www.maledatimes.com ጀማነሽ የማታውቃቸው ነገሮች በመንግስተአብ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ጀማነሽ የማታውቃቸው ነገሮች በ መንግስተአብ

By   /   March 18, 2013  /   Comments Off on ጀማነሽ የማታውቃቸው ነገሮች በ መንግስተአብ

    Print       Email
0 0
Read Time:12 Minute, 39 Second

ይህንን ጽሁፍ ከማንበብወ በፊት እዚህ ላይ በመጫን ይህን ያንብ“ተሀድሶን” ጠርገን ሳናስወጣ “ተዋህዶ” የሚሉ ደግሞ ብቅ ብለዋል

 rtetert
እረኛ ምን አለን በጦማሪ /ብሎገር/ ምን አለ?  መለወጣችንን ስናበስር በደስታ ነው:: ምክንያቱም ትኩስ ትኩስ በተለይ የቤተ ክህነት ወሬዎችን ሲችሉ የደረሱበትን ሳይችሉ የደረሱትንም ቢሆን የሚያቀርቡልን እነርሱ ሆነዋል:: የነማን እንደሆኑ ባናውቅም በወንጌል “ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ” የተባለውን ለጦማሪዎቹ ጠቅሰን ስናነብ እንደ ርግብ የዋህ እንደ እባብ ልባም ሆነን ነው:: ሰሞነኛውን የከተማ ወሬ ምስጋና ይድረሰውና ከሚሽርያ መጽሔት ቀድቶ ያቀረበልን “አንድ አድርገን” የተሰኘ የጡመራ መድረክ ነው:: መጽሔቱ ከጀማነሽ ሰለሞን ጋር ያደረገውን ቆይታ አስነብቦናል::

ቃለ ምልልሱ ያሳዝናልም ያበሳጫልም:: በዝርዝር ከማየት ይልቅ ዋናውን አሳብ በመምዘዝ በጥቃቅን ጉዳዮች ከመከራከር ለምናከብራትና ለምንወዳት ነፍስ የሚመጥን ቀላል ጥያቄ ላቀርብ ወደድሁ:: እህታችን ልትመልሳቸው የሚገቡ በርካታ ነገሮችን እንደዋዛ “አላውቅም” እያለች አልፋቸዋለች:: እንዴ እኛም እንጠይቅሻ ለምን አታውቂም? በሚገባ መመርመርሽን እርግጠኛ ካልሆንሽ ምስክር ልትሆኝ እንዴት
በቃሽ?

ያልሻቸውን ሁሉ ሳልቆጥር ዘጠነኛው የሚሽርያ ጥያቄ ላይ ወሳኝ ግን ያልመለስሽው ጥያቄ ላይ ትኩረት እናድርግ:: “የተዋህዶና የኦርቶዶክስን ልዩነት ያገኘሽው ከየት ነው ” የሚለው:: ለእኔ ዋናው ጉዳይ ያለው እዚያ ላይ ነው:: ጀማነሽ የጠቀሰችው መጽሐፍ“በቅዱስ ኤልያስ መልእክት” ሌላ ቦታ ደግሞ “ በቅዱስ ኤልያስ አዋጅ” ላይ የሚል ነው:: የጥቅስ ችግር ካልገጠማት እንዲህ ያለ የቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ አለመኖሩን ላረጋግጥልሽ እወዳለሁ:: ምናልባት በስሙ የታተመ መጽሐፍ ደርሶሽ እንደሆነ ከመጣልሽም ከመቅደድሽም በፊት መርምሪው የትኛው ኤልያስ የጻፈው ነው? መቼ ነው የጻፈው? አዲስ ግኘትም ከሆነ ከየት ተገኘ? በቃለ ምልልሱ የተጠቀሰው ነቢዩ ኤልያስ መቼም ስለ ጸጋና ቅባት ተዋህዶና ኦርቶዶክስ ጻፈ እንደማትይን እሙን ነው::

”በአደባባይ ሲሰበክ ሰምቼው አላውቅም” ብለሻል:: ይህን ማለትሽ ማለትሽ መልካም አደረግሽ:: ምክንያቱም ቢኖር ትሰሚ ነበር:: ቤተ ክርስቲያን ደብቃ የምትጠቀመው ምንም ዓይነት መጽሐፍ የላትም:: ተደብቆ የኖረ በማስመሰል ለመስበክ ለምን ተሞከረ? ብለሽም ማተት ትችያለሽ::  በዚህ ጉዳይ ጀማነሽ የት ድረስ ነው የሄደችው? የት እነማንን ጠየቀች? ስንት መጻሕፍትን አገላበጠች? እነዚህን ስናልፍ ደግሞ በምላሿ ውስጥ የወረወረቻቸው ሀሳቦች ፍንጭ ሰጪ ሆነው እናገኛቸዋለን:: “ቃለ ውግዘቱን ሲኖዶሱ አልተቀበለም ለምን እንዳልተቀበለ እኔ ውስጡን አላውቅም::” ጀማነሽ ካላወቅሽ ማድረግ የነበረብሽ ምንድን ነው? ያንን ብታደርጊስ ኖሮ ምን ይከሰት ነበር? በቀላሉ መልሱን ባገኘሽው ነበር:: “አላውቅም” መልስ ሊሆን አይችልም:: በሰለጠነ ዘመን አንችን ዓይነት ሰው በዚህ መንገድ ይስታል ተብሎ አይጠረጠርም::

የሊቀ ብርሃናት አድማሱ ጀንበሬን “መድሎተ አሚን” ብቻ ማንበብ የሚፈጥረው መረዳት ቀላል አይደለም:: የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መጻሕፍት ብዙዎቹ በስፋት የዳሰሱት ጉዳይ ነው:: በበርካታ የነገሥታት ዜና መዋእሎችና ገድለ ቅዱሳንም ተመዝግቧል:: በሚያስደንቅ ሁኔታ የታወቁ ጉባኤያት ተዘጋጅተው ክርክሮች የተካሔደባቸውና ውሳኔ /ብይን/ የተሰጠባቸው ነጥቦችን ነው ያነሳሽው:: አልፎ አልፎ በጠቀሻቸው አካባቢዎች የሚታየውን ልዩ ነት አካባቢው ድረስ በመሄድ ለቅድሥት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የዲግሪ ማሟያ ጽሑፍ/ዲማጽ/ ያቀረቡ አባትም ልጠቁምሽ ቀሲስ ስንታየሁ አባተ ይባላሉ:: ምንም እንኳ በአካል ባታገኛቸው መመረቂያ ጽሑፋቸውን በቤተ መጻሕፍቱ ልታገኝ ትችያለሽ:: ሰፊ ትንተና በቂ መረጃም ይሰጥሻል::  ከዚያ በፊት ግን የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ በሚገባ ሳትለይ  የልዩነት መፍጠሪያ መሣሪያ እንዳትሆኝ ሥጋት አለኝ:: አላውቅም የሚል ይጠይቃል ያነባል እንጂ የመሰለውን ሊያደርግ አይችልም::  “እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።” ነው ያለው ቅዱስ ጳውሎስ::/ሮሜ.10፥17/:: ከማን ነው እየሰማሽ ያለሽው?

ቃሉን እየደጋገመች መጠቀሟ የበለጠ ጀማነሽ ያልሰራቻቸው የቤት ሥራዎች መከማቸታቸውን ነው የሚያመለክቱት:: አሁንም በድጋሚ እንዲህ ትላለች:: “አባቶቻችንንም ለመውቀስ አይደለም:: ምስጢር ሆኖ ይሆናል አላውቅም::” ለመውቀስ ሕሊናዊ ድፍረት ያጣሽው ለምንድን ነው? አልጠየቅሻቸውማ:: ታሪኩ ተርከው ክርክሩን ሥዕላዊ በሆነ መንገድ ባቀረቡልሽ ነበር:: ምስጢር የምታደርጊያቸውን ነገሮች ለጊዜው ተያቸው እና በትህትና ወደ ታወቁ አበው ቀርበሽ መጽሐፍ እንደሚለው “የዱሮውን ዘመን አስብ፥ የብዙ ትውልድንም ዓመታት አስተውል፤ አባትህን ጠይቅ፥ ያስታውቅህማል፤ ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፥ ይነግሩህማል።”/ዘዳ.32፥7/:: ተብሏልና በመቅረብ አላውቅም ያልሻቸውን ሁሉ ታውቂዋለሽ::
ጀማነሽ ትቀጥልና ደግሞ በይሆናል ትመልሳለች:: “ወይ አሁን ጊዜው ደርሶ የተደበቀው ተንኮል ቅዱስ ኤልያስ በመምጣቱ ምክንያት ተገልጦም ሊሆን ይችላል::” እህታችን ሃይማኖት እኮ ነው እርግጡን ተናገሪ እንጂ::  እንደፋሽን በቀላሉ ልንከተለው የምንችለው ነገር አይደለም ያነሳሽው:: እንደ ትወናውም አድንቀን የምንተወውም አይደለም:: እነማን ናቸው ልትወቅሻቸው የማትፈልጊያቸው አባቶች? የትኞቹስ ናቸው ይህን ያህል ተከፋፍለው እየተሳደዱ ስላሉቱና ስለተገፉት አበው ያወጉሽ?
የመጣውስ ኤልያስ ማንነው? የት? በሚገባ ያጤንሻቸው አይመስሉም:: አቋም መያዝ ለሕዝብም ይፋ በማድረግ ለመወያየት መፍቀዷየሚያስመሰግን ነው:: ቢሆንም እንኳ የምትከፍለው መስዋእትነት ተገቢ ያልነበረ መሆኑን ስታውቅ የበለጠ ትጎዳለች:: ለዚህ ነው ሐዋርያው “ልዩ ልዩ ዓይነት በሆነ በእንግዳ ትምህርት አትወሰዱ፤” /ዕብ.13፥9/:: በማለት ያሳሰበው:: ምናልባትም ባሕታዊ መሰል አሳቾች ወጥመድ ውስጥ ገብታ ከሆነ የምናውቃት ሁሉ እንጠይቃት:: ማን ያውቃል በዚህ ቃለ ምልልስ ብዙዎችን ታስት ይሆናል ብለን እንደሰው ብናስብም:: ለመዳን ለመመለስም ምክንያት የምትሆንባቸው እድሎች አሉና አድናቂዎቿ ፣ወዳጆቿና ቤተቦቿ የየድርሻችን እንወጣ  ዘንድ ይገባል::

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 18, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 18, 2013 @ 10:42 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar