www.maledatimes.com ማይክሮሶፍት በኢትዮጵያ ፋብሪካ የማቋቋም ሐሳብ እንዳለው ገለጸ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ማይክሮሶፍት በኢትዮጵያ ፋብሪካ የማቋቋም ሐሳብ እንዳለው ገለጸ

By   /   March 24, 2013  /   Comments Off on ማይክሮሶፍት በኢትዮጵያ ፋብሪካ የማቋቋም ሐሳብ እንዳለው ገለጸ

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 29 Second

ግዙፉ ኩባንያ ማይክሮሶፍት በአፍሪካ ለማካሄድ እንቅስቃሴ ከጀመረባቸው መስኮች ውስጥ አንዱ በሆነው የማኑፋክቸሪንግ ፋብሪካዎችን የማቋቋም እንቅስቃሴው ኢትዮጵያንም እንደሚያካትት አስታወቀ፡፡

በዚህ ዓመት ይፋ ያደረገውን ማይክሮሶፍት ኢንሼቲቭ አፍሪካ የተሰኘ ፕሮግራሙን ተከትሎ በመላው አፍሪካ እየተስፋፋ የሚገኘው ማይክሮሶፍት፣ በአፍሪካ ለሚያመርታቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች ማዕከላዊ የሥራ ማስኬጃ ግንባታዎችን በተመረጡ አገሮች እያካሄደ ይገኛል፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ ለሚያካሂደው የቴክኖሎጂ ገበያ እንቅስቃሴ ኬንያን በዋና መናኸርያነት መርጧል፡፡

ከኬንያ በመነሳት እንደ አገሮቹ የኢንፎርሜሽንና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትና የአይሲቲ ማኅበረሰብ መጠን ፋብሪካዎችን እንደሚመሠርት ያስታወቁት በማይክሮሶፍት የአፍሪካ ኢንሼቲቭ ፕሮግራም ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ፌርናንዶ ዳ ሱዛ ናቸው፡፡ ዳ ሱዛ እንዳስታወቁት፣ በኢትዮጵያ እተስፋፋ ያለውን የአይሲቲ ተጠቃሚ ማኅበረሰብ በመመርኮዝ ልዩ ልዩ የቴክኖሎጂ ምርቶችን የሚያወጣና የሚያመርት ፋብሪካ ለማቋቋም ታስቧል፡፡ ሆኖም የተረጋገጠ ነገር ላይ ባለመደረሱም የሚከፈተው ፋብሪካ በምን ሁኔታ ሊቋቋም እንደሚችል ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

ማይክሮሶፍት ለማቋቋም አስቤያለሁ ካለው ፋብሪካው በተጨማሪ በኢትዮጵያም ሆነ በምሥራቅ አፍሪካ የሚንቀሳቀሱ አነስተኛ ድርጅቶች ላይ የሚያተኩር የገበያ ስትራቴጂ ለመከተል እንዳሰበም ዳ ሱዛ አስታውቀዋል፡፡

ኩባንያው አፍሪካን በተለየ ሁኔታ የሚያስተናግድ የዋጋ ማስተካከያ ሊያደርግ መሆኑ ቢነገርም፣ ስለጉዳዩ በቀጥታ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ ለተማሪዎች በቅናሽ ዋጋና በነፃ የሚቀርቡ የተለያዩ ሶፍትዌሮች በማክሮሶፍት ይፋ መደረጋቸውን ግን አረጋግጠዋል፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ አገሮች ሶፍትዌሮችን በሕገወጥ መንገድ አባዝቶ መጠቀም የተለመደ ሲሆን፣ ይህንን ተግባር ለማስቀረት ወይም ለመቀነስ ሲባል ማይክሮሶፍት ለአንድ የሶፍትዌር ምርት ከሚጠይቀው 200 ዶላርና ከዚያ በላይ ዋጋ፣ ለአፍሪካ ማስተካከያ ሊያደርግ ማሰቡን ግን ለኢንዱስትሪው ቅርበት ያላቸው እየገለጹ ነው፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 24, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 24, 2013 @ 10:47 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar