www.maledatimes.com ታማኝ ለአውሮጳውያኖች ጥያቄ ጠየቀ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ታማኝ ለአውሮጳውያኖች ጥያቄ ጠየቀ

By   /   March 18, 2013  /   Comments Off on ታማኝ ለአውሮጳውያኖች ጥያቄ ጠየቀ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 19 Second

ታማኝ፤በፍራንክፈርት ተዘጋጅቶ በነበረው መድረክ ላይ ታዳሚውን እንደሚከተለው ጠየቀ፦
<<በዓለማችን በፍጥነት ከሚያድጉ ነገሮች አንዱና ዋነኛው ምንድነው?>>
ታዳሚው ዝም አለ።
<ጢም ነው> በማለት ራሱ መለሰ።
<በፍጥነት በማደግ የጢምን ሪከርድ የሰበረውስ ማነው?> በማለት በድጋሚ ጠየቀ።
አሁንም ታዳሚው ዝም አለ።
<የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ነው> በማለት ራሱ ታማኝ መለሰ።
ይኽኔ አዳራሹ በሳቅ ተናጋ።
በእርግጥም መንግስትና ሚዲያዎቹ ፦ “ከዓለም ፈጣን እድገት ካዝመዘገቡ አገሮች ኢትዮጵያ አንደኛ ሆነች” በማለት “እየተመዘገበ ነው ስለተባለው እግጅ ፈጣን ዕድገት” ጆሯችን እስኪያብጥ ድረስ ደጋግመው ሢነግሩን ሰንብተዋል። አስቂኙ ነገር ያ <ከጢም> በበለጠ ሁኔታ <በፍጥነት ያደገው ኢኮኖሚ> ከነበርንበት ቦታ ፈቀቅ ሊያደርገን አለመቻሉ ነው። የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ሰሞኑን ይፋ ባደረገው የ2013 የሰብዓዊ ልማት ኢንዴክስ ኢትዮጵያ ከ 187 የዓለማችን አገሮች 173ኛ ላይ እንደምትገኝ ነው የነገረን።
በቀደመው ዓመታት፤ ኢትዮጵያ መጨረሻው የድህነት ጠርዝ ላይ እንደምትገኝ በተገለፀበት አንድ መድረክ ላይ የተገኙ አንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፦”መረጃው ይስተካከል፤ ከኛ በታች ሁለት አገሮች አሉ” ማለታቸው፤ በስብሰባው የነበሩትን ብቻ ሳይሆን ወሬውን የሰሙትን ሁሉ ለብዙ ጊዜ ፈገግ ሲያሰኝ መሰንበቱ አይዘነጋም። አሁንስ”እዚያው የድህነት ጠርዝ ላይ ነን” ሲባል፦ “መረጃው ይስተካከል፤ድሮ 2 አገር ነበር የምንበልጠው፤አሁን ትንሽ ከፍ ብለናል”ብሎ የሚከራከር ይጠፋል ብላችሁ ነው?

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 18, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 18, 2013 @ 4:23 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar