www.maledatimes.com እነ አቶ ስዩም መስፍን ከማእከላዊ አመራርነት ተባረሩ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

እነ አቶ ስዩም መስፍን ከማእከላዊ አመራርነት ተባረሩ

By   /   March 20, 2013  /   Comments Off on እነ አቶ ስዩም መስፍን ከማእከላዊ አመራርነት ተባረሩ

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 5 Second

ሰሞኑን ለቀናቶች  ጉባኤውን ሲያካሂድ የሰነበተው የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ህወሃት በማጠናቀቂያው የፓርቲውን 45 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫ እያካሄደ ይገኛል ።በዚህ ምርጫ ላይ ተሳታፊዎቹንም ሆነ ተሳታፊዎቹንም ለመግለጽ አልቻለም ነበር ሆኖም ግን በአሁን ሰአት ላይ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ሆነው ምርጫውን ምን ከምን ማድረግ እንዳለባቸው ግራ ገብቶአቸዋል ሲሉ የውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል።በተለይም ከአቶ መለስ ህልፈተ ህይወት በሁዋላ ከህወሃት ማእከላዊ ኮሚቲእ ጋር ዘላቂ የሆነ ጉዞ መጓዝ አደገኛ መሆኑን የተረዱት ጥቂት አመራር አካላቶች እራሳቸውን ለማግለል ወስነዋል ሲሉ አክለው ገልጸዋል ሆኖም ግን አንዳንዶች እንደሚሉት ከሆነ ቀጣዩ ጉዞአቸው ወደ አዘቅት ውስጥ ይከታቸዋል ስለዚህ እራሳቸውን መጠንቀቅ ስላለባቸው በጊዚእ ማሰናበታቸው ነው ።ከጥንሡ ካላሳመሩት በመለስ ትከሻ የተጓዙትን ያህል አሁን ግን ሊቀጥሉ አይችሉም በማለት ውሳኒኣቸውን ማሳለፋቸውን ጠቁመዋል ።

ወደ ትግል ከተቀላቀሉ በሁዋላ የአመራር ቦታውን ለመቆናጠጥ ያደረጉት ትግል በአጭር ጊዜ ውስጥ የተሳካላቸው እና ከ አመራር አካል የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ብሎም አምባሳደር እያሉ ህወሃትን ደም በማልበሱ የሚታወቀው እና  ለዓመታት ፓርቲውን በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ያገለገሉት አምባሳደር ስዩም መስፍን ፣ አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ፣ አቶ አርከበ ዕቁባይና አቶ ዘርዓይ አስገዶም አቀረብን ባሉት  ጥያቄ መሰረት እና ፓርቲው እየተገበረበርኩት ነው በሚለው  የመተካካት ሂደት መሰረት በአዲስ አባላት እንዲተኩ የወሰነ ሲሆን አንጋፋ አባላቱ በክብር ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ተሰናብተዋል ሲል የማእከላዊው ኮሚቲእ መግለጹን ውስጣዋቂ ምንጮቻችን አክለው ገልጸዋል ።

ላመንበት ዓላማ በመታገላችንና በመስራታችን አሁን ደግሞ በክብር በመሰናበታበታችን ክብር ይሰማናል ብለው የሽንገላ ቃል የተናገሩት እነ አቶ ስዩም መስፍን መጭው ጊዜ የከፋ እና አጓጉል ቦታ ላይ ሊጥላቸው እንደሚችል ጠንቅቀው እንደሚያውቁት ስለተረዱት ነው በማለት የማለዳ ታይምስ ሪፖርተር ከስፍራው ገልጾአል ።ይህ ቤንዲህ እንዳለ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫው ተካሂዶ የድምፅ ቆጠራ እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን በ እነ አዚእብ በኩል ዝምታን ከመምረጣቸውም በላይ አድፍጠው ተዋጊ ለመሆን ያሰቡ ይመስላሉ በስልጣን ድልድል ላይ ምንም ነገር ውስጥ የተካተቱበት ነገር እንደሌለ አክሎአል  ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 20, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 20, 2013 @ 4:35 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar