www.maledatimes.com ‹ተመራማሪው ዶክተር› ዓለምሰገድ አባይ ወልደማርያም ዘገዬ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

‹ተመራማሪው ዶክተር› ዓለምሰገድ አባይ ወልደማርያም ዘገዬ

By   /   March 14, 2013  /   Comments Off on ‹ተመራማሪው ዶክተር› ዓለምሰገድ አባይ ወልደማርያም ዘገዬ

    Print       Email
0 0
Read Time:67 Minute, 45 Second

‹ከሰደበኝ ስድቤን አምጥቶ የነገረኝ› እያልክ ኋላ እንዳታማርረኛ አማራ ነኝ ብለህ የምታምን ይህችን ብሶት ወለድ ወረቀት አታንብብ፤ ይብስ ትቃጠላለህ፡፡ ምድረ ኮምፕሌክሳም እየተነሣ የጭቃ ጅራፉን በአማራ ላይ መለጠፍ ተያይዞታልና ‹ዘመኑ ነው፤ ሳያውቅ የተኛን አንበሣ ዐውቆ በንቃት የቆመ ነብር ይጫወትበታል› ብለህ ቻል ማድረግ ነው፡፡ ይሄ አሁን ብዕር ያስነሳኝ ቆሻሻና ደደብ ሰውዬ – ዓለምሰገድ አባይ – የሚሉት ደግሞ ከመለስም የባሰ የመጨረሻው ፀረ-አማራና ፀረ-ኢትዮጵያ ሳይሆን አይቀርም፡፡ በሕይወትም ይኑር በሞትም ይለይ በነጻነት ማግሥት ከመለስ ዜናዊ ቀጥሎ ፍርድ ቤት ከምገትራቸው ‹ሰዎች› መካከል አንዱ ነው – የሞተን ሰው መክሰስ በኔ አልተጀመረም – ይሄውና ራሽያም ሰሞኑን አንዱን ሟች የቀድሞ ጠበቃ በግብር ሽቀባ ምክንያት የሙት መንፈሱን ፍርድ ቤት ገትራ ዓለምን በሣቅ እያንከተከተችው ናት – እኔም ለዚያ ያብቃኝ እንጂ መለስን ጨምሮ ፍርድ ቤት የምገትራቸው ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ የዕለቱ አዝማች መፈክሬ፡- [ማሸነፍ ብርቁ ከሆነ ጠላት ይሠውራችሁ!]

“ይሄ ባለጌ ሰውዬ ግን እንዴት እንዴት ነው አማራን በስድብ የሚሞልጨው እባካችሁን? ይሄ ንፍጣም የውሻ ልጅ! ‹የወደቀ ግንድ ምሣር ይበዛበታል› አሉ? አሁንም ድረስ አማራነቴን አለማወቄ በጄ እንጂ እንደርሱ ቢሆን ይህ ጠብ ጫሪነቱ ክተት የሚያሳውጅ ነበር፡፡ ብሎ ብሎ ከኦሮሞ ቀጥሎ በምልዓቱ በኢትዮጵያ ሁለተኛ የሆነን የሕዝብ ክፍል ‹Minority Amhara› ይበል? ይህስ ባልከፋ – አለ እንጂ የሰማይ ስባሪ የሚያካክል የውሸት ቁልል በ‹ጥናታዊ ጽሑፉ› ውስጥ ያጨቀው!”አለኝ አንድ ይህን ምሥጢር ሹክ ያልኩት ወዳጄ፡፡ እኔም “እንደዚህ የሚሰማህ መሆንክን ባውቅ አልነግርህም ነበር” አልኩት፡፡ ለዝርዝሩ ወረድ እንበልማ፡፡ [ማሸነፍ ብርቁ ከሆነ ጠላት ይሠውራችሁ!]

“Identity Jilted or Identity Re-imagined” በሚል ርዕስ ቀደም ሲል ያሣተመውን ‹መጽሐፍ› ሌላ ጽሑፍ ሳነብ በዋቢነት ገብቶ አገኘሁና ያን መጽሐፍ ከመደርደሪያየ አውጥቼ አቧራውን አራገፍኩና ማንበብ ቀጠልኩ፡፡ ከመነሻው የፊት ሽፋን ገጽ ጀምሮ እስከመጨረሻ ስዘልቅ ከሞላ ጎደል ሁሉም ይዘቱ እንትን እንትን የሚልና ክፉኛ የሚገማ ሆኖ አገኘሁት፡፡ አማራ ብሆን ኖሮ ገመዴን ይዤ ወደሚቀርበኝ ዛፍ እሄድ ነበር – ደግነቱ ኢትዮጵያዊ እንጂ አማራ አይደለሁም – ከፍ ሲልም ሰው ነኝ፡፡ “እንደዚህ ጨምላቃ ሰውዬ በዘረኝነትና በዘውገኝነት አረንቋ ሰምጬ በጥላቻና በበቀል ደዌያትም ተመርዤ ሥነ ልቦናዊ ሥቃይ ውስጥ ባለመግባቴ ፈጣሪየን አመሰግናለሁ፡፡” ልል አሰብኩና መታፈር በከንፈር ብዬ ተውኩት፡፡ ይሁንና ምንም እንኳን በአስተዳደጌ የዚህ ወይ የዚያ ዘውግ አባል መሆኔ በወላጆቼ ተገልጾልኝ ወደፈፋና ሸጥ እንድሸጎጥ ባለመደረጌ ምክንያት በአማራነት የተፈረጀ አንድ ታላቅ ሕዝብ ሲሰደብ ያን ያህል ባይሰማኝም የሰዎችን ከንቱነትና ሰይጣናዊ ተፈጥሮ ይበልጥ ለመረዳት እነዚህን መሰል ጽሑፎች ማንበቡ መጥፎ እንዳልሆነ በማመን በሰዎች የተንሸዋረረ ግንዛቤና በጠሉት ላይ እስከምን ድረስ ሊዋሹ ሊጨክኑም እንደሚችሉ እያሰብኩ ያን እንደገማ ዕንቁላል የሚጠነባውን የዓለምሰገድ አባይን ከኢትዮጵያ ጠላቶች በተወሰዱ እጅግ በርካታ ጥቅሶች የታጨቀ ጽሑፍ እየተገረምኩም በሰው ልጅ ከንቱነት እያዘንኩም አነበብኩ፡፡ ‹ለካንስ ፊደል መቁጠር በራሱና ብቻውን ምንም ማለት አይደለም› ብዬም ‹ተፈላሰፍኩ›፡፡ ተማረ የተባለ ሰው ይህን ያህል ወርዶ ከተጨመላለቀ ያልተማረውማ እንዴቱን ከዚህ አይብስ? ለዚህ ለዚህማ በአዲስ አበባና አካባቢዋ የሚርመሰመሱ ይሉኝታቸውን ቸርችረው በልተው የጨረሱ የወያኔ ጅቦችና ዓሣሞች ምን አጠፉ? በሀገርህ ሲወረር አብረህ ውረር የማይማን ፈሊጥ  ከታሪካዊ ጠላቶቿ ጋር ተባብረው ኢትዮጵያን የሚግጡ ሌሎች ዜጎችስ ምን አጠፉ? ዶክተር ተብዬው እንዲህ ጆሮውና ዐይኑ ተመሳጥረውና ኅብረት ፈጥረው በአንዴ ከጠፉ፡- በሰውነት ሳይሆን በመወለድ፣ በእውነት ሳይሆን በሀሰት፣ በሣይንሳዊ መክሊት ሳይሆን በዘረኝነት ቅኝት የተሳሳተና ወገንን ከወገን የሚያናክስ ጥናት ተብዬ ካሰራጨ ከእንግዲህ ለኅሊናስ ሆነ ለሰብኣዊነት ማን ይታመን? ያላነበባችሁት በሞቴ አንብቡትና ፍረዱ፡፡ ከዚያ በኋላ ‹ጥናት እንዲህ ከሆነ ባፍንጫዬ ይውጣ!› ብላችሁ እርግፍ አድርጋችሁ ትተዋላችሁ፡፡ [ማሸነፍ ብርቁ ከሆነ ጠላት ይሠውራችሁ!]

ግሩም ነው፡፡ ‹ሪሰርች› ማለት ለካንስ እንዳማርኛ እንዳበጁት ሊበጅ የሚችል ነገር ኖሯል! ከስሜታዊ ቃለ መጠይቆች ባሻገር እዚህ ግባ የሚባል የምርምርና ጥናት ውጤት ሳይዝ በሪሰርች ስም እየቀለደ አንድን ሕዝብ መሳደብ የማያስቀጣ መስሎ ስላገኘው ብቻ እንደዚያ ሲሞላፈጥ ስታዩት አንዳች ነገር ይሰማችኋል፡፡ አማራን የማይወርፍ፣ የማያንቋሽሽ፣ የማይሳደብ፣ በሀሰት የማይወነጅል ዐረፍተ ነገር በየአንቀጹ አታገኙም፡፡ አማራን እያሳዩ የገረፉት ነው እሚመስል፡፡ የአሁኑ ትውልድ ኢትዮጵያዊ እንኳን፣ የወያኔን ሁልአቀፍ ሀገራዊና ትውልዳዊ ጥፋት በዐይኑ በብረቱ እያዬ ዓለምሰገድ በአማራ ላይ ያለውን ጥላቻ ያህል በወያኔ ላይ የለውም፡፡ የሚገርም ሰው ነው ይሄ ዓለምሰገድ የተባለ ውልቀሰብ፡፡ [ማሸነፍ ብርቁ ከሆነ ጠላት ይሠውራችሁ!]

ይህ ትግሬ ነኝ የሚል ሰው – ግን ልክ እንደነመለስ ሁሉ ከኤርትራ በላይ ለኤርትራ የሚጨነቅ ሰው – ብዙ ቁጭት ያለበት ለመሆኑ መጽሐፉ አፍ አውጥቶ ይናገራል፡፡ ‹ትግራይ ትግሪኝ› ለምን አልተመሠረተችም የሚል ትልቅ ፀፀት አለበት፡፡ ኤርትራና ትግራይ ለምን አንድ መንግሥት አልፈጠሩም፣ ትግራይ የጎንደርን ለም የእርሻ መሬቶች á‹­á‹› ከአላውሃ መልስ ‹ታላቋ ኤርትራ› ወይም ‹ታላቋ ትግራይ› ወይም ‹ታላቋ ትግራይ ትግሪኝ› በሚል የትግርኛ ተናጋሪ ሕዝብና መንግሥት ለምን አልመሠረተችም የሚል ታላቅ ቁጭት አለበት፡፡ ወያኔና ሻዕቢያ እፊታቸው ላይ ያልተጠበቀና ትልቅ የክፍለ ዘመን የሎተሪ ዕድል ተጎልቶላቸው ሳለ የወዲህኞቹ ሃሳባቸውን ቀይረው ለምን በ‹ኢትዮጵያ›ዊነታቸው ጸኑ የሚል የእግር እሣት አለበት፡፡ አማራ ባላገር ነው፣ አማራ እንኳን ሌላ ሕዝብ ራሱን ማስተዳደር የማይችል ቀርፋፋና ኋላ ቀር ሕዝብ ነው፣ አማራ ደደብ ነው፣ አማራ … ምን የማይለው ነገር አለ – በደምሳሳው አማራ የሁሉም ክፉና ኢ-ሥልጡን ነገሮች መገለጫ ነው የሚል ጭፍን አቋም አለው፡፡ ጥናቱና አጥኚው  በውነቱ ከሂትለር የአርያን ዘር በባሕርይ የሚወራረሱ፣ ከዚሁ ዘውግ የናዚ ቅኝት የሚዛመዱ፣ ከፋሺዝም የሙሶሎኒ ሥነ ፍጥረት የሚጋሩ በዓለም የመጀመሪያዎቹ በቀል ወለድ የአጋንንት አካላዊና ቁሣዊ መከሰቻ ናቸው፡፡  ይህን መሰል ሰው በዚህኛው የ21ኛ መቶ ክፍለ ዘመን ማየት ለሰው ልጅ ዘር በአጠቃላይ ሀፍረት ነው፤ ውሸት እግር አውጥቶ ሲራመድ ማየት ለሚፈልግ ሰው ይህን መጽሐፍ በማንበብ ሊያረጋግጥ ይችላል፡፡ የወያኔን ተፈጥሮም ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡

በመሠረቱ በዚህ ረገድ ብዙም ባላውቅ ካለኝ ጥራዝ ነጠቅ ግንዛቤ በመነሣት ስገምተው ጥናትና ምርምር የራሱ አካሄድ ያለው ይመስለኛል – እንደ አቶ ዓለምሰገድ የራስን ሸፍጥ በጥናት ስም ማቅረብ በፍጹም የሚቻል አይመስለኝም – በዘመናችን ዕድሜ ለኮፒ-ፔስት ጥናት እንደቀልድ ከመታየቱና ብዙውን ጊዜም ለፈንድና ለዕቅድ አፈጻጸም ማወራረጃነት የሚውል መሆኑን የሚጠቁሙ ‹ሰነፎችና ምቀኞች› ባይጠፉም፡፡ ሲሉ እንደሰማሁት ጥናታዊ ዘገባ በሦስትዮሽ የማጣሪያ መንገድ ተበዝቆ(triangulation)፣ በዘመናዊ የምርምር መንሽና ላይዳ ተበጥሮ (በ‹qualitative and/or quantitative የአቀራረብ ዘዴ) የተደረሰበት በኩር ሥራ ወይም ከቀድሞ መሰል ሥራ የተሻሻለ ተጓዳኝ ግኝት የሚቀርብበት እንጂ በየመሸታ ቤቱ የተቃረመ የጥላቻና የበቀል ስሜት የሚናፈስበት – እንደሎሬቱ አገላለጽ – የወሬ ማንፈሻ ጋሻ አይደለም – ጥናትና ምርምር፡፡ እንደዚያ ከሆነ እኔን ብዙ ጊዜ የሚገጥመኝን የሞልፋጣ ወያኔዎችን ስንክሳር በጥናት ስም ባቀርብ ተቀባይ ይኖረኛል ማለት ነው -  ይህ የኔና የዓለምሰገድ ዓይነቱ አቀራረብ ጥናታዊ ሳይሆን መሸታዊ ነው ሊባል የሚችል፡፡ የዓለምሰገድ ‹ጥናት› መነሻውም መድረሻውም አሉቧልታና ፀረ-ኢትዮጵያ የውስጥና የውጭ ኃይሎች በንግግር ወይም በጽሑፍ ያስቀመጧቸው ሃሳቦች ናቸው፤ በተጨማሪም የጥንት የዋሃን ወደተንኮል ይዞርብኛል ብለው ያልተናገሩት ገራገር የግል አስተያየትና ሃሳብም እንደጥናት ግብኣት ተካትቷል፡፡ በጥናት ጽሑፍ ውስጥ ሊጠቀስ የሚገባው እንደአፈወርቅ ገ/የሱስ ያለው ግላዊ አስተያየት አይደለም – ለተለዬ ዓላማ ካልሆነ በስተቀር፡፡ እዚህ ቦታ እገሌ እንደነገረኝ ተብሎም ጥናታዊ ጽሑፍ አይቀርብም፡፡ ነውር ነው፡፡ የምሁራዊነትን ይዘት ያወርደዋል፡፡

ለምሳሌ የዛሬ 17 ዓመታት ገደማ ከአንድ የአንድ መሥሪያ ቤት የግዥ ሠራተኛ የነበረ ትግሬ ወያኔ ጋር (ኦ! በዘውጋዊ ቀመሩና በሥራው አጋጣሚ በጣም ብዙ ገንዘብ ዘርፎ እጅግ የከበረና ቢጠሩት የማይሰማ ቀጭን ጌታ ነው! አሁን፡፡) ሊፍት ሰጥቶኝ አብሬው ስሄድ ፕሮፌሰሮች አሥራትንና መስፍንን አንስቶ “አነ እንተሆንኩ ለነዚሁን ሰዎቹ እንኳዕ የፕሮሶፌርነት ማዕርግ የ12ኛ ካርድም አልሰጣቸውም ነበረ!” በማለት በንዴት እየፎገላ  የተናገረውን ካለዛሬ ለማንም አልተናገርኩም – እውነቴን ነው፤ የዚህ ዓይነቶቹን እውነተኛ ገጠመኞቼን ብጽፋቸው ወረቀትና ቀለም አይበቃኝም – ሰውዬው ያን ያለው ጭልጥ ካለ ወገናዊኑ እንጂ ሰዎቹንና አቋማቸውን ተረድቶ አይደለም፤ በብዙ መቶ ሺዎች – ምናልባትም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ -  ተጋሩ አኅዋትና ከምዙይ ሰብዓይ ከምዝሰምዖን አነ ብወገነይ እፈልጥ እየ – ምክንያቱም የአሊየት ጉዳይ ከእንስሳዊነት ባሕርያችን የምንጋራው በምክንያት ሳይሆን በደምና በአጥንት እየተፈላለግን የምንቧደንበት ጥንታዊ የትስስር ገመድ ነው፤ መሠረቱም ማይምነትና ኋላቀርነት እንዲሁም የመኖር ዋስትና ሥጋት (insecurity)ነው፡፡ [recommended read on this issue:- The virtue of Selfishness, Ayn Rand] ፡፡ ይህ ከፍ ሲል የገለጽኩት የዛሬ 17 ዓመቱ ገጠመኜ በጣም ግለሰባዊ ነው፡፡ መላ ትግሬን አይወክልም – ከዚህም በላይ ሊሉ የሚችሉ ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ መብታቸውም ነው – እኛስ እነሱን ስንትና ስንት እንላቸው የለም – ዕድሜ ለዚህ የ‹እነሱ›ና ‹እኛ› መለሳዊ ከፋፋይ ፈሊጥ፡፡ ነገር ግን በጥናት ስም ይህን አሉቧልታ ሁሉ አጠረቃቅሜ ‹ጥናታዊ ጽሑፍ› ብዬ ባቀርብ ያሳፍራል፡፡ ዓለምሰገድም ማፈር አለበት፡፡ አማራን መጥላት ሌላ – በጥናት ስም ይህን የተከበረ የሣይንስ ዘርፍ – ጥናትና ምርምርን – አቧራና ጭቃ ላይ ጥሎ ማርመጥመጥ ሌላ፡፡ ቢያንስ ቢያንስ – የለውም እንጂ ቢኖረው ኖሮ የራሱ ኅሊና እየቆዬ በቆጠቆጠው ነበር፡፡ አብሮ ኗሪ በሆነ ሕዝብ መሀል ይህን የመሰለ ግፍና በደል መሥራት ታሪክ ይቅር የማይለው የግፍ ግፍ ነው – “አያልፍ የለም አለፈና፤ ኑ ይሏችኋል እቡና” መባባል የማይቀር ከሆነ አሁን የምንለውና የምናደርገው ሁሉ ለነገው የአብሮነት ሕይወታችን እንቅፋትና የሆድ መቀያየምን የማይፈጥር መሆን ይገባዋል – የዱባን ጥጋብ መቆጣጠር ካለስንቅ መዝመትን ያስቀራልና ማስተዋልን ከአሁኑ እንለማመድ፡፡ አሁን እየተደረገ ያለውን ሰማይና ምድር ሊቋቋሙት የማይችሉትን የወያኔ ትግሬ ግፍ ዓለምሰገድ ቢመለከት – አሁንም ዐይን የለውም እንጂ – ምን ሊል ይችል ይሆን? ለነገሩ ‹አውቆ የተደበቀ› እንዲሉ የነሱ ጥፋት ለርሱ የፅድቅ መንገድ ነው፡፡ ሰዎች እንግዲህ እንዲህ ነን፡፡ ለራስ ስንቆርስ የማናሳንስ – ለሰው ስንቆርስ የምንቀናንስ፡፡

የዚህን ውሸታምና ዘረኛ ሰውዬ አርቲ ቡርቲ ጽሑፍ በስፋት ለመቃኘት ጊዜውም ሆነ ፍላጎቱ  የለኝም፡፡ ደግሞም በወቅቱ ልክ ልኩን የነገረው ሰው ሊኖር ይችላል ብዬ አስባለሁ፡፡ እኔም መጽሐፉ ከታተመ ከ14 ዓመታት በኋላ እንዲህ እየተንጨረጨርኩ ልወርፈው የዳዳኝ ገና አሁን ስላነበብኩት ነው – ያላነበብከው ነገር ምንጊዜም አዲስ ነው የሚል እምነት አለኝ – “ብለነው ብለነው የተውነውን ነገር፤ ሚስቱ ዛሬ ሰምታ ልትታነቅ ነበር” የሚለውን የኔ ቢጤዋን ሞኝ ሚስት አስታውሱና በነገሮች መመሳሰል ዘና በሉ፡፡ የትኛው ሞልፋጣ ምን እንዳለ ማስታወሱ በራሱም መጥፎ አይመስለኝም፡፡ ይሄ አማራ የሚባል ፍጡር ግን ፈርዶበት! ምን ይሆን ጥፋቱ ምድረ ወያኔ እንዲህ የሚረባረብበት? ምድረ ማይም የሚቀረሽበት ይሄ አማራ የሚባል ነገር አንድ ተፈጥሯዊ መስህብ ሳይኖረው አይቀርም ግዴላችሁም፤ ሙት አሉት ሞተላቸው – ተሰደድ አሉት ተሰደደላቸው – ድሃ ሁን አሉት ደኸየላቸው – ታመም አሉት ታመመላቸው – አትብላ አሉት ተራበላቸው – አትናገር አሉት ዱዳ ሆነላቸው – አትመልከት አሉት ታወረላቸው፤ በተዘረፈ ገንዘብ ከየትም ባሰባሰቡት ትብታብና ደንቃራ፣ አንደርብና አፍዝ አደንግዛቸው ሰመመን ውስጥ ግባ አሉት ሰማይ ምድሩ ዞሮበት አንቀላፋላቸው፡፡ ከዚህ በኋላ የምን አትርሱኝ ነው? ለአቡሻክሩ መዞር፣ ለአበቅቴው መጥባት ደግሞ የዘመን ዑደቱን መጠበቅ እንጂ የወደቀን መቀጥቀጥ፣ ‹የተሸነፈን› መነረት ሃይማኖታዊም ሞራላዊም ሰብኣዊም አይደለምና ወያኔዎች  እባካችሁን በአቡነ አረጋዊ ይሁንባችሁ  በምንም ይሁን በምን – በገደሉም ይሁን በባህሩ ጂኒ  ‹ማሸነፋችሁን› ተገንዝባችሁ አሁን በመጨረሻው ዘመን ላይም ቢሆን በቅጡ ግዙ(ን)፡፡ ሞቶም አጥንቱ እንዳያርፍ ያስደንግጥ ያለበት ይመስል ዘወትር በእውንም በህልምም የሚበረግጉ ወገኖች መብዛታቸው ይገርማል፡፡ ነገሩ የበሽታ ነው – ነጫጭባዎቹ psychosis ይሉታል – የአእምሮ በሽታ ስሙና ዓይነቱ ብዙ ነው፡፡ ህክምናም የለውም – መፍትሄው የአመለካከትና የአስተሳሰብ ለውጥ ወይም አካላዊ ሞት ነው – አንዱን መምረጥ ነው፡፡ ሆድ እንደሆነ አይሞላም – የድሎት ኑሮም አይጠገብም – ጥላቻም ገደብ የለውም፡፡ ከሁሉም ይልቅስ ያንቀላፋ ኅሊናን ቀስቅሶ ነፍስ እንዲዘራና ተጨባጩን እውነታ እንዲገነዘብ ማድረግ ለሁሉም የሚበጅ መልካም ነገር ነው – ወርቃማ አጋጣሚዎች ዕድሜያቸው አጭርና ባልተጠበቀ ሰዓት አሟልጨው ከእጅ የሚወጡ መሆናቸውን መረዳት በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ የሥነ አእምሮ ህመም መድሓኒት ቢኖረው ኖሮ ወያኔ በኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን ነገር ሁሉ እየተመለከተ ያለ ዓለምሰገድን እሚያህል ትልቁን ምድራዊ የትምህርት ደረጃ የተጎናጸፈ ሰው ይህን ገሃድ የወጣ የከተማ መንግሥት-ለበስ ውንብድና ለመሸፈን በሚመስል ሁኔታ እንዲህ ባልተወራጨ ነበር – ‹ድንቄም ጥናታዊ ጽሑፍ! መድበለ ቅሌት ወውርደት› በሉት ይህን ጽሑፍ የምታነቡለት ወዳጆቹ፡፡ [ማሸነፍ ብርቁ ከሆነ ጠላት ይሠውራችሁ!]

ቀጣዩን ተመልከቱና  በዱሮው የደርግ ቋንቋ የአማራን አናሳነት ወይም ንዑስነት ተመልከቱ – ከዋሹ አይቀር እንዲህ ነው፡፡ አዲዮስ ሪሰርች!

 

Even as Tigray enetered the armed struggle in 1975, … elites of both sides of Mereb retained separate political identities. Notwithstanding the difference in visions and self perceptions, they managed to coordinate their struggles against the Amhara minority regime. (p. 7, emphasis added)

 

የኛ ማለትም የነሱ ምሁር እንግዲህ ይሄ ነው(የነሱ ስል የወያኔዎች ማለቴ እንጂ የሰፊው የትግራይም ሆነ የኤርትራ ሕዝብ ማለቴ አይደለም – ከእነሱ ጋር ጊዜው ሲደርስ በመለሳዊ የፈግጠው ፈግጪው ስድ አንደበት ሳይሆን በጨዋ አንደበት እንነጋገራለን! ያኔ ማን ያውቃል ቋንቋም ሳያስፈልገን እንዲሁ በረቂቁ አውታረ ልቦና ወኅሊና ልንግባባም እንችል ይሆናል – ለርሱ የሚሳነው ነገር የለምና!) – አማራ አናሳ ‹ጎሣ› ሲሆን ይታያችሁ – የአቶ ስንሻው ቤተሰብ ዓይነት የአንድ አካባቢ ነገድ፡፡ ጥናት ማለት እንግዲህ ይዘኸው የምትነሳውን የሪሰርች ጥያቄ የሚመልስልህን ግሳንግስ ዐረፍተ ነገር መኝታህ ላይ ቁጭ ብለህ እየጠፈጠፍክ መጋገር ብቻ ነው ማለት ነው ፡፡ ይህን ሰው ‹የኛ›ና ‹የነሱ› ፈሊጥ ከተወገደ በኋላ አግኝቼ ብንወቃቀስና ምናልባትም እስከዚያን ጊዜ ድረስ ‹የሕክምና ሣይንስ አጥንቼ› የጄኔቲክ ዲኤንኤ ቀመሩን ብመረምረው ደስ ይለኛል፡፡ አብዛኛው ጽሑፉ የጥናትና ምርምርን ፈለግ ካለመከተሉም በላይ ጭልጥ ያለ ውሸት ነው፡፡ በክህደትም የተሞላ ነው፡፡ ለምሳሌ ጣሊያኖችን ያሸነፈው ኃይል ከመላዋ ኢትዮጵያ የተውጣጣ መሆኑን ላለማመን ሲፈልግ ‹ጣሊያን በአፍሪካ ጦር መሸነፍን እንደውርደት ስለቆጠረችው …› በማለት የኢትዮጵያን – እርሱ ‹የአማራው ዘረኛ መንግሥት› በሚል የሚጠራትን የኢትዮጵያ ሕዝብ ተጋድሎ በማንኳሰስ ድሉን ለሌላ አሳልፎ ይሰጣል፡፡ ለነገሩ ደባው እንጂ የሚያናድድ ድሉ በርግጥም የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የመላው ጥቁር ሕዝብ ድል መሆኑ ተወስቶ የማይጠገብ ታሪካዊ ኹነት ነው፡፡ ኢትዮጵያን ማንሳቱ የሚጠቅመው ከሆነ ያነሳል፤ አለበለዚያ ‹የአማራው ዘውግ የገዢ መደብ› እያለ ነው ከኢትዮጵያ ጋር በተመሳስሎ (synonymously) አማራውን አላግባብ የሚያነሳ የሚጥል – ያባቴ አምላክ የሥራውን ይስጠውና፡፡ [ማሸነፍ ብርቁ ከሆነ ጠላት ይሠውራችሁ!]

ቀጣዩን ደግሞ ተመልከቱልኝ፡- …The failure of the shared commonalities and war against a common enemy [Dergue/Ethiopiawinet] to shape a single trans-Mereb political identity is puzzling. (ibid)

 

እንደዚህ የሚለው – ነገሩም ዕንቆቅልሽ የሆነበት – ወያኔና ሻዕቢያ ድል ካደረጉ በኋላ አንድ ሆነው ያቺን ማርና ወተት እንደመና ከሰማይ የሚዘንብባትን ‹የቃል ኪዳን› ምድር ‹ትግራይ ትግርኝ›ን ለምን አልመሠረቱም? የሚል ቁጭት እያንገበገበው ነው – ( በቀላል የሚቀየም ሰው አይኑር፡- ኢትዮጵያ ሁሉም ነገር አላት – ሁሉም ነገር ግን በግድ በአንድ አካባቢ ይገኝ አይባልም – አያስኬድምም፤ እዚህ ወርቅ እዚያ ጤፍ፤ እዚህ ነዳጅ እዚያ ቡና… እንጂ በግድ ትግራይ እንደደቡብ ወይም ምዕራብ እንደ ምሥራቅ ይሁኑ አይባልም፤ ከሆኑልንም እሰዬው)፡፡ ይህን ሰውዬ ግን ወገኛ በሉት፡፡ አንዱ አቀባይ ሌላው ተቀባይ፣ አንዱ አምራችና አስመራች ሌላው በላተኛ፣ አንዱ ሎሌ ሌላው ጌታ ሆነው እየተቀማጠሉ ከመኖር ለማን ጀቴ ብለው ነው ከአላውሃ ወዲያ በደረቁቻ መሬት – ለብዙ ዘመናት አገልግሎት ከመስጠት አኳያ አፈሩ ወደድንጋይነት ዛፉም ወደቁጥቋጦነት በተለወጠ መሬት ላይ ተወስነው የሚኖሩ?  በሞኝ ደጅ ሞፈር መቁረጥ እየተቻለ የሌለን ጠባይ የምን ግድርድርነት ነው? ትግራይ ትግሪኝ ጥንቅር ብሎ ይቅር እንጂ የምን በችጋር መቆራመድ? ትክለ ሰውነትን ሳይቀር የሚቀይርና የተላጠ ሙዝ የሚያስመሰል ባለቤት የሌለው የመሀል አገር ሀብትና ጥሪት እያለ የምን መረብ ምላሽ ነው? ይሉኝታ ዱሮ ቀረ፡፡  ዓለምሰገድ ግን ጅልነትም አለበት ልበል? አላህ ከላይ ፈረደባቸውና የኋላ ኋላ ለይምሰልም ቢሆን – ከላይ ሣይሆን ባልጠበቁት ሁኔታ ከግርጌ ተመነቃቀሩ እንጂ እንደመነሻውማ ዕቅዳቸው ሌልኛ ነበር – ‹አላህ ሲቆጣ ሽመል አይቆርጥም ፤ ያደርጋል እንጂ ነገር እንዳይጥም› እንዲሉ ሆኖባቸው፡፡ ይህን መሠሪ የሁለትዮሽ ሸፍጥ ብፃይ ዓለምሰገድ አያውቀውም ማለት ይከብደኛል፡፡ መንገብገቡ ግን እንደአካሄድ ትክክል ነው – ይንገብገብ ፣ ይቆላጭም፡፡ ግን ግን ሁለቱ የዲያብሎስ ውላጆች በጋራ የሠሩትንና አሁንም ድረስ እየሠሩት የሚገኙትን ኢትዮጵያንና ኢትጵያዊነትን የማጥፋት ዘመቻ መርሳት አይገባንም – እርሱም እኛም፤ በቂያማ ቀን የምናወራርዳት ሒሳብ ልትኖረን ስለምትችል ‹ንቁም በበኅላዌነ በዐቢይ ትጋህ ወአርምሞ፣ እስከንረክብ ነጻነት በከዊነ ወልደአብ ወእሞ› እንድንል በጥራዝ ነጠቁ ‹ቅኔ ዘረፋ›፡፡ የጎጃምንና የወሎን ገበሬ በፎርጅድ ብር ስንትና ስንት መኪና ሙሉ እህል በተለይም ጤፍ እኒያኞቹ ከገዙና እኒህኞቹም እኒያኞቹን በጠራራ ፀሐይ ከሸኙ በኋላ ምሥኪኑ ገበሬ ብሩን ሊጠቀምበት ወደባንክ ሲሄድ እኒህኞቹ የሠሩትን ተንኮል እያወቁ ገበሬውን በወንጀለኝነት አላሰሩትም? በዚህች በኢትዮጵያ  ምድር ላይ እጅግ የሚዘገንን ግፍ ተሠርቷል! ክፍያውንም የሚችለው እንደሌለ ብዙ ጊዜ  ተገልፆኣል፡፡ በትዕግሥት መጠበቅ ብቻ ነው፡፡ አስታውሱ – የነዚህ ‹ወገኖቻችን›ን ወንጀል እንኳን ሌላው የዓለም ዜጋ ሰይጣን ራሱስ ሊሠራው ይችላልን?… ስንቱን በጋራ አሠሩ – ገደሉ  – አሰደዱ – አሳደዱ(በጠፍ ጨረቃ ወስደው ደብዛዋን ያጠፉት ማርታ መኮንን ትዝ አለችኝ፤  ከጨካኙ የባሕር አውሬ ከሻርክ የባሱ እነዚህን አውሬዎች የሚሊዮኖች ደምና ዕንባ በሠልፍ እየጠበቃቸው ነው!)፡፡ አዲስ አበባ የሻዕቢያ መንቦራቦሪያ አልነበረችምን(አሁንስ ቢሆን ማን ያቃል አይደለች ትሆን ይሆን?) ግን አይዞን ወንድሞችና እህቶች፣ እናቶችና አባቶች ፣ ጓዶች፣ ይህም ያልፋል፡፡ (በድርበቡ መንጌን መሰልኩባችሁ ልበል? ሆን ብዬ ላስታውሳችሁ ፈልጌ ነው፡፡ሰው ካልመሄድ ወይ ካልሞተ አይመሰገንም፡፡ በስንት ስለት የተገላገልኩትን ደርግን መናፈቄ ይገርመኛል – የዕድላችን ጥመቱም እንዲሁ፡፡)  [ማሸነፍ ብርቁ ከሆነ ጠላት ይሠውራችሁ!]

በነገራችን ላይ የቫቲካንን የጥቁርና የነጭ ጪስ የሞኞች የሚመስል ትዕምርታዊ የሊቀ ጳጳስ የምርጫ ሂደት ተከታትዬ አሁን በዚህ አንቀጽ መመለሴ ነው፡፡ ይቺ የሌጋሲ ነገር ታዲያ በእግረ መንገድ ሰሞኑን ከምንጊዜውም በላይ እየገረመችኝ መጥታለች፡፡ በ‹ፍራንሲስ አንደኛ›(Francis I) የጵጵስና ስም እንዲጠራ የወደደው አዲሱ አርጀንቲናዊው የጣሊያን ዝርያ ተመራጭ ሊቀ ጳጳስም በመጀመሪያ ንግግሩ የቤኔዲክት 16ኛን ሌጋሲ እጠብቃለሁ ሲል ብሰማ ጊዜ ቅንጭላቴ በአንዴ ሰሜን ኮሪያ ደርሶ ኢትዮጵያንም በበረራ ክልሉ አጣልፎ ወደጳጳሱ አህጉር ወደላቲን አሜሪካ ቬንዝዌላ ውስጥ ቆይታ አድርጎ ተመለሰ፡፡ ግሩም ነው! ነገሮች እንዴት ነው እየተመሳሰሉ የሚሄዱ ያለ? የሻቬዝና የመለስማ በሚገርም ሁኔታ አንድ ሆነው አረፉት፡፡ ልዩነታቸው ግን መለስ የደረቅ ጣቢያ ወኪልና የችጋር አምባሳደር – የጥቂቶች  ቀፈት ገልባጭ – የብዙዎች አንጀት ቆራጭ ሲሆን ሁጎ ሻቬዝ – ምንም እንኳን በአምባገነንነትና እልኸኛነት ዝንባሌው ክፉኛ ቢታማና ሄንሪክ ካፒሪሌስን የመሰሉ ሣተና ጠላቶችን ቢያፈራም – የድሆች አባትና የሀገር ዕድገት መሠረት በዚያውም የብዙኃንን የፍቅር ልብ የገዛ፣ ለባዕዳን የተፈጥሮ ሀብት ብዝበዛ ሀገሩንና ሕዝቡን አጋልጦ ያልሰጠ በዚህ ሥራውም ውድ ክፍያ ከፍሎ ሲያበቃ ያለውን ሕዝባዊና ሀገራዊ ፍቅር በደሙ ዋዥቶ ያወራረደበት መሆኑ ነው፡፡ … የኤርትራንም ቲቪ ጎብኘት አድርጌ ነበር – ከመመለሴ በፊት፡፡ ‹የሞኝ ልቅሶ ሁልጊዜ አበባየ› እንዲሉ ሰዎች የትና የት በደረሱበት በዚህ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘመን የሻዕቢያ ቲቪ አሁንም የሚያላዝነው ስለትግሉ ዘመን የደርግና የኤርትራ አማፂያን ጦርነት ነው፡፡ ድብልቅልቅ ያለ የበረሃ ጦርነት እያሳዩ – የሆሊውድ ፊልም ይመስል – ተመልካቾቻቸውን ‹እያስተማሩ ያዝናናሉ›፡፡ ባለንበት የምንረግጥ የአፍሪካ ቀንድ ደናቁርት ሆነን መቅረታችን ሆድ ሆዳችሁን አልበላውም? ሰው የምንሆን መቼ ይሆን?

ስለዚያ ብሽቅ ትግሬ-ርትራዊ ዶክተር ተብዬ ይህንንም በነካ ዐይናችን እንመልከት፡- The 1974 anti-feudal Ethiopian popular revolution, … actually ended up unleashing ethno-regional forces that, in 1991, brought the Amhara hegemony into its demise. (op. cit, p. 12፣ emphasis added)

የዘሬን ብለቅ ያንዘርዝረኝ ያለው(ችው) እነማን ነበሩ? እንዲያው ይህ ጥጋበኛና ጠባብነት ለካንስ አፍንና መላ ሰውነትን መደዴ ነው እሚያደርጉ! á‹« በከልቻ የጣር መንፈስ አማራን አርቀን ቀብረናል፤ እንኳንስ ለባንክ የቦርድ አባልነት ለዘበኛም ቢሆን እሱን አታንሱብን፣ በሽታችን ይመጣብንና ያንቀጠቅጠናል እያለ ይወራጫል – á‹« ደደቡ ‹ጄኔራል› – ለነገሩ ለካንስ እርሱም ባጃቢው አጥኚነት በርሱ ‹ተማሪነት› በርቀት ኤምኤውን ይዟል አሉ – ተስፋየ ገ/አብ ነው በመጽሐፉ የነገረን፡፡ ገንዘብ ካለ እንኳንስ ዲግሪና ሕንፃ ቤት መንገድም በሰማይ አለ አይደል? ችግሩ ተንጋለው የተፉት ተመልሶ ሊያውም ወዳፍ መምጣቱ ነው፡፡ ምን አለ ትሉኛላችሁ! [ማሸነፍ ብርቁ ከሆነ ጠላት ይሠውራችሁ!]

ይህ በሽተኛ ሰውዬ – ዓለምሰገድ – በመጥሐፉ ላይ ዳር እስከዳር እሚለው ‹የአማራ ገዢ መደብ ጨቋኝና ጨካኝ ነው› ነው፡፡ በአማራ ጥላቻ ሁለመናው ፍጹም ታውሯል፡፡ አማራን እንደ እባብ ነው የሚቀጠቅጠው – ሌሎች ኢትዮጵያውያን ብሄር/ብሔረሰቦችንማ ከነመፈጠራቸውም ዘንግቷል – አማራ ላይ ብቻ ነው ፊጥ ያለውና እርሱን በየአጋጣሚው የሚጨፈጭፈው – ኢትዮጵያ ውስጥ ካለ አማራ አንድም የሌላ ብሔር ዜጋ ያለም አልመሰለው፡፡ ስለወያኔ ትግሬ ደግሞ ትንፍሽ አይልም፡፡ ኢትዮጵያን ለአማራ ሰጥቶ ሌሎችን ፎሪ አውጥቷቸዋል፡፡ ከቤተ መንግሥት ዘበኛ እስከ መከላከያ ተራ ወታደር ድረስ በትግሬ ስለታጨቀው የወያኔ መንግሥትና የግፍ አገዛዝ አንዲትም ቃል አይተነፍስም – እንዲተነፍስ መጠበቁም ቂልነት ነው – በመሠረቱ፡፡ የለየለት የሻዕቢያና ወያኔ ጉዳይ አስፈጻሚ ቡችላ ኢትዮጵያዊ እንዲሆን አንጠብቅም፡፡ በጥናት ስም የሠራው ዕኩይ ተግባር ግን መቼም ቢሆን  የሚረሳ አይደለም፡፡ አሁንም የኢትዮጵያ አምላክ የሥራውን ይክፈለው፡፡ [ማሸነፍ ብርቁ ከሆነ ጠላት ይሠውራችሁ!]

ለመሆኑ አፄ ምኒልክ አማራ ብቻ ነበሩ? አፄ ኃ/ሥላሴ አማራ ብቻ ነበሩ? መንግሥቱ ኃ/ማርያም አማራ ብቻ ነበር? የጥንቱ አፄ ገላውዴዎስ አማራ ነበሩ? በእውኑ ኢትዮጵያን ያስታዳደረ ሁሉ አማራ ብቻ ነበር? ኢትዮጵያ ከ1983á‹“.ም ወዲህ ካልሆነ በስተቀር በአንድ ዘር ፍጹማዊ የበላይነት እንዲህ እንዳሁኑ አበሳዋን አይታ ታውቅ ይሆን? አማርኛስ የ80 ብሔር/ብሔረሰብ መገናኛ ድልድይ ሆኖ ማገልገሉ ያሸልመው ነበር እንጂ እንደጋለ ብረት ሊያስቀጠቅጠው ይገባ ነበርን? ይሄ ነገር የበሉበትን ወጪት መስበር አይሆንምን? አሁን አማርኛ ባይኖር ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ በምልክት ቋንቋ ሊገዛ ነበረ ወይ? ምን ዓይነት የሚመር ቀልድ ነው? ምሥጋናው ፅድቁ ቀርቶ ዕልቂቱ ኩነኔው ቢቀር ምናለበት? ለምን ግፍ ለልጆቻቸው ያቆያሉ? ለምን ያናግሩናል? ለምን መገፋታችንን ተቋቁመን፣ ችግራችንን ችለን ለፈጣሪያችን እየጮህን የመከራ ሕይወታችንን እርሱ እስከፈቀደ ድረስ እንድንገፋ አይተውንም? ወይንስ የጊዮርጊስስ ግብር የበላ ሳይነኩት ይለፈልፋል እንደሚባለው ሆኖ ይሆን? አማርኛ እየተናገረ አራት ኪሎን የተቆጣጠረ ሁሉ አማራ ነው እየተባለ ይህ ምሥኪን ሕዝብ ላይ ማንም እንዲያስታውክ የፈቀደለት ማን ይሆን? ጊዜ? ፈጣሪ? ዕድል? የታሪክ አጋጣሚ? ጉልበት? ገንዘብ ወይንስ የነዚህና የመሰል ቅንብሮች ውሁድ? በዚህ ዓይነት አማርኛን የመጀመሪያ ቋንቋው ያህል አጣርቶ እየተናገረ አማሮችን ሙሉ በሙሉ ለመጨረስ ተነስቶ የነበረው ግን ልቡን አይቶ እግሩን እንደነሳው እባብ የዕቅዱን እኩሌታ እንኳን ሳያከናውን በአጭር የተቀጨው መለስ ዜናዊስ ለምን የአማራው ገዢ መደብ አልተባለም? ከዋሹ አይቀር እንዲያ ማለትም ይቻል ነበር፡፡ ታዋቂው ገጣሚ – ገሞራው – ምን አለ? “ምን ያለ ዘመን ነው ዘመነ ግርምቢጥ፤ ውሻ ወደ ግጦሽ አህያ ወደ ሊጥ፡፡” ቀን የሰጠው ዓለምሰገድ ቅሉ በውሸት ቱማታ ጥናት ተብዬ የጠላ ቤት ወሬው የአማራን አከርካሪ ሊሰብር የገማ ብዕሩን ማንሳቱ ማንን ቢንቅ ይሆን? ለነገሩ ከራሱ ሌላ ማንንም ሊንቅ አይችልም – ናቂ ተናቂ ነውና፡፡ በዕብሪተኛው አባቱ ቃል – ‹ወራዳ ነው › – እደግመዋለሁ – ‹ወራዳ ነው› – እንዳልለው ከጨዋነት አንጻር ትዝብት ውስጥ ሊጥለኝ ይችላልና ለፈጣሪ ብቻ እተወዋለሁ፡፡ [ማሸነፍ ብርቁ ከሆነ ጠላት ይሠውራችሁ!]

ለአንዱ ጓደኛየ ይህን ጉዳይ ስነግረው ‹ይህ የውሻ ልጅ ያላለው ነገር የለም በለኛ› ቢለኝ ጊዜ ‹አይ፣ ተው ስድብን ለሰዳቢ መተው እንጂ ሲሳደቡ አብሮ መሳደብ ከትሁት ሰው አይጠበቅም› ብዬ አበረድኩት፡፡ ‹ለዚህ የሳዋ ቤት ቱሪናፋው ደግሞ ታሪካዊ ጠላቶቻችን የገንዘብ ድጋፍ አድርገውለት እኮ ይሆናል›  አለኝና በማከልም “ስሜትና የቡና ቤት ቃርሚያ መሆኑን እያወቁ እንዲያ አድርገው ከሆነ ‹የጠላትህ ጠላት ወዳጅህ ነው› ከሚለው እሳቤ በመነሳት መሆን አለበት፡፡ አለበለዚያ ቃለ መጠይቅና የቡና ላይ ጨዋታ ተይዞ ወይም አንድ ሰው በራሱ ተነሳሽነት በጽሑፍም ይሁን በቃል፣ በጠባብ መድረክም ይሁን በሰፊ አደባባይ ያንጸባረቀውን ሃሳብ በዋቢነት እየጠቀሱ ከደንብ ውጪ ሰውን ማሳሳት ተገቢ አይደለም ብቻ ሳይሆን ሪሰርችን መግደልና ተኣማኒነቱን ማሳጣት ነው፡፡” አለኝ፡፡ እኔም ሌላ ሃሳብ አስከተልኩ፡- እገሌ እንዳጫወተኝ “አፄ ኃ/ ሥላሴ አሥመራ ላይ በሕዝብ ፊት ‹ኤርትራ መሬቷን እንጂ ሕዝቧን አንፈልግም› ብለው ተናግረዋል፣ ወዘተ. የሚል ከአሉቧልታ ውጪ የሚጨበጥ ነገር የሌለው ነገር በጥናት ስም ማውጣት ወንጀል ብቻ ሳይሆን ሥርየት የሌለው ኃጢኣትም ነው፡፡ ጊዜ ሰጠኝ ብሎ ያለ የሌለ ዕድፍን በሕዝብ ላይ መለደፍ አይነጋ መስሏት ቋቷ ውስጥ የዓለምሰገድን የሚመሰል ቆሻሻዋን እንዳስቀመጠችው ሴት መሆን ነው፡፡ ነውርን ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ ዝንታለሙን ይሉኝታቢስ መሆን ከሰውነት ተራ መውጣት ይመስለኛል፡፡ ሁሉም ነገር ያልፋል፡፡ መጽሐፍ የያዘው ነገር ግን በቀላሉ አያልፍም፡፡ እስከወዲያኛው ያስተዛዝባል ፤ ከዚያ ያለፈ መዘዝም ሊያስከትል ይችላል፡፡ አንዴ ከመናገርህ ሁለቴ አስብ የሚባለውም ለዚህ ነው፡፡ የጭቃ ጅራፍን ከማንጓት በፊት የምንለው ነገር ሊያመጣ የሚችለውን የዞረ ድምር መመልከት ተገቢ ነው፡፡” አልኩት፡፡ [ማሸነፍ ብርቁ ከሆነ ጠላት ይሠውራችሁ!]

ይህን ቆሻሻ መጽሐፍ ሳነብ ጎን ለጎን እያየሁ የነበረው በስሙ እየተነገደበት ያለውን ምሥኪን አማራ ሳይሆን የአሁኑን የትገሬውን የገዢ መደብ ነበር፡፡ “ያ የውሻ ልጅ ያላጤነው እንግዲህ ይህን ነው” አለና á‹« ጓደኛየ ነገር ጀመረኝ፡፡ “የኔ ዘመዶች ምን እያደረጉ ነው? ይህን ነገር ስለአማሮች ስናገር እነሱንስ አያስወቅስብኝ ይሆን ወይ? ማለት ሲገባ ዐወቀች ዐወቀች ሲሏት የባሏን መጽሐፍ እንዳጠበችው ሴት የራሱን ጉድ ነው የዘከዘከው፤ ትዕቢት ደግሞ ኅሊናን በዕብሪት ሞራ ይሸፍናል፡፡ እንጂ አማራስ ይህ ጭንጋፍ የዘበዘበውን ያህል ኃጢኣት በማንም ላይ ይሠራል ብዬ አላምንም፤ ጥፋት ነበረበት ቢባልም እንኳን በንጽጽራዊ ዕይታ ኢምንት ጥፋትን በብዙ ሺህ ዕጥፍ በሚገመት የጥፋት ቁልል አጠፌታውን በመመለስ አማራን እንደክርስቶስ ይህን ያህል መውገር የፈሪ ዱላ ያስብላል፤ ይህ ነገር ደግሞ ከባህልም ከሃይማኖትም አብሮ ከመኖር የቆዬ ትውፊትም አንጻር ለወደፊቱ አያቀባብርም፡፡ አማራ በአማራነት ተደራጅቶ የማንንም ንብረት አልዘረፈም፡፡ ጥፋት አልነበረም ማለት ግን አይደለም፡፡ አማራ በአማራነት ተሳስቦ ቡድናዊ ጥፋት በማንም ላይ ለማድረስ የሚያስችል ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ ዝግጅት ባይኖረውም በተናጠል ደረጃ ጥፋት ያጠፉ አማርኛ ተናጋሪዎች መኖራቸው አያጠያይቅም፡፡ ሆኖም ጥፋትን በጥፋት መመለስ ሌላ ሦስተኛ ጥፋት እንዲጸነስ በር መክፈትና በቀለኝነትን ማበረታታትም ነው…” እያለ ያወርደው ገባ – ብሶቱን፡፡ ባላቋርጠው ማቆሚያ ባልኖረው፡፡

 

ይህ ሰውዬ ብዙ የሀሰት ውንጀላዎችን በአማራው ላይ ደፍድፏል፡፡ ‹አማሮች የኤርትራን ንብረት ዘርፈዋል፤ ከጣሊያን መውጣት በኋላ የአየር ላይ በገመድ መንሸራተቻ የትራንሰፖርት መሣሪያዎችን ነቅለው ሸጠዋል…› ብሏል፡፡ á‹« እውነት መሆን አለመሆኑን የሚያጣራ ያጣራው – እኔ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር ተፈጽሞ እንኳን ቢሆን  አማራ ብቻ ተነጥሎ ያን አይሠራም ባይ ነኝ፡፡ ይህ ሰው በዚህ ብቻ አይገታም፡፡

አማራን ለማዋረድ ካለው ያልተገራ ስድ ፍላጎት የተነሳ የኤርትራ ክፍለ ሀገር ሰዎችን እጅግ የሰለጠኑ አድርጎ ሲያቀርብ አማሮችን በዚያው አንጻር እጅግ ኋላ ቀርና ከፍ ሲል እንደተገለጸው ‹እንኳንስ ሌላ ሕዝብ ሊያስተዳድሩ ራሳቸውንም ማስተዳደር አይችሉም› በማለት በማይማዊ ድፍረቱ አንጓጧል፡፡ በሌላ ምዕራፍ ደግሞ ኤርትራውያን በጣሊያኖች ሸረኛ አገዛዝ ከአምስተኛ ክፍል በላይ እንዳይማሩ የተደረጉ ማይማን፣ ከተራ የጥበቃና አትክልተኛ ሥራዎች በስተቀር ከፍ ባሉ ቅጥሮች እንዳይመደቡ የሚከለከሉ አላዋቂና የተዘነጉ ዜጎች እንደነበሩ ያወሳል፡፡ ሰውዬው የሚለውን የሚያውቅም አይመስልም፡፡ እዚህ የሚለውን እዚያ ያፈርሰዋል፡፡

በሌላም በኩል የ‹አማራውን ገዢ መደብ› ለማንኳሰስ የአፄው ወታደሮች በሸበጥ ጫማ ወደኤርትራ እንደሄዱ ይናገራል፡፡ ቀጥሎም ከመሀል ሀገር ለማስተማር ወደኤርትራ የሄዱ አማሮች በባዶ እግራቸው ክፍል ውስጥ እንደሚገቡና እንደሚያስተምሩ በዚያም ምክንያት የዚያች ግዛት ዜጎች በአማሮች እንደሚያፍሩ ይናገራል፡፡ የሚገርም ነው፡፡ የሁለት ብር የዘመኑን የቻይና ፍራቢ ጫማ አጥተው ባዶ እግራቸውን ወደ ክፍል ገብተው አስተምረው ከሆነ የዚያን ጊዜዎቹ አስተዳደሮች – አሁን በሕይወት ያሉቱ – ሊጠየቁ ይገባል፡፡ ነገር ግን እንደኔ እንደኔ ይህ ዓይነቱ ወሬ ተራ የተርቲብ ወሬ እንጂ በፍጹም እውነትነት ያለው አይመስለኝም፡፡ ያኔ መምህራን ንጉሥ ነበሩ፡፡ እንኳን ያኔ አሁን በባዶ እግራቸው አልሄዱም፡፡ የሚገርም ዓለምሰገድ ነው እባካችሁን፡፡ ይህንን ለይቶለት ያበደን ሰው ጠበል መውሰድና የተሣፈረበት በሚሊዮን የሚቆጠር አጋንንት እንዲወጣለት ማድረግ ከጨዋ አንባቢና ከቅን ቤተዘመድ ይጠበቃልና ሰውዬው በሕይወት ካለ እባካችሁን አትጨክኑበት፡፡ መለስ የአማራ ጥላቻው አናቱ ላይ ወጥቶ በአጭር ተቀጨብን፡፡ የዚሁ ዋልጌ ሟች ጓደኞችም በአብዛኛው  ገሣ ለብሶ ከብት ከመጠበቅ ውጪ ሌላው ቀርቶ ከአድማስ ባሻገር ሌላ አገር ያለ በማይመስለው በዚሁ የአማራ ሕዝብ ላይ ጦራቸውን ሰብቀው በምናብም በተግባርም ሊጨርሱት ቢቋምጡም የነሱም የአሁንና የወደፊት ዕጣ የሚያምር አይመስልም፤ አንዱ የአንዱን የቀብር ጉድጓድ መቆፈሩ በእስካሁኑ ሁኔታ የማያዋጣ መሆኑን ያላወቁ ጅሎች ለጊዜው በሚያብለጨልጭ ዓለማዊ ሀብትና ንብረት እየተታለሉ ወንድማቸውን መቅበሩን ተያይዘውታል – እነሱም ተራቸው ሲደርስ የማይቀርላቸው መሆናቸውን ግን ረስተውታል፡፡ ባለጌ ባልጎ ያባልጋል፡፡ ኤዲያ! ሊያልፍ ያለፋል አሉ? ለማንኛውም – [ማሸነፍ ብርቁ ከሆነ ጠላት ይሠውራችሁ!]

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 14, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 14, 2013 @ 11:05 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar