www.maledatimes.com አማረ አረጋዊ ሲፈተሽ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አማረ አረጋዊ ሲፈተሽ!

By   /   March 20, 2013  /   Comments Off on አማረ አረጋዊ ሲፈተሽ!

    Print       Email
0 0
Read Time:12 Minute, 40 Second

« ሪፖርተር » ጋዜጣ በመለስ ዜናዊ ትእዛዝ እንደተቋቋመ ያውቃሉ?

(ከኢየሩሳሌም አ.)E-Reporter
አዲስ አበባ አየር ማረፊያ፣ ነሃሴ 13 ቀን 1997ዓ.ም ፣ ምሽት 2 ሰዓት…ለእረፍት መጥቶ የነበረ ጓደኛዬን ለመሸኘት በስፍራው ተገኝቻለሁ። ..እንዳጋጣሚ በቅርብ ርቀት የ<ሪፖርተር> ጋዜጣ ባለቤት አማረ አረጋዊን አየሁት፤ ወደርሱ አምርቼ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ < ወደ አሜሪካ ለእረፍት የላከውን ልጁን ለመቀበል እንደተገኘ > ገለፀልኝ። …ከዛም ወደ ወቅቱ የፖለቲካ ትኩሳት በመግባት ወሬ ቀጥልን፤ በመሃከሉ አማረ ፥ « ..ሲሳይና እስክንድር የጋዜጠኝነት ካባቸውን አውልቀው ለምን በግልፅ ፖለቲከኛ አይሆኑም? » ሲል በሹፈት አይነት ጠየቀኝ። « ምን ማለት ነው?» ስል መልሼ ጠየቅኩት፤ ..« በግልፅ የሚፅፉትን አታይም እንዴ?..የቅንጅት ዋና አቀንቃኞች ሆነዋል እኮ..» ካለ በኋላ አያያዘና « ..ይህችን አገር ልደቱና ሃይሉ ሻውል እንዲመሯት ነው የሚፈልጉት?…ልደቱ ነው አገር ለመምራት የሚቀመጠው?..» ሲል ያቺ የማውቃት የአማረ ፌዝና ሹፈት ፈገግታ በስሱ እያሳየኝ፤ …በዛ ሰሞን አማረ <አቋሙን> ይፋ አውጥቶ በቅንጅትና በጋዜጦች በተለይም በኢትኦጵና ምኒልክ ጋዜጦች ላይ በየሳምንቱ ..ለገዢው ፓርቲ የወገነ የቃላት ጦርነት የገጠመበት ወቅት ነበር።
አዳምጬው ሳበቃ እንዲህ አልኩት፥ « አማረ በምርጫው ማግስት ምን ብለህ ነበርየፃፍከው?..የሽግግር መንግስት ይቋቋም..ብለህ አልነበር?.. አሁን አቋምህን ለምን እንደቀየርክ አውቃለሁ!..» ስለው አይኑን በልጥጦ፥ « ምንድነው የምታውቀው?» አለኝ።.. < አዜብ መስፍን በቢቲ ማስታወቂያ ባለቤት ፀጋዬ በኩል አስጠርታህ ሌላ አራተኛ ሰው ጭምር ባለበት ምንድነው የተነጋገራችሁት?..አዜብ ከባለቤቷ የተላከ መልክት ነገረችህ፤ እንዲህ ስትል፥ « ሁሉም ጋዜጦችና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተጠራርገው እስር ቤት ይገባሉ። አንተም መግባት ትፈልጋለህ ወይ?..በማለት መለስ ንገሪው ብሎኛል፤» ብላ ነግራሃለች። ከዛም አቋምህን ቀየርክ፤ » አልኩት።…ግንባሩን አጨማዶ ገላመጠኝ። ..አያያዝኩና፥ « ደግሞስ አገሪቷን ማን ይምራ ነው የምትለው?..ሕዝብ የመረጠው ማንም ይሁን ማን…ድምፁ መከበር አለበት። አንተ ግን ካለ ሕወሐት/መለስ ሌላ ሊመራ አይችልም ..እያልክ ነው..» አላስጨረሰኝም..ጥሎኝ ሄደ። በወቅቱ ጉዳዩን በኢትኦጵ ጋዜጣ ላይ ፃፍኩት..
አማረ፥ ከማስታወቂያ ሚ/ር ለምን፣ እንዴትና በማን ተባረረ?…« ሪፖርተር » ጋዜጣ በመለስ ዜናዊ <ልዩ> ትእዛዝ እንደተቋቋመ ያውቃሉ?..አሁን የቲቪ ስርጭት እንዴትና በማን ትእዛዝ ሊጀምር ቻለ?…ከነደብረፂዮን ጀርባ በምስጢር የሚሰጠው ድጋፍና ለፓርቲው የሚያደርገው ስውር ተጋድሎ….በሚሉና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ እመለስበታለሁ።

የአማረ ገመና ሲገለጥ!

602146_450872691655077_1071298125_n
(ከኢየሩሳሌም አ.)
አማረ አረጋዊ በማስታወቂያ ሚ/ር የኢቲቪ ስራ አስኪያጅ ሃላፊ እያለ በጣም አፀያፊ ተግባራትን በየእለቱ ይፈፅም ነበር። እሱን ጨምሮ አራት የሕወሐት ሃላፊዎች ተመሳሳይ ወራዳ ተግባር ይፈፅሙ ነበር፤ አንዱ ዋሽንግተን የሚገኝና የፓርቲው ሰላይ ሲሆን አንዱ የሻዕቢያ ተላላኪ ሆኖዋል፤ ሌላው ሹም በርካታ ሴቶችን የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ በሽታ ሆን ብሎ በማስያዝ አገር ቤት እንዳለ (እስከ 2000ዓ.ም) አውቃለሁ፤ አሁን ግን በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ መረጃው የለኝም።…
በወቅቱ ባለስልጣን የነበሩት አቶ ታምራት ላይኔ ጉዳዩን ሰምተው አማረን ግምገማ ይጠራሉ፤ ቃል በቃል እገልፀዋለሁ፥ « አማረ ቢሮ ውስጥ (office sex) ትፈፅማለህ፤ ..» በማለት በማስረጃ አስደግፈው ሲነግሩት፣ የሰጠው መልስ ፥ « በረሃ አይደለም ያለሁት፤ ስራዬን እስካልበደልኩ ድረስ የፈለኩትን ማድረግ እችላለሁ፤ መብቴ ነው..» የሚል ነበር። በዚህም ምክንያት በታምራት ትእዛዝ አማረ ከሃላፊነት እንዲነሳ ተደረገ።.. በእርግጥ አማረ ኢቲቪ እያለ ለጋዜጠኞችና ለፕሮግራም አዘጋጆች ሙያዊ ነፃነት በመስጠት በኩል ስሙ በበጎ የመነሳቱን ያክል፣ በአንፃሩ ለዜና አንባቢነት..ወዘተ ለመቀጠር የምትመጣ ሴት እንደግዴታ የሚቀርብላት ገላዋን ለአማረ <ማቅረብ> ነበር። በሕዝብ የሚታወቁና የተጎበኙ በዝርዝር ማንነታቸውን መግለፅ ቢቻልም ለዛሬው ማለፍን መረጥኩ። በነገራችን ላይ አንድ ሴት በግሩፕ ጭምር ቢሮ ውስጥ ያማግጡ እንደነበር ሳልጠቁም አላልፍም።…በተጨማሪ በወቅቱ የማ/ሚ/ር የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ « ዳንዲ» በሚለው መፅሃፍ እንደገለፁት « በስነምግባር ጉድለት የተገመገሙና እርምጃ የተወሰደባቸው እንዳሉ..» ጠቁመው ነበር። ያውም በጨዋ አገላለፅ!! ስም ግን አልጠቀሱም። አንዱ ግን አማረ ነበር።….
አማረ በአቶ ታምራት ውሳኔ በተላለፈበት ሰሞን እንዳጋጣሚ አቶ መለስ ለጉብኝት አውሮፓ ነበሩ። ሲመለሱ የጠየቁት « አማረ የታለ?» ብለው ነበር። የተፈጠረው ሁኔታ ተነገራቸው። አማረን አስጠርተው አነጋገሩት። ከዛም አማረ ጋዜጣ መጀመር እንደሚፈልግ ገለፀ። በሃሳቡ ተስማሙ። ጋዜጣው «እንደ መነፅር ሆኖ መንግስትን፣ፓርቲውን..» ማገልገል እንዳለበት ተስማሙ። በአቶ መለስ ቀጭን ትእዛዝ ለ<ሪፖርተር> ወይም « ኤም.ሲ.ሲ» ማስጀመሪያ አንድ ሚሊዮን ብር (በወቅቱ ምንዛሬ ከሁለት መቶ ሺህ የሚበልጥ ዶላር) እንዲፈቀድለት አደረጉ። ለገንዘቡ መፈቀድ የተሰጠው ሽፋን ወይም ምክንያት < የግልጋሎት ዘመን > የሚል ነበር። በአንፃሩ የእርሱን ሁለት ወንድሞች ጨምሮ 36ሺህ የፓርቲው ታጋዮች በመለስ ዜናዊ « ጓሓፍ » ወይም <ቁሻሻ> ተብለው ጎዳና በጅምላ የተጣሉት አንዳች ሳንቲም ሳይሰጣቸው ነበር። የትና ለማን ነው አማረ ያገለገለው?..ስንት አመት?..ሴቶች እህቶቻችን <ገላ> ላይ እንዳሻው <ስለተገለገለ> ?…የሚሉ አስገራሚ ጥያቄዎች መነሳታቸው ግድ ነው።
ያም ሆነ ይህ አማረ ከመለስ በተበጀለት የህዝብ ገንዘብ ..በግል ፕሬስ ሽፋን የሚነግድበትን <ጋዜጣ> ጀመረ። እንደተባለው <መነፅር> ሆኖ ቀጠለ። የአየር መንገድ ስራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ አህመድ ቀሎ ከሃላፊነት ሲነሱ በ<ጦቢያ> ጋዜጣ ላይ በወቅቱ በሰጡት መግለጫ « እኔን ያባረረኝ መንግስት ሳይሆን..ለመንግስት መስተዋት ሆኖ በሚያገለግለው ሪፖርተር ጋዜጣ ነው» ብለው ነበር።…አማረ ሲበዛ ቂመኛ ሰው ነው፤ ታምራት ላይኔን እስኪበቃው በጋዜጣው ተበቅሏቸዋል። ከታሰሩ በኋላ ፥ < ከመኖሪያ ቤታቸው ቁምሳጥን ውስጥ የተገኘ የፍቅር ደብዳቤ…» እያለ በየሳምንቱ ዘምቶባቸዋል።
(ይቀጥላል)
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 20, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 20, 2013 @ 5:15 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar