www.maledatimes.com አንድ ምሬት | አቤ ቶኪቻው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አንድ ምሬት | አቤ ቶኪቻው

By   /   March 14, 2013  /   Comments Off on አንድ ምሬት | አቤ ቶኪቻው

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 53 Second
አንድ ምሬት

ሰሞኑን ኮምፒውሬ ወሰድ መለስ ሲያደርጋት ነበር እና በቅጡ መገናኘት አልቻልንም፡፡ ይባስ ብላም የመረጃ ማጠራቀሚያ መሳሪያዋ (ሀርድ ዲስኳ) ከጥቅም ውጭ ሆኖ የነበሩኝ በሙሉ እንዳልነበሩኝ ሆነዋል፡፡ እኔም ብያለው፤ “ሁሉም አላፊ ሁሉም ጠፊ ነው… ገዢው ፓርቲም ጭምር” እዚህ ጋ እንኳን ገዢው ፓርቲ መግባት አይገባውም ነበር፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ወዳጆች በተለያየ ጊዜ ጽንፈኛ ሆንክ ሲሉ አስተያየት እየሰጡኝ በመሆኑ እነሱን ለማስደሰት ይሁነኝ ብዬ ያደረግሁት ነው!
አረ እኔ የምለው ወዳጄ ቀልዱ ቀልድ ነው፤ የኮምፒውተሬስ እሺ በራሴው ጦስ ያመጣውት ነው፡፡ ድረ ገጼ ላይ ደግሞ በዚህ ሰሞን በርካታ አስተያየቶች እንዳሉኝ ምልክት ተመልክቼ ማን ምን አለ ይሆን… ብዬ ወደ አስተያየቱ ጓዳ ስገባ ምንም እርባና የሌላቸው ጹሁፎች እየተመለከትኩ ነው፡፡
የነዚህ መልዕክቶች ባለቤት ማን እንደሆነ እርሱ ባለቤቱ ይወቀው አብዛኛዎቹ፤ “እንዲህ ነው እንጂ ድረ ገጽ” በሚል ማበረታቻ የሚመስል አማላይ ቃል የተሞሉ ናቸው፡፡ አስተያየቶቹ እጅግ የበዙ ከመሆናቸው የተነሳ ከመንግስታችን ፈርጀ ብዙ ችግር ሁላ ይብሳላ፡፡
ምን ጠረጠርክ ይበሉኝ… ምናልባት እነ አጅሬ ይሆኑ እንዴ… እንዲህ በአስተያየት ብዛት የሚያማርሩን…! ሀገር ቤት እያለን የአይነ ቁራኛ አስተያየታቸው ቢቀፈን ሀገር ለቀን ወጣንላቸው! አሁን ደግሞ የት ሂዱ ብለው ነው እንዲህ የሚያደርጉን…! ብለን እንቀውጠው እንዴ! (አንድ ወዳጅ መሆን የተሳነው ግለሰብ፤ “እነ ቐሽ ገብሩ በተሰዉት እኮ ነው አንተ ዛሬ ማንችስተር ለመኖር የበቃኸው እናም ማመስገን ይገባሃል” ብሎኛል፡፡ እውነቱን ነው… ለዚህ የስደት ኖሮ የበቃነው… በታጋዮቻችን የተነሳ ነው እናም ልናመሰግናቸው ይገባል፡፡ እግዜር የስራችሁን ይስጣችሁ ብለን እንመርቃቸዋለን! ከዛ ቁጭ ብለን ምርቃቱ ሲደርስ መመልከት ነው…!)
የምር ግን አረ መላውን የምታውቁ አንድ በሉኝ…! እንዴ… የወዳጆቼን አስተያየት እኮ ማየት አልቻልኩም! እስቲ ማነው ጎበዝ እኒህን አስተማሪ የበደላቸው ሴረኞች ሃይ የሚልልኝ! የምር ምርር ነው ያደረጉኝ! ነውር አይደለም እንዴ…!

አንድ ምሬትአንድ ምሬት | አቤ ቶኪቻው
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 14, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 14, 2013 @ 8:04 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar