www.maledatimes.com በዘገየው አብዮት ምሳዬን ቀታሁት - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በዘገየው አብዮት ምሳዬን ቀታሁት

By   /   March 23, 2013  /   Comments Off on በዘገየው አብዮት ምሳዬን ቀታሁት

    Print       Email
0 0
Read Time:11 Minute, 11 Second

ዛሬ ምሳዬን ቀጣሁት

ጧት ታክሲ ለመያዝ እየተጋፋሁ ባንዱ እጅ…ልዕልና ..የምትባለውን
ጋዜጣ አየሁና ታክሲ መሳፈሩን ትቼ ይህንንማ ሳላይ አልሄድም በማለት ወደ ጋዜጣ ሻጮች ዘንድ አመራሁ፡፡እስካሁን ተከራይቼ ነበር የማነበው፡፡ባንድ ጋዜጣ እስከ አንድ ብር ካምሳ ነው ክራይ፡፡የዛረው ግን ገና ርእሱን ሳየው ከራሴ እይታ ጋር በሀሳብ መገላበጥ ጀመርኩኝ፡፡.የጋዜጣው ትልቁ ርእስ ..የዘገየው አብዮት …ይላል.. በምስል ደግሞ መለስ ዜናዊ ብሄር ብሄረሰቦችን ይመስለኛል ተሸክሞ መቆም አቀቶት መሰለኝ ከነተሸከመው ነገር ባፍጢሞ ሊደፋ እንደ ደረሰ አይነት መንገዳገድ ይታይበታል( ገና ሳየው የመሰለኝን ነው እየተናገርኩኝ ያለሁት)፡፡ ስእሉ በጣም ተመችቶኛል፡፡ እኔ ግን በጣም ውስጤን በጥያቄ ያገላበጠው …የዘገየው አብዮት … የሚለው ነገር ነው፡፡ ምንማለት ነው እያልኩን የራሴን ሀሳብ መደርደር ጀመርኩኝ፡፡ የመለስ መሞት እራሱ አንድ አብዮት ነው ማለቱ ይሆን…የመለስ ዜናዊ መሞት ተከትሎ እየተነሳ ያለ አብዮት ካለ ከየት በኩል በኢህዴግ ውስጥ ወይንስ ከኢህአዴግ ውጪ … ብቻ አልመጣልንም በወቅቱ… የዘገየው … የሚለው ቃል ንክስ አድርጌ አነበብኩት አሰብኩት.. በኢትዮጵያ ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋርም በተለያየ አቅጣጫ ለማዛመድ እየሞከርኩኝ እያለሁ ጋዜጣ ሻጩ ገ ደረስኩና ስንት ነው ስለው አስር ብር አለን፡፡ በኪሴ የነበው አስራ ሰባት ብር ከአምሳ ሳንቲም ነበር፡፡ ከቤት ስወጣ አስራ አራት ብሩ ለምሳ መብያ ብዬ ነበር የበጀትኩት ሌላው ለታክሲ፡፡እሮብና አርብ ምሻ የምበላባት ምግብ ቤት አለች፡፡ ቤቱ ለሁለት የተከፈለ ነው፡፡ ባለ 14 እና ባለ 17 ብር በየአይነት የሚሸጥበት ተብሎ፡፡ ከትናንት ወዲያ ሶስትሆነን ነው በባለ 14ቤት የበላነው ምግብ ሁላችንም ሆድ ቁርጠት ለቆብን ነበር፡፡ አስታውሳለሁ ስንበላው በርበሬው እንደ ኢህአዴግ ካድሬ ነበር የሚያቃጥለው፡፡ንድድ ነበር ያልነው፡፡ ዘይታቸውም እግዜር ነው የሚያውቀው፡፡ እንዳውም ከዛ ቤት አለፍ ብሎ መንገድ ላይ ተነጥፈው ከሚሸቱት እቃዎች መካከል ሞጆ ዘይት ተብሎ በ27 ብር ይህ ዘይት ሱቅ ውስጥ ስትጠይቁ እስከ 55 ብር ነው፡፡ በርበሬ ደግሞ እሩብ ኪሎ 14 ብር ሱቅ በኪሎ እስከ 85 ብር ነው፡፡ ይህ ባለ 14 ብር በርበሬና ባለ 27 ብርዘይት ሳይሆኑ አይቀሩም ሆድ ሆዳችንን ያሉት፡፡ ይህንን ልተወውና ወደ ጋዜጣው ልመለስ ፡፡ ትንሽ ገለጥ ገለት አድርጌ አየሁት፡፡ ጥሩ ነው በተለይ አብርሃም ደቦጭ የሚባለው ስው ፣፣የመጽሀፍት ዳሰሳ ..በሚለው አምዱ ስር ስለ ፕሮፌሰር መስፍን መጽሀፍ…. የጻፋትን ሳይ የበለጠ ልቤ ተሰቀለና ግዛው ግዛው አለኝ ፡፡ ገዛሁት፡፡ሌላ ጊዜ ፍትህ ጋዜጣን እንገዛ የነበር ነው በአንድ ላምስ ተደራጅተን ነበር፡-መምህራን ማለቴ ነው-የትምህርት ቤታችን ፡፡
መንገድ ላይ ምንም ሳልከፍተው በቃ አጣጥፌ ቀትታ ወደ ት/ቤት አመራሁ፡፡ የመጀመሪያው ክፍለ ጊዜ ስላልነበረኝ ቀጥታ ወደ ቤተመጸሀፍት አመራሁና ማንበብ ጀመርኩኝ፡፡ መጀመሪያ የተሜን አንድ በሉ አየሁት…በጋዜጣው ፊትገጽላይ መለስ የተሸከመው ነየብሄርቤሄረሰብ ቅራቅንቦና .. በደንብ በቃል ተገልጾ ባላገኘውም… የመለስ መሞት አንዱ የአብዮቱ አካል እንደሆነና ለመጨረሻው ስኬት ግን የተቃዋሚ ሀይሎች እንቅፋት የበዛበት ተግባር ምክንያት እንደሆነ የተረዳሁ መስለኛል፡፡ ለእኔ .. የማይቀረው አብዮት የሚለው ርስ ከነ ምስሉ ፡ስንፍና ይዞኝ ነው እንጂ ጥሩ አንባቢ እና ተመልካች ካገኘ ባለ ብዙ ገጽ እና ትርጉም ያለው የነጻነት ደውል ነው( ግን ተመስገን ደሳለኝ በምስሉ ላይ የሚታዩት ሰልፈኞች ለምን የታህሪር አደባባይ ሰዎች እንዳረጋቸው አልገባንም-በብሄር ብሄረሰቦች ቀን የወጡ አሽቃባጭ ሰልፈኞች ቢሆኑ የበለጠ ሳይስማማ አይቀርም ነበር፣) !! በጣም ያናደደኝ የአብርሃም ደቦጭ ጽሁፍ ነው፡፡ የታሪክ ተመራማሪ ከሚለው መገለጫው ጋር በፍጹም የማይመጣጠን ትንተና፡፡አጠቃላይ ሀሳቡ ፕሮፌስር መስፍን የፈጠሯት ን ኢትዮጵያ አላውቃትም የየሚል ነው፡፡ርእሱን ብቻ ልንገራችሁ…የፕሮፌሰር የመጨረሻ ጥይት/ጥይቶች፡. ቢትል ኢንቲሞሎጂ?…የመጨረሻጥይት… የምትለዋ ነገር.. ምንማለት ነው ብሎ ትርጉሙን ለሚፈልግ ሰው አባባሉ ግልጽነው፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ቢደክሙም ቢደክሙም አልተሳካላቸውም ያለሟትን ኢትዮጵያ በሀሳብ እንጂ በእውን መሆን አልቻለችም ሚል ነው፡፡ አንዳንዶቹ ቃላቶች በጣም ..ከእኔ ንባብ ወጣ ያሉ ስለሆን ..ተጨማሪ ንባብ ሳያስፈልገኝ አይቀርም፡፡ግን ፕሮፌሰር መስፍን ያለሟት ኢትዮጵያ ሆና ኖራ ባለመገኘቷ አብርሃም ደስተና እንደሆነ፣፣፣ከአጻጻፉ መረዳት ይቻላል፡፡ የሳቸውን መጽሀፍ አስታከው የሆድ የሆዳቸው እየተናገሩ ያሉ ሰዎች የፕሮፌሰሩን መጽሀፍ ሆድ ማግኘት የቻሉ አይመስለኝም፡፡ ሁሉም የራሱን ሆድ ሁሉም የራሱን ሀገር ሁሉም የራሱን ታሪክ ብቻነው መፍጠር የሚፈልጉት የሚመስለው፡፡የኢትዮጵያ ሆድ የእኔም ሆድ ነው ብለው የነገሩን እሳቸው ብቻ መሰሉኝ -ፕሮፌሰር፡፡ በፈረንጅ የተደቀለ የታሪክ ዳቦ እየገመጡ በወረቀት ቀለም የወረፈሩረ ሁላ የራስ አጥንት የሌለው ማንነት á‹­á‹ž በተልፈሰፈሰ የባርነት እውቀት ይልመጠመጣል፡፡ ሌላውንም ለማልመጥመጥ ይፈልጋል፡፡፡፡ግዴለም ስለሚያናድድ ልተወውና አሁን 12፡00 አልፏል እራቴን ወደ እዚህ ጎተት አድርጌ ምሳን ብበላ ይሻላል፡፡አንድ ቀን ምሳና እራት በደንብ መብላት የቻልኩኝ እለት የሆዴን በጣም በመናደድ ለመግለጽእሞክራለው፡፡ አሁን ግን በባዶ መናደድ ባዶ እራስ ያደርጋልና እንደምንም ብዬ እራሴን ብጠብቅ ይሻለኛል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 23, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 23, 2013 @ 9:25 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar