www.maledatimes.com የታማኝ በየነ መልእክት ከአውሮጳ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የታማኝ በየነ መልእክት ከአውሮጳ

By   /   March 17, 2013  /   Comments Off on የታማኝ በየነ መልእክት ከአውሮጳ

    Print       Email
0 0
Read Time:11 Minute, 41 Second

እንኳን ደህና መጣችሁ
እውቁ የሰባዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ታጋይ፡ጀግናውና እውነተኛው፡ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ፡አረቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ፡ክቡራትና ክቡራን፡ የዚህ መረሃግብር ታዳሚ የሆናችሁ፡የሀገሪ የእናታለም ኢትዮጵያ ልጆች፡በመጀመሪያ ጥሪያችንን አክብራችሁ፡ በስአቱ በመገኜታችሁ፡ በእራሴናበአዘጋጅ ኮሚቴው ስም፡ ከልብ፡ በማመስገን፡ እንኳን ደህና መጣችሁ እላለሁ።
የተከበራችሁ ወገኖቸ፡ሁል ጊዜም: እንደሚባለውና: በውልም እንደምታውቁት፡ኢሳት እንዳያይ፡ አይኑን ለተሸፈነው፡ የኢትዮጵያ ህዝብ አይን ነው፡
ኢሳት እንዳይሰማ፡ ጆሮውን ለተደፈነው፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ጆሮነው፡ኢሳት እንዳይናግር፡ አፉን ለታፈነው የኢትዮጵያ ህዝብ ልሳን ነው፡ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ፡ ህዝብንም፣ ታሪክንም፣ እግዚያብሄርንም፡የከዳውንና፣ የናቀውን፡ ከውልደቱ እስከ እለተ ሞቱ፡ ውሸትን ማጭበርበርና፡ ማስመሰልን የእለት ጉርሱ ያመት ልብሱ ያደረገውን፡፡
ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር፡ ከዓለም ካርታ እንድትፋቅና፡ እኔ ኢትዮጵያዌ ነኝ፡ በማለት፡ አፍሞልቶ ደረት ነፍቶ፡ የሚናገር ዜጋ፡ እንዳይኖር፡እድሜልኩን፡ ቀን እረፍት፣ ሌት እንቅልፍ አጥቶ፣ ሲሰራ የኖረውን፡የዘረኛውን፣ የአንባገነኑን፣ የነፍሰገዳዮን፣ በአንድ ቃል የጥፋት መልክተኛውን፡ የመለስ ዜናዊን፡ እልፈተ ህይወት ያፋጠነና፡
ቀሪ የወያኔን መንጋም እያርበደበደ ያለ፡ እርሳስ አልባ ሚሳየላችን ነው፡፡
ኢሳትን ስናስብ ደግሞ፡ ታማኝን ጨምሮ፡ ጀግኖቻችንን የኢሳት ጋዜጠኞችን፡ ባይነህሌናችን፡ መቃኜት የግድ ይሆናል፡፡
ብዙዎቻችሁ፡ እንደምታስታውሱት፡ጀግናው ወንድማችን፡ አበበ ገላው፡ግንቦ 18 ቀን 2012 በተፈጥሮው ድንጉጥና ፈሪ፡ ግን ጨካኝ የሆነውን፡
የመለስ ዜናዊን፡ አቅል ሊያስትው፡ ግንቦት 6 ቀን 2012 ኖረዌይ መጥቶ ነበር።
በዚሁ ቀን በነበረን የጋራ ምሽት፡ እኔ ፕሮግራሙን እመራ ስለነበር፡ጀግናው ወንድማችን፡ በማለት ሳሞግስው፡ እረተው እኔ ጀግና አይደለሁም ነበር ያለኝ፡
በበኩሌ ግን፡ ብዙው ኢትዮጵያዊ፡ ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ሲጠራ ለመገኜት በሚፈራበት ባሁኑ ወቅት፡ ፊት ለፊት ወጥታችሁ፡ የኢትዮጵያ
ህዝብ፡ የተጠማውን፡ እውነተኛ መረጃ በመስጠት፡ ላይ ያላችሁት የኢሳት ጋዜጠኞች በሙሉ፡ ለእኔ ከጀግኖች ሁሉ፡ የላቃችሁ ጀግኖቸ ናችሁ
ነበር ያልሁት፡ቃሌም ሰመረና አቤ ከዚህ ተመልሶ፡ 8ቀን ሳይቆይ፡ ሁላችሁም የምታውቁትን፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ሲያበራ የሚኖር ገድል አስመዘገበ፡፡
በስራውም እኛ ወገኖቹ እጅግ በጣም ኮራንበት፡ስለዚህ ወደ እለቱ ፕሮግራም፡ ከመግባታችን በፊት፡ ወንድማችን ታማኝ በየነ፡ኖርዌይ የምንገኝ፡ ኢትዮጵያውያን፡ በጋዜጠኛና አክቲቪስት፡ አበበ ገላው ላይ የተሸረበውን፡ የወያኔ ሴራ የምናወግዝ ብቻ ሳይሆን፡ከጎኑ ተሰልፈን፡ ከአእምሮና ከጉልበት አልፎ የአካልና የህይወት
ዋጋ፡ ለመክፈል፡ በቁርጠኝነት የተዘጋጀን መሆናችንንና፡ ለሌሎችም ጀግኖቻችን፡ ለኢሳት ቴሌቭዥንና ሪዲዮ ጋዜጠኞች፡ ያለንን አክብሮት፣ አፍቅሮትና፣ አድናቆት፣ ያደርስልን ዘንድ፣ ቃል እንዲገባልን፡ በእናንተ ስም፡ በታላቅ ትህትና እጠይቃለሁ።
ታማኝ ወንድሜ፡አመሰግናለሁ፡፡
ታማኝ ነህና፡ መልክታችንን፡ እንደምታደርስልንም፡ አንጠራጠርም፡ውድ ወገኖቸ፡ኢሳት፡ እርሳስ አልባ ሚሳየላችን ነው፣ኢሳት፣ ልሳናችን፣ አይንና ጆሮአችን ነው ካልን፡
ከሚደርስበት አፈና፡ እንጠብቀው ዘንድ፡ በእኛ እዚህ በምንገኝ ሁሉ ላይ፡ሰፊህዝብን ያህል፡ ሀያል አዛዥ፡ ታሪክን ያህል ሀቀኛ ተሟጋች፡በጀርባው ያሰለፈና፡ ልናመልጠው፡የማንችል፡ የትውልድ አደራ ተጭኖብናል፡፡
ብርቅዬውና፡ የመድረኩ ንጉስ፡ታማኝ በየነ፡ በመካከላችን የተገኜውም፡የእኛን አደራ ተጋርቶ፡ ኢሳትን ቀጣይ የሚያደርግ፡ ገንዘብ ለማሰባሰብ ነው፡፡
ስለሆነም፡ ኖርዌይዎች የምንታወቅበትን ልግስና፡ ዛሪም በማድረግ፡ያለንን የእናት ሀገር ፍቅርና፡ የወገን ክብር፡ ደግመን በተግባር፡መግለጽ ይጠበቅብናል፡፡
ውድ የሀገሪ ልጆች፡እሰከአሁን ሌላ ማንም ሳይሆን፡ የህሌና እና የመንፈስ፡ ጉልበቶቻችን ብቻ፡ ተጋግዘው እያዘዙን፡ለ21 አመት በእዬ ጓዳ ጎድጓዳው፡ ወያኔን አምተናል፣ ጨካኝነቱን እያጋለጥን ጽፈናል፣ ተሰልፈናል፣ በእዬ መድረኩ አውግዘናል፡፡ያመጣነው ለውጥ ግን የለም፡፡
በውግዘት፡ የሚመጣ ነገር ቢኖር ኖሮ፡ ደርግ ከመጥፋቱ በፊት፡ የአሜሪካ ኢንፔሪሊዝምን፡ ከአስር ጊዜ በላይ፡ በደመሰው ነበር፡፡
በአለም ታሪክ፡ በጩኸት፡ ነጻ የወጣች ሀገር ብትኖር፡ አንድ እያሪኮ ብቻ ነች፡አሁንካለፈው ተምረን፡ ነጻ ለመውጣት፡ ከጩኸት ይልቅ፡ ድርጊትን ማስቀደምና እጣታችነን ወደሌሎች ከመቀሰር፡ ይልቅ እኔ ምን ሰራሁ፡በማለት እራሳችንን፡ መጠየቅን መጀመር አለብን።
የዛሪው ኢሳትን፡ ለመደገፍ የምናደርገው፡ አስተዋጽኦም፡ ወደተግባራዊ ስራና እራስን ወደመጠየቅ፡ መሸጋገራችንን አመላካች ነው።
ባጠቃላይ፡ ኢሳት ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊ እነት፡ ያደረገውንና እያደረገ፡ ያለውን፡ መጠነ ሰፊ ተግባር፡ እየዘረዘርሁ የምታውቁትን በመድገም ጊዜያችሁን አላባክንም፡፡
በዚያ ፋንታ ግን በመጨረሻ የምለው ቢኖር፡ የመስተንግዶ ኮሚቴው፡ ታዳሚውን ለማስደሰት፡ ሁሉንም ነገር አሟልቶ፡ በመጠባበቅ ላይ፡ ስለሆነ ከእናንተ፡ የምንሻው፡ የተለመደውን ኢትዮጵያዊ፡ ጭዋነት ብቻ ነው፡፡
አሁንም አስተባባሪ ኮሚቴውን በመወከል፡ በድጋሜ እነኳን ደህና መጣችሁ እያልሁ፡ እለቱ እራሳችንን፡ በማዝናናት፡ልሳናችን የሆነውን፡ ኢሳትን፡ የምንረዳበት ቀን ነውና፡ እጃችን ፈታ ይበል፡ የሚለው ዋናው የመልእክቴ፡ መቋጫ ነው፡፡
አመሰግናለሁ
ማተቤ መለሰ ተሰማ
10.02.2013

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 17, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 17, 2013 @ 11:12 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar