www.maledatimes.com አቢዮት ልጇን ትበላለች አቶ ዕቁባይ በረኸ ይግባኝ ተጠየቀባቸው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አቢዮት ልጇን ትበላለች አቶ ዕቁባይ በረኸ ይግባኝ ተጠየቀባቸው

By   /   March 18, 2013  /   Comments Off on አቢዮት ልጇን ትበላለች አቶ ዕቁባይ በረኸ ይግባኝ ተጠየቀባቸው

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 24 Second

የቀድሞ የሜጋ ማስታወቂያ ሥራ አስኪያጅና የኦዲዮ ቪዡዋል አሳታሚዎች ማኅበር ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዕቁባይ በረኸ፤ የፌዴራል ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በእርሳቸውና እና በሜጋ ኪነጥበባት ማዕከል ላይ አቅርቦት በነበረው የታክስ ማጭበርበር ወንጀል ክርክር ጉዳይ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘው ዐቃቤ ሕግ ይግባኝ በማቅረቡ ምክንያት የደረሳቸውን የፍርድ ቤት መጥሪያ አልቀበልም ብለዋል በሚል ተከሰው ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ በትናንትናው ዕለት ልደታ በሚገኘው ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስምንተኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው የነበሩት አቶ ዕቁባይ በአሁኑ ወቅት የሜጋ ሥራ አስኪያጅ አለመሆናቸውን በመግለጽ መጥሪያውን ለመቀበል ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ተናግረዋል፡፡

ይግባኙን ያቀረበው ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ፤ ይግባኙን የጠየቀው በእርሳቸውና በድርጅቱ ላይ መሆኑን በመግለጽ ሁለቱን የይግባኝ አቤቱታዎች አጣምሮ ማቅረብ እንዲችል ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቆ ለመጋቢት 30 ቀን 2005 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡ ሜጋ ኪነጥበባት ከ1997 እስከ 2000 ዓ.ም ድረስ ገቢን አሳውቆ ግብርን ባለመክፈልና አትራፊ ድርጅት ሆኖ ሳለ እንደከሰረ በማስመሰል፣የደሞዝ ግብር እና ቫት አሟልቶ አልከፈለም የሚሉ ክሶች ሲቀርቡበት አብረው ተከሰው የነበሩት የድርጅቱ የቀድሞው ሥራ አስኪያጅ አቶ ዕቁባይ በረኸ ጥፋተኛ ተብለው የተጣለባቸው የአራት ዓመት እስራት በገደብ ተነስቶላቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡ አቶ ዕቁባይ በ2001 ዓ.ም ከሜጋ ከለቀቁ በኋ የግል ድርጅት አቋቁመው ‹‹ገመና›› የተሰኘውን ተከታታይ የቴሌቪዥኝ ድራማ አሠናድቶ በማቅረብም ይታወቃሉ፡፡Addis admass

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 18, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 18, 2013 @ 12:30 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar