www.maledatimes.com የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በበረሃ በውሃ ጥም ልንሞት ነው ሲሉ ምሬታቸውን ገለጹ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በበረሃ በውሃ ጥም ልንሞት ነው ሲሉ ምሬታቸውን ገለጹ

By   /   March 18, 2013  /   Comments Off on የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በበረሃ በውሃ ጥም ልንሞት ነው ሲሉ ምሬታቸውን ገለጹ

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 23 Second

ከባለፈው ሁለት ወራት ጀምሮ ውሃ ጠፍቶ ከተለያዩ ክልል ለትምህርት ብለው በካምፓስ ውስጥ ሰፈረው የሚገኙት በሱዳን ቦርደር እና በደቡብ ኢትዮጵያ አሶሳ (የቀድሞ ስሙ አቆልዲ) የቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል ዋና ከተማ ነው ።ከጥንት ጀምሮ  በከፍተኛ በበረሃነቷም የምትታወቀው አሶሳ ዛሬ ከፍተኛ የዉሃ ችግር እንደገጠማት እና መንግስት ምንም አይነት ውሳኔ ሳያሳልፍ ወራቶችን እንዳስቆጠረች እንደዚሁም በአካባቢው  ዉሃ ስለሌለ ከፍተኛ ኪሎ ሜትር ተጉዞ በቦቴ መኪና ተቀድቶ የመጣው ውሃ ጋዝ ጋዝ እያለ እንኳን ሊጠጣ የውሃ ጥምን ማርካት የማይችል እና በአሁን ሰአት አብዛኞቹ ተማሪዎችን ለዉሃ ወለድ ብሽታ ከመዳረጉም በላይ ምንም የተጠናከረ የጤና ኬላ እና የህክምና ባለሙያዎች እንደሌሉ በአሶሳ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች እና መምህራን አቤቱታቸውን ለማለዳ ታይምስ የዜና ማእከል እባካችሁ ችግራችንን አሰሙልን ሲሉ በላኩት መልእክት ገልጸዋል ።ተማሪዎቹ እንዳሉት ከሆነ እኛ ከቤተሰብ በምናገኛት እርዳታ ውሃ ገዝተን መጠቀም የማንችል ሲሆን የሚመጣውን ዉሃ ከችግራችን ለማምለጥ ስንል የባሰ ወደ ከፋ ችግር ላይ እንደወደቅን ሊረዱልን አልቻሉም ።በአሁን ሰአት ከሁለት ወራት በላይ ያለፈው የዉሃ ችግር በክፉኛ ብዙ ተማሪዎች በዉሃ ወለድ በሽታ እያሰቃየ የሚገኝ ቢሆንም  የዩኒቨርሲቲው አስተዳደርም ሆነ የአካባቢው ርእሰ መስተዳድር እንዲሁም መንግስት አቤቱታችንን ሊሰሙን አልቻልንም መፍትሄ አጥተናል በሰላም ከቤተሰቦቻችን ተለይተን በበሽታ ተጠምደን ልንገናኝ ወይንም ችግራችን ሳይታወቅ እንድንሞት አንፈልግም ትምህርት ለመቅሰም እንጂ በዉሃ ወለድ በሽታ እንድንሞት አይደለም የመጣነው ሲሉ አክለው ገልጸዋል ።የማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል ለቤንሻንጉል ክልል መስተዳድር ያደረገው የስልክ ጥሪ አልተሳካም አሁንም ደግመን እንሞክራለን ሆኖም ግን ከአስተዳደሩ ምላሽ የሚሰጡን ከሆነ አሁንም በራችን ክፍት ነው በበስልክ ቁጥሮቻችን ወይንም በዌብሳይታችን ላይ በሚገኙት ኢሜል መል እክት ማስተላለፊያ መንገድ ቢገልጹልን ደስተኞች ነን ማለት እንገልጻለን።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 18, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 18, 2013 @ 12:24 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar