ መስጠት፤ ባጠቃላይም ማናቸውንም ሥልጣን ሆነ ሀብት “እኛ” በሚላቸው ወገኖቹ መያዙና ማስያዙ፤ አስገራሚ አይደለም። ይህ ከቅኝ ገዢዎቹ የሚያመሳስለው ይዘቱ
ነው። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት፤ የትም ቦታ የፈፀመውና በመፈፀም ላይ ያለው ግፍ፤ የተለዬና ነጠላ ተግባር አይደለም። ሌሎች ተቀጥላዎቹ የፈፀሙትም አይደለም። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት መሠረታዊ ፍልስፍናውና መመሪያው የሆነው ፀረ-ኢትዮጵያ ተግባሩ ነው። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ዘረኛና አምባገነን ነው። ይህ ምንነቱ ነው። አረመኔነቱ፣ አድላዊነቱና ሙስናው፤ አካሉ ናቸው። ያለነዚህ ሊኖር ፈፅሞ አይቻለውም። ባህሪው ብቻ ሳይሆኑ፤ አካሉ ናቸውና! የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት የገዛውና ሥልጣኑን እስካሁን ጠብቆ ያቆየው በአረመኔነቱና በአረመኔነቱ ብቻ ነው።
የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር አባላት፤ በትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባርነት ስም፤ የትግራይን ሕዝብ አደጋ ላይ እያስቀመጡት ነው። ትግሬ ያልሆነው ኢትዮጵያዊ ሁሉ፤ ትግሬ በሆነው ኢትዮጵያዊ እንዲነሳ ሆን ብለው የፈጠሩት ክስተት፤ ሥር እየያዘ ነው። ባንድ በኩል ሥልጣን በሙሉ በየትም ቦታ በትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር አባላት እጅ ገብቷል። በሌላ በኩል ሀብት በሙሉ በትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር አባላት እጅ ገብቷል። ቀጥሎም ከፍተኛ ትምህርትና ወታደራዊ ክፍሉ በትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር አባላት እጅ ገብቷል። የሃይማኖት መሪዎች፣ የመሬትና ሕንፃ ባለቤቶች፣ የሕክምና ባለሙያዎች፣ የገጠር አስተዳዳሪዎች በሙሉ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር አባላት ናቸው። ምንም እንኳ በገዢዎቹ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር አባላትና በትግራይ ሕዝብ መካከል ግልፅ የሆነ ልዩነት ቢኖርም፤ ገዢዎቹ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት አባላት፤ ይኼ እንዲደበዝዝና ቀሪዎቹ ኢትዮጵያዊያን ትግሬዎቹን በድፍን እንዲጠሉ ሙሉ ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው። የትግሬዎች ነፃ አውጪ አባላት በሙሉ ከትግራይ የመጡ ናቸው። ነገ ቀሪዎቹ ኢትዮጵያዊያን በዘመዶቻቸው በትግሬ ኢትዮጵያዊያን ላይ ትልቅ ዘመቻ እንዲደረግባቸው ጥረት እያደረጉ ነው። ይኼን እንዴት ነው ማቆም የሚቻለው? የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ይኼን እያራገበ ነው። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት የሚያራግበው አደጋ ደግሞ ቀላል አይደለም።
በዚህ ሂደት፤ አንድ፣ አንድ፣ እያልን ትዕግሥታችን እየተሟጠጠ፣ ተስፋችን እየጨለመ፣ ምርጫችን እየጠበበና ልባችን በቂም በቀል እየተሞላ ነው። መመለሻ ወደሌለበት ጎዳና ልንገባ ነው። በትግሬዎች ላይ ያለው ጥላቻ ከቀጠለ፤ ትግሬዎችና ትግራይ እንደሶሪያ አውሊያዎች የሚያሰጋ ወደፊት ይጠብቃቸዋል። የሶሪያ አውሊያዎች ከአሳድ ጋር ሕልውናቸውን አቆራኝተው አብረው ሊጠፉ ነው። ወያኔ ደግሞ በተመሣሣይ መንገድ፤ የትግራይ ወገናችንን በተመሣሣይ ዕጣ እንዲማገድ መንገዱን እየጠረገ ነው። ይኼን ማቆም የሚቻለው፤ አደጋውን የተገነዘቡ ትግሬዎችም ሆነ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በአንድነት፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥትን ነጥለን ለመደምሰስ ስንነሳ ብቻ ነው። አዎ በርግጥ አሁን አዲስ ትምህርት እና አዲስ ታሪክ እየተሰበከ ነው። የዛሬ የትግራይ ወጣቶች የሚሰጣቸው ትምህርት፤ የሚያጠኑት ታሪክና የተዘጋጀላቸው እውነታ፤ በትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የተቀመመ መርዝ ስለሆነ፤ ከትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ጋር አብረው የሚቆሙ ናቸው። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር እንደ ንጉሠ
ነገሥቱና እንደ ደርግ፤ ዘለዓለማዊ ነኝ ብሎ ስለሚያምን፤ ከትግራይ ውጪ ያሉትን ሌሎች ኢትዮጵያዊያንንም ጭምር በፈጠራ ታሪክ እያዋከባቸው ነው። ሀቁ ግን፤ ምንም ዓይነት የታሪክ ስዕል ከፊታቸው ቢዘረጋ፤ ዛሬ መራብና መጠማታቸው፣ ዛሬ መራቆትና መታመማቸው፤ በሩን ለሌላ ነገር በሙሉ ስለዘጋ፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት በደል ብቻ ነው ከፊታቸው ጥርሱን አግጥጦ የሚታያቸው። እናም የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ላይ ይነሱበታል። ፍራቻዬ ግን፤ እነዚህ ሲነሱ፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ በትግሬዎች ጉያ መደበቁና የዛሬ የትግራይ ወጣቶችን ግንባር አሠልፎ ማስጨረሱ ነው።
ልክ እንደ ሶሪያው አሳድ፤ የትግራይ ወጣቶችን እስካፍንጫቸው አስታጥቆ በአየርም በምድርም፣ በታንክም በሳንጃም፤ ሌሎችን ኢትዮጵያዊያንን ለመጨረስ ይጠቀምባቸዋል። ለጥቂት ገዢ የትግሬዎች ነፃ አውጪ አባላት፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በሁሉም ወገን ያልቃሉ። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ለዚህ እያመቻቸን ነው። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መሪዎች፤ ራሳቸውን ከሥልጣን ውጪ ሊያዩ አይቻላቸውም። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር በኢትዮጵያዊያን ላይ ዘምቷል። ይኼን መቀበል የሚቸግራቸው አሉ፤ ሀቁ ግን ግልፅ ነው። በአማራው፣ በኦሮሞው፣ በሶማሌው፣ በአፋሩ፣ በደቡብ ሕዝብ፣ በአኙዋኩ፣ በትግሬው፣ በሁሉም ላይ ዘምቷል። ይኼን በወታደሩ፣ በፖሊሱ፣ በፀጥታ ኃይሉ፣ በአስተዳደር ክፍሉ፣ በሙሉ ተግብሮታል። በጥይት፣ በታንክ፣ ባውሮፕላን፣ በሳንጃ፣ በሁሉም ፈፅሞታል። በየዓይነቱ በትግሬዎች ነፃ አውጪነት ስም አስኪዶታል። ይኼን ግፍ፤ ኢትዮጵያዊያን ይረሱታል ወይንም ፈርተው ይተውታል ብሎ ያስባል ወይ? የሚረሳውስ ምንድን ነው? የደርግን በደል፣ የደርግን ግድያ፣ የሕዝቡን መራቆት እንባቸውን እያንቆረቆሩ እየተረኩልን፤ እነሱ በእጥፍ አባዝተው በጉሮሯችን ላይ ሸነቆሩብን። አሸባሪነት የወያኔ ደንበኛ መመሪያው ነው።
የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር በአማራው ወገናችን ላይ የተለዬና የተነጣጠረ የዘር ማጥፋት ዘመቻ አያካሄደ ነው። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር በኢትዮጵያ የትግራይን የበላይነት ሊያራምድ የሚችለው፤ አማራን ብቻ ሳይሆን፤ ቀሪዎችን ኢትዮጵያዊያንን በሙሉ በመርገጥና በመጨፍለቅ ነው። ይህ በሕልሙ ብቻ ተወስኖ መቅረት አለበት። የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁን የሚኖርበት ሀቅና በፋሽስቱ ጣሊያን ወረራ ጊዜ ያሳለፈው የኑሮ ሀቅ ተመሳሳይ ነው። እኛም ያለራሳችን ሀገር በስደት የምንኖረው ኑሮ፤ በንብረት ሀገር ቤት ካሉት ዘመዶቻችን የተሻልን ነን ብለን ብናስብም፤ ስደት ራሱ ጉድለት ነው። እንደ አርበኞች ሰማዕቶቻችን ሀገራችን የምትጠብቅብንን እናድርግ። ይኼ ዕድል ስለተሠጠኝ በጣም አመሰግናለሁ።

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 13, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 13, 2013 @ 8:03 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar