www.maledatimes.com የኢትዮጵያውያን የግፍ ቀንበር በመካከለኛው ምስራቅ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኢትዮጵያውያን የግፍ ቀንበር በመካከለኛው ምስራቅ

By   /   March 20, 2013  /   Comments Off on የኢትዮጵያውያን የግፍ ቀንበር በመካከለኛው ምስራቅ

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 37 Second

የኢትዮጵያውያን ጩኸት ከመካከለኛው ምስራቅ-     ብዙ ዜጎች ተገድለዋል ብዙዎችም ታስረዋል መንግስትም መፍትሄ አልባ ሆኖ ጥርስ የሌለው አንበሳ ሆኖአል ።  በዱባይ ለሚገኙትም ሰራተኞች የመውጫ ቪዛ እንዳይሰጣቸው የኢትዮጵያ መንግስት ለዱባይ የስደተኞች ጉዳይ ገልጦአል ወደ ሃገራቸው መግባት የሚፈልጉ ሴቶች በሙሉ በስቃይ ላይ ይገኛሉ ፣ወደየትኛውም አገር እንዳይዘዋወሩ የሚከለክል ህገደንብ ማውጣቱንም ከዱባይ የምትገኘው ወኪላችን ገልጻልናለች፣  –በሳኡዲ የመን ድንበር የታሰሩ እስረኞች ለመልቀቅ ገንዘብ እየተጠየቁ ነው::

በሳኡድ ፖሊሶችዛፍ ላይ  የታሰረው ኢትዮጵያዊ

በሺዎች የሚቆጠሩ በሳኡዲ የመን እስር ቤት ያሉ ስደተኞች አስፈላጊውን ክፍያ እየከፈሉ እንደሚለቀቁ የየመን የደህንነት ባለስልጣን መሃመድ ነጃድ አስታወቁ::

ሁነታዎችን አደገኛ ያደረገው ባለፈው የካቲት ወር ላይ ኢትዮጵያውያን ለሃገራቸው አደገኛ እና ህገወጥ አስጊ መሆናቸውን የሳኡዲ ሚዲያዎች (  http://www.youtube.com/watch?v=DSS4bAVP-fA  )الكنبه إذا عزمك أثيوبي تروح له ؟ / Couch if your determination Ethiopian his imagination?/ የተላለፈውን ዘገባ ተከትሎ ነው:: ይህን ዘገባ የሰሙ የሳኡዲ እና የየመን ዜጎች በድንበሩ አከባቢ እና በሳኡዲ አረቢያ ውስጥ ህገወጥ ናቸው ያሉዋቸውን ሰዎች እየያዙ ያስረክባሉ ቢባልም እውነታው ግን ከኢትዮጵያውያን ገንዘብ እንዲያመጡ ያስገድዷቸዋል::

በሳ ኡዲ  አሰሪዎቹ የተቃጠለው ኢትዮጵያዊ
በህገወጥ ደላሎች የተደፈሩ ሴቶች

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የኢኮኖሚ ድቀት እና የፖለቲካ አምባገነንነት ሸሽተው ወደየሰዉ አገር የሚሰደዱት ወገኖች
በወጣትነታቸው ሰርተው ራሳቸውን እና ቤተስቦቻቸውን ለመርዳት እንኳን አልታደሉም::ከተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት(http://www.un.org/apps/news/story.asp?NewsID=43928&Cr=yemen&Cr1=refugee#.UUiOcDcj8wq ) ባወጣው ዘገባ 84.000 ኢትዮጵያውያን የኤደንን ሰርጥ አቋርጠው በአስፈሪው የውሃ ማዕበል አልፈው ወደ መካከለኛው ምስራቅ ያቋርጣሉ::

አብዛኛው አስቸጋሪውን የባህር ጉዞ የጨረሰው በቀጥታ ወደ የመን ሳኡዲ ድንበር ይሄድ እና በህገወጥ ደላሎች እና ድንበር አሻጋሪዎች ወደ ሳኡዲ ለመግባት ሲሞክር በወሮበሎች በዘራፊዎች በአጭበርባሪዎች ገንዘቡን ይበላል ተይዞ ለፖሊስ ያስረክቡታል ፖሊስም ድጋሚ ገንዘቡን ይነጥቀዋል ::
በቅርብ ጊዜ የወጣ የUNHCR ሪፖርት ( http://www.middle-east-online.com/english/?id=51172 ) እንደሚያመለክተው የየመን እና የሱዲ የድንበር ላይ ባለስልጣናት ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ ኢትዮጵያውያንን አስገድደው ይደፍራሉ:ገንዘባቸውን በጉልበት ይነጥቃሉ ይላል::እንዲሁም ከቤተሰቦቻቸው ገንዘብ ይጠይቃሉ ያሌለውን ገድለው አካሉን በጥቁር ገበያ ይሸጡታል:: http://www.youtube.com/watch?v=2zTA4U0W3DI&feature=player_embedded

በሳዑድ ፖሊሶች የተያዙ ኢትዮጵያውያን በመኪና ታስረው በየተራ ሲጎተቱ
በየመን አደን ባህር ላይ የተገኘች ኢትዮጵያዊ ከነልጇ
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 20, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 20, 2013 @ 11:42 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar