www.maledatimes.com አዲስ አበባ ውስጥ የተፈጠረው ግጭት ወደ ብሔር ግጭት አድጎ የ8 ሰዎችን ህይወት ማለፉን ተጠቆመ፡፡ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አዲስ አበባ ውስጥ የተፈጠረው ግጭት ወደ ብሔር ግጭት አድጎ የ8 ሰዎችን ህይወት ማለፉን ተጠቆመ፡፡

By   /   March 16, 2013  /   Comments Off on አዲስ አበባ ውስጥ የተፈጠረው ግጭት ወደ ብሔር ግጭት አድጎ የ8 ሰዎችን ህይወት ማለፉን ተጠቆመ፡፡

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 41 Second

በአዲስ አበባ በሚገኘው ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ስሙ ቦሌ ለሚ በሚባል አካባቢ ማክሰኞ መጋቢት 3 ቀን 2005ዓ.ም. ኮብልስቶን በሚሰሩ ሰዎችና በአካባቢው ነዋሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት 8 ሰዎች መሞታቸውንና በርካታ ሰዎች መቁሰላቸው ተጠቆመ፡፡
በፍኖተ ነፃነት ዘጋቢዎች የተጠናቀረው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ የግጭቱ መንስኤ የሞባይል መጥፋት እንደሆነ እና በዚህም ኮብልስቶን ትሰራ የነበረችን የአንዲት የአካባቢው ነዋሪ ሴት ጡት ሌላው ሰራተኛ በመቁረጡ ህይወቷ ማለፉን ተከትሎ በአካባቢው ነዋሪዎችና በኮብል ስቶን ሰራተኞቹ መሀከል ግጭት ተነስቷል፡
፡ በዛው ዕለት ፀቡን ለማረጋጋት የሞከረ ፖሊስም በኮብልስቶን ተመቶ ወዲያው ህይወቱ ማለፉን ጠቁመዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ጉዳዩ ወደ ብሔር ግጭት ተለውጦ ፀቡ እስከ ሐሙስ መጋቢት 5 ቀን መዝለቁንና ህይወቷ ያለፈው ወጣት የአካባቢው (ኦሮሚያ) ተወላጅ በመሆኗ ጉዳዩ ወደ ማኀበረሰቡ በመድረሱ በርካታ የአካባቢው ሰዎች ከአያት ኮንዶሚኒየም እስከ ቦሌ ለሚ ድረስ ከበባ በማድረግ በሰራተኞች መካከል የኢህአዴግ አደራጅና ሰላይ ናቸው የተባሉ 6 የወላይታ ተወላጆችን በመግደልና በርካታ ሰዎችን በማቁሰላቸው በአካባቢው ከ3 ተሸከርካሪ ያላነሱ የፌደራል ፖሊሶች ግጭቱን  ለማረጋጋት ቢገኙም ለማረጋጋት  እንዳልቻሉ ሆኖም በርካታ የአካባቢው  ነዋሪዎችን ወስደው እንዳሰሩ የዓይን  እማኞች ገልፀዋል፡፡ ይሁን እንጂ እስከ አሁን ከፖሊስ ወገን የተሰጠ ማረጋገጫ የለም፡፡ 

የዝግጅት ክፍሉ ጉዳዩ በቀጥታ  ይመለከተዋል ወደ ተባለው ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መረጃ ክፍል ስለጉዳዩ ለማረጋገጥ ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም ለጊዜው አልተሳካም፡፡ ዘገባው ወደ ህዝብ እንዲደርስ እስከተደረገበት መጋቢት 7 ቀን  2005ዓ.ም. ድረስ ቀደም ሲል በርካታ ሰዎች የኮብልስቶን ስራ ይሰሩበት
የነበረው አያት ጨፌ እና ቦሌ ለሚ የሚባል አካባቢ ማንም ሰው እንዳይገባ የተደረገ ሲሆን ከሰራተኞች ጋር እዛው  በሚገኝ ቀበሌ ለጊዜው ማንነታቸው
ያልታወቁ የመንግስት ባለስልጣናት እያወያዩ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡ ችግሩ እስኪፈታም በአካባቢው እስከ ሰኞ መጋቢት 10 ቀን 2005ዓ.ም. ድረስ ስራ እንደለሌም ምንጮቻችን ከስፍራው ጠቁመዋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 16, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 16, 2013 @ 8:49 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar