www.maledatimes.com “ከእኔ ልጅ ጋር ሐረር ከተማ ውስጥ አራት ሰው በፓሊስ ነዳጅ እየተደፋበት በእሳት ተቃጥሎ ሞቷል” - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

“ከእኔ ልጅ ጋር ሐረር ከተማ ውስጥ አራት ሰው በፓሊስ ነዳጅ እየተደፋበት በእሳት ተቃጥሎ ሞቷል”

By   /   March 16, 2013  /   Comments Off on “ከእኔ ልጅ ጋር ሐረር ከተማ ውስጥ አራት ሰው በፓሊስ ነዳጅ እየተደፋበት በእሳት ተቃጥሎ ሞቷል”

    Print       Email
0 0
Read Time:22 Minute, 25 Second

ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ(ከሀረር ሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈፅሞባቸው የተባረሩ አዛውንት)

“ልጄ በእሳት ተቃጥላ እንድትሞት ተደርጋ፣ ቤቴን ተነጥቄና ንብረቴ ወድሞ ከሀረር ተባረርኩ” ሲሉ አንዲት የ67 አመት ባልቴት በተለይ ለፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ አስታወቁ፡፡ ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ የሚባሉት እኚሁ እናት የ75 ዓመት አዛውንት የሆኑት ባለቤታቸውም እንደ እሳቸው ሁሉ ጎዳና ላይ መውደቃቸውን ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዘጋቢ ከዕንባቸው ጋር እየታገሉ አስረድተዋል፡፡“በሐረር ከተማ ቀበሌ 17 ውስጥ ከ30 ዓመት በላይ ኖሬ፤ ሀብትና ንብረት አድርቼ እኖር ነበር አሁን ግን በአካባቢው እንዳልኖር ተደርጌያለሁ” የሚሉት ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ “ከ30 ዓመት በላይ የኖርኩበትን ቤቴን የወረዳው አስተዳዳሪ እና የወረዳው ፓሊስ አዛዥ አስጠርተው ቤትሽን ለወ/ሮ አኒሳ መሐመድ ሸጠሽ ግቢውን እንድታስረክቢያት አሉኝ፡፡ እኔ ቤቴን የመሸጥ ሐሳብ የለኝም፡፡ ቤቴን ሸጪ የት እወድቃለሁ? አልሸጥም አልኳቸው እንቢ ካልሽ ከአገራችን እናባርራሻለን በገንዘብ አልሸጥም ካልሽ በባዶሽ ተባረሽ ወደ አገርሽ ትሄጃለሽ አሉኝ፡፡ እኔ ሌላ አገር የለኝም የምሄድበትም ቦታ የለኝም መንግስት ባለበት አገር ቤትሽን ተቀምተሽ ውጪ የሚለኝ የለም ብዬአቸው ተመለስኩኝ” በማለት የችግሩ መነሻ ነው ያሉትን ጉዳይ ወደኋላ መለስ ብለው ያስረዳሉ፡፡
ጎስቋላዋ የ67 ዓመት ባልቴት በመቀጠልም “በማግስቱ እኔ ቡና አፍልቼ፣ ባለቤቴም ጫማውን አውልቆ ፍራሽ ላይ አረፍ ብሎአል፤ አንድ ፓሊስ በሩን በሰደፍ እና በእርግጫ መቶት በሩን በረገደው፡፡ ምንድነው? ብለን ስንወጣ ከ30 በላይ ፓሊሶች ቤታችንን ከበውታል፡፡ ይህች ናት፡፡ ነይ ውጭ! ብሎ ለሁለት ሶስት ሆነው ጎተቱኝ፡፡ እባካችሁ ምን አደረኩ ብዬ ስለምናቸው አንቺ ለህግ አልገዛ ያልሽ አመጸኛ ነሽ! ወንጀለኛ ነሽ እያሉ መሬት ለመሬት ጎተቱኝ፡፡ እባካችሁ ምንም የሰራሁት ወንጀል የለም ብዬ ጮኩኝ፡፡ ጎረቤት ተሰበሰበ ምንድነው ብሎ ጠየቀ ማንም ምላሽ አልሰጠም” የሚሉት ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ ሟች ልጃቸውን በሀዘን ተውጠው እያስታወሱ ይቀጥላሉ “ልጄ ባል አግብታ የምትኖረው ሌላ ቦታ ነው፡፡ ቀን ቀን ምግብ እየሰራች ትሸጣለች ፓሊሶች እናትሽን ከበው እየደበደቡ ናቸው ብሎ ጎረቤት ሲደውልላት ሮጣ መጣች፡፡ ደርሳ ምን አድርጋ ነው ብላ ብትጠይቅ ቤቱን አስረክቢ ስትባል እንቢ ብላ ነው አሏት፡፡ የተወለድንበትና ያደግንበትን ቤት ከህግ ውጭ እንዴት እንነጠቃለን ብላ ስትጮህ ጥላው ሄዱ” በማለት በለቅሶ ያስረዳሉ፡፡
ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ በመቀጠልም “ያንለቱኑ ማታ ልጄ ምግብ የምትሸጥበት ቦታ ሁለት ሰዎች ተመጋቢ መስለው ከገቡ በኋላ (ረመዳን የተባለ ፓሊስና እንዳለ
ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ(ከሀረር ጠሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈፅሞባቸው የተባረሩ አዛውንት)ግርማ የተባለ ወጣት) ቤቱን አስረክቡ ስትባሉ አናስረክብም የምትሉት ለምንድነው ብለው ረመዳን ልብሷና ሰውነቷ ላይ ጋዝ ሲደፋባት እንዳለ ግርማ የተባለው ላይተር ለኩሶ አቃጥለዋታል፡፡ ሳትሞት ሆስፒታል ደርሳ ነበር፡፡ በማግስቱ አዲስ አበባ አምጥቼ ላሳክም መኪና ተከራይቼ ይዤ ስወጣ ፓሊስ እዚህ ትታከም እንጂ ከሐረር አትወጣም ብሎ ከለከለኝ፡፡ እኔም ገንዘብ ካለኝ እንኳን አዲስ አበባ አሜርካን ወስጄ ባሳክም ለምን እከለከላለሁ ብዬ ብጮህ ባለቅስ ማንም ሊደርስልኝ አልቻለም፡፡ ልጄ ህክምና አጥታ ሞተች፡፡” ብለዋል፡፡
ባልቴቷ ከልጃቸው ሞት በኋላ የደረሰባቸውን በምሬት ያወጋሉ “እኔንም ከቤቴ አስወጥተው ቦታውን ሺጭላት ላሏት ሴት ሰጧት፡፡ አሁን ቦታዬ ላይ ፎቅ እየተገነባ ነው፡፡
እኔና ባለቤቴ ግን ጎዳና ተጣልን፡፡ የአካባቢው ህብረተሰብ አዋጥቶ የሰጠኝን 3ሺ ብር እንድ ፓሊስና አንድ ደላላ መጥተው ነጠቁኝ፡፡
ሐረር ውስጥ አደሬ ወይም ኦሮሞ ካልሆንክ አቤት የሚባልበት ቦታ የለም፡፡ አማራ ነው ከተባለ ሁሉም ባለስልጣን በደረሰበት ግፍና ስቃይ ይስቅበታል፡፡ በደርግ ጊዜ የሐረር ፓሊስ አዛዥ ትግሬ ነበር፤ የማረሚያ ቤት አዛዥም ትግሬ ነው፡፡ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ትግሬ ነው፡፡ ለምን ትግሬ ሆነ ያለ አንድም ሰው የለም፡፡ ዛሬ በሀረር
በየትኛውም መስሪያ ቤት አማራ ባለስልጣን የለም፡፡ ባለቤቴ ኦሮሞ ነው፡፡ ልጆቼም ኦሮሞ ናቸው፡፡ እኔ አማራ በመሆኔ ብቻ ይህ ሁሉ ጉዳት ተፈጸመብን፡፡” የሚሉ
ወይዘሮዋ የተፈፀመባቸው የሰብአዊ መብት ጥሰት ዘራቸውን መሰረት ያደረገ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡
አክለውም “አዲስ አበባ መጥቼ ለእንባ ጠባቃ ተቋም አመለከትኩኝ፡፡ ፌደራል እንባ ጠባቂ ተቋም እንዴት እንዲህ ይፈጸማል ብለው ይዘውኝ ሐረር ተመለሱ፡፡ የቤቴ
ካሳ እንዲከፈለኝ ተወሰነልኝ፡፡ የክልሉ ባለስልጣናትም እሺ ይፈጸምሎታል ብለው ቃል ገቡልኝ፡፡ እንባ ጠባቂዎቹ ወደ አዲስ አበባ ተመልሱ፡፡ እነሱ ከተመለሱ በኋላ ግን
ምንም መፍትሄ አልሰጡኝም፡፡ በድጋሚ አዲስ አበባ መጥቼ ለእንባ ጠባቂ ተቋም ባመለክት እነሱም ውሳኔያቸውን እንደ አጀማመራቸው ሊያስፈጽሙልኝ አልቻሉም፡
፡ ጉዳዬንም ለመስማት ፍቃደኛ አልሆኑም፡፡” በማለት የበደላቸውን ስፋት ለፍኖተ ነፃነት ዘጋቢ በዝርዝር አስረድተዋል፡፡ “ዛሬ እኔ አዲስ አበባ ላይ ባለቤቴ ደግሞ
ሐረር ላይ ጎዳና ላይ ነን፡፡ መፍትሔ ማግኘት አልቻልኩም” ሲሉ ተስፋ መቁረጥና ምሬት ተሞልተው በለቅሶ የመንግስት ያለህ … የህዝብ ያለህ በማለት ጥያቸውን ያቀርባሉ፡፡

የወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማን ጉዳይ አስመልክቶ የፌደራሉ እንባ ጠባቂ ተቋም ለሐረሪ ክልላዊ መንግስት ጸጥታ ቢሮ የጻፈውን ደብዳቤ እንደተመለከትነው ደብዳቤው ከዚህ በፊት ስለጉዳዩ ተጠይቆ መልስ አለመስጠቱን በማስታወስ አሁን በድጋሚ በ 15 ቀን ውስጥ መልስ እንዲሰጥ ያለበለዚያ በህግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት አስፈላጊውን
እርምጃ እንደሚወስድ የሚገልጽ ነው፡፡ ሆኖም የእምባ ጠባቂ ተቋም ውሳኔ ባልቴቷንና ባለቤታቸውን ከጎዳና ተዳዳሪነት የሚታደግ አልሆነም፡፡
በጉዳዩ ላይ የፊደራል እንባ ጠባቂ ተቋም አስተያየት እንዲሰጥበት ወደ ተቋሙ ህዝብ ግንኙነት ክፍል በማምረት ባለሙያዎችንም አነጋግረን ነበር፡፡ በቅድሚያ ያነጋገርናቸው የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ ጉዳዩን ከስሙንና በእጃችን ያለውን መረጃ ከተመለከቱ በኃላ ወደ ሌላው የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ መሩን፡፡እሳቸውም በተመሳሳይ ሁኔታ ማስረጃችንን ከተመለከቱ በኃላ ይህንን ጉዳይ የሚያውቁት ዋና አማካሪው አቶ ቀነአ ሶና ናቸው፡፤ እሳቸውን አነጋግሩ አሉን፡፡ አቶ ቀነአን በወቅቱ ማግኘት አላቻልንም፡፡ በሌላ ጊዜ ተመልሰን ቢሮአቸው ያሉትን የተቋሙን ሰራተኛ አቶ ቀነአን እንደምንፈልግ አስረዳናቸው፤ አቶ ቀነአን ወደ መስክ ወጥተዋል፡፡ ሰሞኑን ቢሮ አይገቡም አሉን፡፡ በዚህ ምክንያት የፌደራሉን እንባ ጠባቂ ተቋም አስተያየት ማካተት አልቻልንም፡፡
ጉዳዩ ተከቷል ወደ ተባለለት ወረዳ ፖሊስ ደወልን የሐኪም ወረዳ ፖሊስ ወንጀል መከላከል ሀላፊ የሆኑትን ሳጂን ተሾመ ሰይፉን አግኝተናቸዋል፡፡ ወ/ሮ ኢትዮጵያ
ይልማ ደረሰብኝ የሚሉትን በደል ወቅቱን ጠቅሰንም አስረድተናቸዋል፡፡ ሆኖም ሳጂን ተሾመ ሲመልሱ ‹‹እኛ ፖሊሶች በየሁለት ዓመቱ እንቀያየራለን፡፡ አሁን በዚህ ወረዳ
ያለነው ከሁለት ዓመት ወዲህ ተዛውረን የመጣን ነን፡፡ ስለዚህ ጉዳይ የሚያውቅ ሰው የለም፡፡ በአሁኑ ወቅት በወረዳችን “ከእኔ ልጅ ጋር ሐረር ከተማ ውስጥ አራት ሰው በፓሊስ ነዳጅ እየተደፋበት በእሳት ተቃጥሎ ሞቷል” ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ(ከሀረር ሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈፅሞባቸው የተባረሩ አዛውንት)የመንግስት ሰራተኞች በግድ ለአባይ ግድብ ከደመወዛቸው ላይ እንዳይቆረጥብን ሲሉ ፒቲሽን ተፈራርመው ለመንግስት አቀረቡ፡፡
በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች ከዚህ በፊት ለአንድ ዓመት አቅማችን ሳይፈቅድ ከወር ደመወዛችን ላይ ለአባይ ግድብ ሲቀቆረጥ ነበር፤ አሁን ግን ካለብን የኑሮ ውድነት የተነሳ አቅማችን አይፈቅድም ስለዚህ ያለፈቃዳችን ሊቆረጥብን አይገባም ሲሉ የመንግስት ሰራተኞች ፒቲሽን ተፈራርመው ማስገባታቸው
የደረሰን መረጃ አመልክቷል፡፡
ሰራተኞቹ በቁጥር 36 የሚደርሱ በዞኑ በተለያየ የመንግስት መስሪያ ቤት የሚሰሩ እንደሆኑ የተገለፀ ሲሆን እስካሁን የተሰጣቸው ምላሽ ግን የለም፡፡ እንደ ሰራተኞቹ ገለፃ ከሆነ “በአሁን ወቅት በሀገሪቱ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ተከስቶ እያለ ያለፈቃዳችን ለአንድ ዓመት ያህል ተቆርጧዋል፤ አሁን ግን አንችልም፡፡ ስለዚህ አሁንም በኢህአዴግ
ካድሬዎች አማካኝነት ያለፈቃዳችን ከደመወዛችን ላይ እንዳይቆረጥ እስከመጨረሻው እንታገላለን” ሲሉ አስታውቀዋል፡፡
በተለይ በዞኑ አረካ ወረዳ ያሉ የግብርና ሰራተኞች ድርጊቱን ተቃውመው አቤቱታ ለወረዳው አስተዳደርና ግብርና ፅ/ቤት ቢያቀርቡም አቤቱታቸውን ውድቅ እንዳደረጉባቸው በመግለፅ በጋራ የተስማሙ ሰራተኞች እስከ ፍርድ ቤት ድረስ በመሄድ ክስ እንደሚመሰርቱ አስታውቀዋል፡፡
ስለጉዳዩ ለማጣራት የዝግጅት ክፍሉ ወደ ወረዳው ዋና አስተዳደር አቶ ደመቀ ደጀኔን ለማግኘት ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ቢደረግም አልተሳካም፡፡ ይሁን እንጂ ወደ ወረዳው ግብርና ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ጴጥሮስን ስለጉዳዩ ጠይቀናቸው “ተቆረጠ የተባለው ደመወዝ ሰራተኞቹ በተስማሙት መሰረት ነው፤ በርግጥ በታህሣስ 2005 ዓ.ም. ሊቆረጥ ሲል ወቅቱ በዓል ስለነበረ እንዳይቆረጥብን ስላሉ ቅሬታቸውን የተቀበልን ቢሆንም ኋላ ከጥር 2005 ዓ.ም. ጀምሮ 2ኛ ዙር እንዲቆረጥ በተስማሙት መሰረት መቆረጥ ተጀምሯል፡፡ በዚህም ዙሪያ አንዳንድ ግለሰቦች ከወር ደመወዛቸው ላይ እንዳይቆረጥ ቅሬታ ያቀረቡ ቢሆንም ከተጀመረ በኋላ ማስተናገድ እንደማንችል ተነጋግረን ተግባብተናል” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ አረካ ወረዳ በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የተወለዱበትና ምርጫ የተወዳደሩበት ስፍራ መሆኑ ይታወቃል፡፡
የመንግስት ሰራተኞች በግድ ከደመወዛቸው ላይ ለአባይ ግድብ መቆረጡን በመቃወም ፊርማ አሰባሰቡ ሮመዳን የሚባል ፖሊስ የለም፡፡ ምናልባት የወረዳው መስተዳድር የሚያውቁት ነገር ካለ እነሱን ብትጠይቁ ይላል፡፡›› በማለት መልሰውልናል፡፡በአሁኑ ጊዜ ያሉትን የወረዳውን አስተዳዳሪ አቶ ኢስማኤልንም ስለጉዳዩ ጠይቀን በሰጡን መልስ ‹‹እኔ በቅርብ ጊዜ ነው የመጣሁት ስለዚህ ጉዳይ የማውቀው ነገር የለም፡፡
የሚያውቁት ነገር ካለ ከእኔ በፊት የነበሩትን ጠይቋቸው›› ብለውናል፡፡ ከእሳቸው በፊት የወረዳው አስተዳዳሪ የነበሩትን አቶ ጀማል አህመድን አፈላልገን ጠየቅናቸው፡፡ “እኔ ድርጊቱ ተፈፀመ በምትለኝ ወቅት እዚያ ወረዳ አልሄድኩም፡፡ ስለዚህ ጉዳይ የማውቀው ነገር የለም፡፡ ከእኔ በፊት የነበረውን ሰው አፈላልጋችሁ ጠይቁ ብለውናል፡፡” ከእሳቸው በፊት የነበሩትን አስተዳዳሪ ማንነትና አድራሻ ማግኘት ባለመቻላችን ዜናውን በተገቢው ሁኔታ ሚዛናዊ ማድረግ አልቻልንም፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 16, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 16, 2013 @ 8:42 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar