www.maledatimes.com የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች የረሃብ አድማ መቱ,ፓትርያርኩ ሊያነጋግሯቸው ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተናገሩ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች የረሃብ አድማ መቱ,ፓትርያርኩ ሊያነጋግሯቸው ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተናገሩ

By   /   March 24, 2013  /   Comments Off on የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች የረሃብ አድማ መቱ,ፓትርያርኩ ሊያነጋግሯቸው ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተናገሩ

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 9 Second

-    ፓትርያርኩ ሊያነጋግሯቸው ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተናገሩ

መጋቢት 4 ቀን 2005 ዓ.ም. የተቃውሞ ደብዳቤ ለፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ያቀረቡት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች፣ ላለፉት አሥር ቀናት ትምህርታቸውን ከማቆማቸውም በተጨማሪ፣ ከመጋቢት 12 ቀን 2005 ዓ.ም. ምሽት ጀምሮ የረሃብ አድማ ማድረጋቸው ታውቋል፡፡

ተማሪዎቹ ያቀረቡት የተቃውሞ ደብዳቤ ለአንድ ሳምንት ምላሽ ስለተነፈገው፣ መጋቢት 12 ቀን 2005 ዓ.ም. ፓትርያርኩ በሚያስቀድሱበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ ልብስ ተክህኖ ለብሰው በመሄድ ቢጠብቋቸውም፣ ፓትርያርኩ ያለወትሮአቸው ሳይገኙ መቅረታቸውን ደቀ መዛሙርቱ ተናግረዋል፡፡

ከመልካቸው በስተቀር መጠሪያቸውና ማንነታቸው የማይታወቁ ግለሰቦች፣ አመልካች ጣታቸውን እየቀሰሩ ሊያስፈራሯቸው መሞከራቸውን የገለጹት ተማሪዎቹ ጥያቄያቸው ተገቢና አስፈላጊ በመሆኑ ምላሽ እስከሚሰጣቸው ድረስ የረሃብ አድማውንና ትምህርት ማቆማቸውን እንደሚገፉበት ተናግረዋል፡፡

ፓትርያርኩን በጽሕፈት ቤታቸው ተገኝተው ለማነጋገር ለመጋቢት 6 ቀን 2005 ዓ.ም. በንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ በኩል ቀጠሮ ተይዞላቸው እንደነበር የገለጹት ተማሪዎቹ፣ በዕለቱ ለመግባት ሲሞክሩ “የሲኖዶስ አባላት ስብሰባ ላይ ናቸው” በማለት በጥበቃ ሠራተኞች መከልከላቸውን ተናግረዋል፡፡

ከኮሌጁ ኃላፊዎች ጋር ሊያወያዩአቸው ወደ ኮሌጁ የመጡ የጠቅላይ ቤተ ክህነትና የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ተማሪዎቹ ያነሷቸውን ጥያቄዎች በማቅረብ ከማወያየት ይልቅ፣ ለመሸምገል መሞከራቸው እንዳሳዘናቸው የገለጹት ተማሪዎቹ እነሱንና የኮሌጁን ኃላፊዎች ሊያስማሟቸው የሚችሉት ያነሷቸውን ጥያቄዎች በመመልከት መፍትሔ እንዲያገኙ ሲያደርጉ ብቻ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡

ተማሪዎቹ ምግብ የማይበሉና ትምህርታቸውን የማይማሩ ከሆኑ የተሰጣቸውን ብርድ ልብስ፣ አንሶላና መታወቂያ አስረክበው የኮሌጁን ግቢ እንዲለቁ የኮሌጁ አስተዳደር ማስታወቂያ ማውጣቱ ግርምት እንደፈጠረባቸውም ገልጸዋል፡፡

ተማሪዎቹ ላቀረቧቸው ጥያቄዎችና በረሃብ አድማ ላይ ስለመሆናቸው ኮሌጁም ሆነ ቤተክህነት ምን እያደረጉ እንደሚገኙ ማብራሪያ እንዲሰጡን የኮሌጁ የበላይ ጠባቂ አቡነ ጢሞቲዎስን፣ የሥልጠናና ትምህርት ዋና ክፍል ኃላፊውን አባ ሠረቀንና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ አቡነ ፊሊጶስን አግኝተን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካልንም፡፡ source Reporter

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 24, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 24, 2013 @ 10:49 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar