www.maledatimes.com የአንድነት አባል በፀጥታ ኃይል የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የአንድነት አባል በፀጥታ ኃይል የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው

By   /   March 16, 2013  /   Comments Off on የአንድነት አባል በፀጥታ ኃይል የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 45 Second

በሰሜን ጎንደር ዞን ደምቢያ ወረዳ በምትገኘው ቆላድባ ከተማ የአንድነት ፓርቲ አባል ላይ በአካባቢው የፀጥታ ኃላፊ የግድያ ሙከራ እንደተደረገባቸው ተገለፀ፡፡
የአንድነት ፓርቲ አባል የሆኑት አቶ እያዩ ተኮላ እንየው መጋቢት 1 ቀን 2005 ዓ.ም. በከተማው የቀበሌ 02 የፀጥታ ኃላፊ በሆኑት አቶ እያዩ ካሳ በጥይት የግድያ
ሙከራ እንደተደረገባቸው ለፍኖተ ነፃነት የደረሰው መረጃ ያረጋግጣል፡፡
የአካባቢው ምንጮች ለፍኖተ ነፃነት እንደገለፁ ከሆነ ተኩሱ የተከፈተው ከሌሊቱ 7፡00 ሰዓት ላይ የግል ተበዳይ በመኖሪያ ቤታቸው እያሉ እንደሆነና
የቀበሌው ሀላፊም ከዚህ በፊት ስልክ እየደወሉ ያስፈራሯቸው እንደነበር ያስረዳል፡፡ የጋዜጣው ዝግጅት ክፍል የግድያ ሙከራ የተደረገባቸውን አቶ እያዩ ተኮላን
ጠይቀናቸው “አዎን በጦር መሳሪያ ቤቴ ድረስ በመምጣት የቀበሌው ኮማንደር እያዩ ካሳ በተጠቀሰው ቀን ተኩስ ከፍተውብኛል፣ ከዚህ በፊትም በተንቀሳቃሽ ስልኬ እየደወሉ ያስፈራሩኛል፤ ስለዚህ ክስ እየመሰረትኩ ነው” ሲሉ ምላሽ ሰጥተውናል፡፡ ተኩስ በመክፈት የግድያ ሙከራ አድርገዋል የተባሉትና የአካባቢው የፀጥታ
ኃላፊ በሆኑት አቶ እያዩ ካሳ በበኩላቸው “እኔ የፈፀምኩት ተኩስም ሆነ ያደረኩት የግድያ ሙከራ የለም” ሲሉ አስተባብለዋል፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 16, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 16, 2013 @ 8:57 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar